2018-06-08 16:02:00

የሐሰት ዜናዎችን እንዴት ለይተን ማወቅ እንችላለን?


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጥር 16/2010 .. በሉርድ በተካሄደው  52 ዓለማቀፍ  የመገናኛ ብዙሃን ቀን ጉባሄ ላይ ያስተላለፉትን ምልእክት

እውነት ነጻ ያወጣችኃል” (ዩሐንስ 832)የውሸት ዜና እና ጋዜጠኛ ለሰላም

ክፍል ሁለት

2. የሐሰት ዜናዎችን እንዴት ለይተን ማወቅ እንችላለን?

ማንኛችንም ብንሆን እነዚህን ውሸቶች የመቃወም ግዴታ እንዳለብን ይሰማናል። የተጣራ እና እውነት የሆነ መረጃ ብዙውን ጊዜ ሆን ተብሎ በተሳሳተ ሁኔታ እና በተዘዋዋሪ በሚያሳዝን መልኩ በማታለል እና አንዳንድ ጊዜ የተራቀቁ የስነ-ልቦናዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ ተመሰርቶ ሐሰት በሆነ መልኩ ሰለ ሚቀርብ ይህንን መለየት ቀላል የሆነ ስራ አይደለም።

የእዚህን መልእክት ሙሉ ይዘት ከእዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ሰዎች በመገናኛ ብዙሃን የሚቀርቡ የሐሰት ዜናዎች ጋር ከመተባበር እና እነዚህን የሐሰት ዜናዎችን ከማሰታጨት ይልቅ፣ መረጃዎችን በሚገባ በመተንተን፣ መረጃዎች በግባቡ እንዲተረጉሙ እና እንዲገመግሙ፣ ውሸትን እንዲያስተባብሉ እና እንዲያጋልጡ በእዚህም ረገድ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስተማር የሚረዱ የትምህርት ፕሮግራሞችን ሲሰጡ ቆይተዋል። ይህንን ክስተት ለመግታት ያስችል ዘንድ ችግሩን የሚመለከቱ ደንቦችን ለማቋቋም የሚረዱ ተቋማዊ እና ሕጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ፣ የቴክኖሎጂ እና የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ኩባንያዎች መስፈርቶችን በማስቀመጥ በእጃቸው የሚገኙትን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዲጂታል የግለሰብ የግል መገለጫ መለያዎችን ተጠቅመው ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያግዙ ሥራዎችን እያከናወኑ ባለመሆናቸው በጣም ያስደንቃል።

ሆኖም ግን የተዛባ መረጃን መከላከል እና ለይቶ ማወቁ ጥልቅ እና ጥንቃቄ የተሞላበት የማስተዋል ሂደት ይጠይቃል። የእባብ ዘዴ በመባል የሚታወቀውን ዘዴ በመጠቀም  በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ላይ እርምጃን ለመውሰድ እና ለማጥቅት ዝግጁ የሆኑትን ሰዎች እኛ ለይተን ማወቅ እና ማጋለጥ ይኖርብናል። ይህ የሰይጣን የማጭበርበር ችሎታ በመጽሐፍ ቅዱሳችን በዘፍጥረት መጽሃፍ ውስጥ በሰው ልጆች ታሪክ አጀማመር ላይ የመጀመሪያውን የሐሰት ዜና ፈጠረ (ዘፍ 3 1-15)፣ በሰው ልጆች ኃጢአት አሳዛኝ ታሪክ የጀመረው፣ የሰው ልጅ የገዛ ወንድሙን መግደል በጀመረው (ዘፍጥረት 4)፣ በእግዚአብሔር፣ በጎረቤት፣ በማህበረሰቡ እና በፍጥረታትም ላይ ሳይቀር  በሚፈጸሙ  ስፍር ቁጥር የሌላቸው ክፉ ድርጊቶች ላይ የሰው ልጆች እንዲሰማሩ አደረገ። የዚህ የተዋጣለት "የውሸቶች ሁሉ አባት" የሆነ የእባቡ ዕቅድ (ዮሐ 8:44) ከእዚህ ጋር በጣም የሚመሰሳል ሲሆን በስውር የሚሰራ ተንኮል፣ በማባበል፣ ልብን በማሞቅ ወደ ውስጥ የሚገባ ውሸት እና ክርክር በጣም አደገኛ ነው።

በመጀመሪያው የኃጢያት ታሪክ ውስጥ ፈታኙ ወደ ሴቲቱዋ በመቅረብ በእርግጥ እግዚአብሔር፣በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉብሎአልን?”(ኦ. ዘፍጥረት 3፡1) በማለት ለእሷ ደኅንነት የተጨነቀ  እና ለእርሷ የሚያስብ ጓደኛ በመምሰል በከፊል ትክክለኛውን ነገር በመናገር በጀመረበት ወቅት፣ ሴቲቱም ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በርግጥ ትሞታለህ። (ኦ.ዘፍ.2፡17) የሚለውን የእግዚኣብሔር ቃል በማስታወስ የእባቡን ሐሳብ ታርማለች። ነገር ግን ሴቲቱ በየዋህነት መንፈስ  እባቡን እንዲህ አለችው፤ በአትክልቱ ስፍራ ካሉት ዛፎች ፍሬ መብላት እንችላለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአትክልቱ ስፍራ መካከል ከሚገኘው ዛፍ ፍሬ እንዳትበሉ፤ እንዳትነኩትም፤ አለበለዚያ ትሞታላችሁብሎአል። (ኦ.ዘፍ.3፡2) በማለት ትመልስለታለች። ይህ የሴቲቱ መልስ ሕጋዊ መሰረት የነበረው እና በአዎንታዊ ቃላቶች የተሞላ ነው፣ የእባቡን መልስ ካዳመጠች በኋላ እና አታላዩ በፈጠረው እውነት በሚመስሉ መልሶች፣ በእዚህም በመሳብ ሰቲቱ ተታለለች። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ሴቲቱ እባቡ ያቀረበውን መረጃ እውነተኛ መሆኑን /አለመሆኑን ማረጋገጫ በመሻት “ ይህንን ከበላን አንሞትም ወይ? ብላ ጥያቄ ታቀርባለች።

 ፍሬውን በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ  እንደ ሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ፣ እንደ እግዚአብሔር  እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው (ኦ.ዘፍ. 3፡5) ብሎ በመመለስ በእዚህም ተግባሩ ፈተኙ አፍራሽ ተግባሩን  እውነታን የተላበሰ በሚመስል መልኩ ያቀርባል። እግዚአብሔር የሰጣቸው የአባትነት ትዕዛዝ ለእነርሱ በጎ በማሰብ የነበረ ቢሆንም ቅሉ፣ ነገር ግን በጠላት የማታለል ተግባር የተነሳ  ሴቲቱም የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም  ለማግኘት የሚያጓጓ እንደሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው  ወስዳ  በላች፤ ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ (ኦ.ዘፍ. 3፡6) በእዚህም ምክንያት የእግዚኣብሔር ትዕዛዝ ዋጋ ቢስ ሆነ። ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው ታሪክ አሁን ላነሳነው ሐሳብ መሰረታዊ የሆነ አስተንትኖ እንድናደርግ አስፈላጊ የሆነውን ነገር በማሳየት፣ የተዛባ መረጃ በጣም ጎጂ የሆነ ነገር እንደ ሆነ በማሳየት፣ በተቃራኒው ደግሞ የተዛባ ወይም ሐሰት የሆኑ መረጃዎችን ማመን የሚያስከትለውን አስከፊ የሆነ ውጤት እንድንረዳ ያደርገናል። ሌላው ቀርቶ ትንሽ የተዛባ እውነት በራሱ እንኳን አደገኛ የሆነ ውጤት ሊያስከትል ይችላል።

እዚህ አደጋ ላይ የሚጥለን ራስ ወዳድነታችን ወይም ደግሞ ስግብግብነታችን ነው። የሐሰት ዜናዎች ብዙውን ጊዜ በብዙዎቹ ይታያሉ፣ በፍጥነት በመሰራጨታቸውም የተነሳ እነርሱን ማስቆም በጣም ከባድ ነው፣ ይህም የሚሆንበት ምክንያት እነሱን ማሰራጨት በራሱ የማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮችን ያበረታታል በሚል ሕሳቤ ሳይሆን፣ ነገር ግን በሰው ልጆች ውስጥ በቀላሉ ሊሰርጽ በሚችለው የስግብግብነት መንፈስ ምክንያት ነው። በኢኮኖሚው ዘርፍ በተንሰራፋው የማጭበርበር ተግባሮች እነዚህን የሐሰት መረጃዎችን በማሰራጭት ለስልጣን ያላቸውን ጥማት፣ ሐብትን ለማጋበስ እና ለመደሰት መሻትን ያመጣል፣ ይህም ይበልጥ አሳዛኝ የሆነ ነገርን በመፍጠር ተጠቂዎች እንድንሆን ያደርገናል፣ ከእዚህም በከፋ መልኩ ውስጣዊ ነፃነታችንን ሊያሳጡን ከሚችሉ ውሸቶች በባሰ ሁኔታ  ከአንዱ ውሸት ወደ ሌላ ውሸት በመሄድ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንድናማራ ያደርጋሉ፣ ይህም በጣም አሳዛኝ የሆነ ነገርን በመፍጠር ጭንቀት ውስጥ ይከታል። ሰዎች ክፉን ከደጉ በመለየት መልካም የሆኑ ውሳኔዎችን ማድርግ እንድችሉ፣ የኛን ጥልቅ ምኞቶች እና ዝንባሌዎች እንዴት ማስተካከል እንደ ሚገባ፣ ነገሮችን በሚግባ እንዲገመግሙ እና ፍላጎቶቻችንን እና ዝንባሌዎቻችንን በሚገባ እንዲረዱ፣ መልካም ለሆኑ ነገሮች ዓይናቸውን እንዲከፍቱ እና ማንኛውም ፈተና ማለፍ ይችሉ ዘንድ፣ ትምህርት እውነታን ለይቶ ለማወቅ አስፍላጊ ነው የምንለው በእዚሁ ምክንያት ነው።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.