2018-05-08 15:25:00

52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን በመጭው እሁድ ግንቦት 5/2010 ዓ.ም. እንደ ሚከበር ተገለጸ


በመጭው እሁድ ግንቦት 5/2010 ዓ.ም. 52ኛ ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን እንደ ሚከበር ይታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለእዚህ 52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን የመረጡት መሪ ቃል “እውነት ነጻ ያወጣችኃል፣ የሐሰት ዜና እና ጋዜጠኛ ለሰላም” የሚል መሪ ቃል እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው እሁድ በግንቦት 5/2010 ዓ.ም. የሚከበረውን 52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን አስመልክተው በትላንታንው እለት ከሬዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ አሌሳንድሮ ጂዞቲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደ ገለጹት የሰላም መንፈስ ማስፈን የሚችሉ ጋዜጠኞች ይበዙ ዘንድ በማበረታታት “ጋዜጠኞች ራሳቸው ሰው በመሆናቸው የተነሳ የጋዜጠኞ አገልግሎት ለሰው ልጅ መልካምነት እና ለሰላም መረጋገጥ” መሆን እንደ ሚገባው ገለጸው በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ የሚኖሩ የማኅበርሰብ ክፍሎች ከጋዜጠኞች ሙያ ጋር በተያየዘ መልኩ ከፍተኝ የሆነ ተግዳሮት እየገጠማቸው እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ከእዚህ ቀደም ይህ 52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን በፈረንሳይ ሀገር በሚገኘው ሉርድ በሚባል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጸበል በሚገኝበት የጸሎት ስፍራ የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ጴትሮ ጳሮሊን በተገኙበት ተከብሮ ማለፉን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ በካርዲናል ፔትሮ ጳሮሊን አማክይነት በጥር 16/2010 ዓ.ም ባስተላለፉት የጽሑፍ መልእክት “እውነት ነጻ ያወጣችኃል” (ዩሐንስ 8፡32)“የውሸት ዜና እና ጋዜጠኛ ለሰላም” በሚል አርእስት ጠንካራ እና ሰፊ የሆነ መልእክት ለዓለም ማስተላላፋቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጥር 16/2010 ዓ.ም “እውነት ነጻ ያወጣችኃል” (ዩሐንስ 8፡32)“የውሸት ዜና እና ጋዜጠኛ ለሰላም” በሚል መሪ ቃል ያስተላላፉት መልእክት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው የጋዜጠኝነት ሙያ የተከበረ ሙያ እንደ ሆነ በመግለጽ፣ ነገር ግን ይህ ሙያ በእውነት ላይ ብቻ መመስረት እንደ ሚገባው፣ ጋዜጠኞች ራሳቸው ሰው በመሆናቸው የተነሳ የአገልግሎታቸው ማዕከል የሰው ልጆች መሆን እንደ ሚገባቸው በመግለጽ፣ ጋዜጠኞች በተለይም በእውነት ላይ ተመስርተው ለዓለም ሰላም የበኩላቸውን ጥረት እንዲያድጉ የተመጽኖ መልእክት ማስተላለፋቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ጋዜጠኞች በማነኛውም መልኩ የሚሰጡት አገልግሎት ሕዝብ እና ሕዝብን ብቻ ማእከል ባደረገ መልኩ ሊሆን እንደ ሚገባው የገለጹት ቅዱስነታቸው ጋዜጠኛ ለሰላም፣ ጋዜጠኛ ለሕዝብ አገልግሎት፣ በተለይም ደግሞ ጋዜጠኞች ድምጽ ለሌላቸው ሰዎች ድምጽ መሆን እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው መገልጻቸው የታወቀ ሲሆን አንድ ጋዜጠኛ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ “ለሚፈጠሩ ውዝግቦች እና ለሚነሱ ግጭቶች መፍትሄ የሚሆኑ አማራጮችን በመጠቆም” ለተፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ የሚሆኑ ሐሳቦችን የሚያፈልቅ ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው በአጽኖት ገለጸዋል።

በጋዜጠኞች እና በሰላም መካከል ያለው ግንኙነት በማንሳት በመረጃ እና በአንድ ባሕል መካከል ያለው ግንኙነትን በተመለከተ ለየት ባለ ሁኔታ የተናግሩት ቅዱስነታቸው እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም ዓለማቀፍ የሰላም ቀን በተከበረበት ወቅት ማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን “የግድየለሽነትን ስሜትን በማሸነፍ” ለሰላም ግንባታ የሚደረገውን ጥረት በኃላፊነት መንፈስ ሊደግፉ እንደ ሚገባ መናግራቸውም የሚታወስ ሲሆን ጋዜጠኞች ክህሎቶቻቸውን የግል ፍላጎቶቻቸውን ብቻ ለሟሟላት ሳይሆን እውነትኛ የሆኑ ነገሮችን ብቻ ለማገልግል እንዲያውሉት ቅዱስነታቸው ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጪው እሁድ በግንቦት 5/2010 ዓ.ም የሚከበረውን 52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን አስመልክተው ከሬዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ አሌስንድሮ ጂዞቲ ጋር ባደርጉት ቆይታ፣ በተለይም ወጣቶች ከማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን መዋቅሮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው ማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ወይም አውታሮች ለወጣቱ ትውልድ መረጃን ከመስጠት ባሻገር የወጣቱን ትውልድ መጻይ እድል ላይ ጥላ የሚያጠሉ በመሆናቸው የተነሳ በእዚህ ረገድ ጋዜጠኞች መረጃ የሚያገኙበትን መነገድ እና ያገኙትን መረጃ የሚያስራጩበት ሁኔታ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

አንድ እውነተኛ ጋዜጠኛ “ድምጽ ለሌላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች ድምጽ ሊሆን እንደ ሚገባው” በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ማነኛውም መረጃ የምያንጽ፣ ሰላም የሚፈጥር እንጂ ሁከት እና ብጥብጥ የሚፈጥር ሊሆን እንደ ማይገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

Noti 2

በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 30/2010 ዓ.ም. ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ቀን ተከብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ቀን በዛሬው እለት ረፋዱ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ በርካታ የጣሊያን የቀይ መስቀል ማኅበር አባላት በተገኙበት መከበሩ የታወቀ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተገኘው ለጣሊያን የቀይ መስቀል አባላት አጠር ያለ ንግግር ማድረጋቸውን ለመረዳት ተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው ባለፈው ጥር ወር ከጣሊያን የቀይ መስቀል ማኅበር አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት የእናንተ ተግባር በመፍሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከተጠቀሰው የደጉ ሳምራዊ ተግባር ጋር ይመሳሰላል ማለታቸውን መዘግባችን ይታወሳል።

ላለፉት 150 ዓመታት ያህል በሚያዝያ 30 ቀን ይህ ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር ቀን እና ዓለማቀፍ የግማሽ ጨረቃ ማኅበር እንደ ሚከበር የሚታወቅ ሲሆን ይህም ቀን የሚከበረው የዛሬ 150 ዓመት ገደማ እነዚህን ሁለት ማኅበራት በመሰረተው እና ሰብዕዊ አገልግ`ሎቶችን በሕይወቱ ዘመን አከናውኖ ባለፈው ሲውዘርላንዳዊው ሄንሪ ዱናንት የልደት ቀን እንደ ሚከበር ይታወቃል።

የቀይ መስቀል ማኅበር በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ 17 ሚልዮን የቦጎ ሥራ አባልት እንዳልቸው የሚታወቅ ሲሆን በዋነኛነት “በአነስተኛ የሆኑ ልምዶችን በመጠቀም ህይወትን እንዴት ማዳን ይቻላል?" የሚለውን አመለካከት በዘጎች ውስጥ በማስረጽ ድነገተኛ የሆኑ አደርጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ሁሉ ዜጎች ባላቸው ችሎታ እና አቅም የአደጋ ሰላባ የሚሆን የማኅበርሰብ ክፍሎችን እንዴት ማገዝ እንደ ሚችሉ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ በተለይም ደግሞ ድንገተኛ የሆኑ ማንኛቸውም ዓይነት አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ለተጎችጂው የመጀመሪያ እርዳታ የሚሰጡበትን ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚረዳ ዓለማቀፍ ማኅበር ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት የተከበረውን ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ቀን በማስመልከት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ የስብሰባ አዳራሽ ከጣሊያን የቀይ መስቀል ማኅበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደ ገለጹት "አንድ የበጎ ፈቃድ ተልዕኮ መሆን የሚገባ አንድ እርዳታ ለሚፈልግ ሰው የሚያስፈልገውን እርዳታ ፍቅር በተሞላው መልኩ በነጻነት መስጠት እንደ መሆን እንደ ሚገባው ገልጸው በአጠቃላይ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን የደጉ ሳምሪዊ ተግባር ማከናወን መሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸው የተጎጂውን ሥነ ምግባራዊ ባሕሪይ ወይም ያለውን ሀይማኖት ከጥያቄ ውስጥ ሳናስገባ በተቻለን አቅም እና ፍጥነት ቁስሎቹን ማዳን እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ማሕበር ሰብኣዊ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ የተባሉ  ሦስት መርሆች ያለው ዓለማቀፍ ማኅበር እንደ ሆነ ያወሱት ቅዱስነታቸው በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ለምሳሌም በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በተፈጥሮ አደጋዎች እና ባህር ላይ አደጋ የሚያጋጥማቸውን ስደተኞ ስይቀር ለመርዳት በዓለማቀፍ ደረጃ እነዚህን በጎ ተግባራት በማስተባበር የእርዳታ ስራዎችን  በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተባበር ዋነኛው ተግባራቸው ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው በአክብሮ ገለጸዋል።

Noti 3

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ይህ የካቶሊክ ማኅበራዊ አስተምህሮ በሚል አርእስት ዘወትር ማክሰኞ  በእዚህ ሰዓት የምናቀርብላችሁን ዝግጅት አሁን ጀመረ። በእዚሁ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በተሰኘው ዝግጅታችን ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅብራዊ አስተምህሮ መስረት የጣሉ የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዎችን፣ ማኅበራውዊ አስተምህሮዎች እንዲሁም ይህ የቤተክርስቲያኑዋን ማኅበራዊ አስተምህሮ በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት የቤተ ክርስቲያን አባቶች የጻፉዋቸውን፣ ሐዋሪያዊ መልእክቶች እና ቃለ ምዕዳኖችን በመዳሰስ ነባራዊ የሆነውን የዓለማችን፣ የቤተክርስትያናችንን እና የሀገራችንን ሁኔታ በዳሰሰ እና ከግምት ባስገባ መልኩ ወደ እናንተ ማቀረብ አሁን እንጀምራለን። ይህ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ማሕበራዊ አስተምህሮ የሰኘ ዝግጅታችን ነው።

ቀደም ባሉት ጊዜያት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ሕጋዊ መሰረቱን፣ ታሪካዊ አጀማመሩን የሚጠቀምባቸው ዘዴዎችን በተመለከተ ሰፋ ያሉ አስተምህሮዎችን ማቅረባችን የሚታወ ሲሆን በተጨማሪም የካቶሊክ ቤተክርስትያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በመረጃነት ወይም በምንጭነት የሚጠቀባቸው መጽሐፍ ቅዱስ፣ የቤተክርስቲያን አባቶች በተለያዩ ውቅቶች ያስተማሩዋቸው አስተምኅሮች እና የጻፉዋቸውን ቃለ ምዕዳኖች፣ ሐዋሪያዊ መልእክቶች፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ እና አስተምህሮ፣ በነገረ መለኮት እን የፍልስፍና አስተምህሮዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ መሆኑ ገልጸና።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በዋነኝነት መሰረቱን የሚያደርገው የሰው ልጅን ክብር እና የማይገሰሱ መብቶቹን በቀዳሚነት ከግምት በማስገባት እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን 4 ምንጮች በመረጃነት በመጠቀም የሚሰጥ አስተምህሮ ነው።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ አራት ዋና ዋና መርሆችን መሰረት በማድረግ የቤተክርስቲያኗን አስተምኅሮ ማሕበራዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረግ ይጀምራል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያም ማኅበራዊ አስተምህሮ መሰረታዊ መርሆዎች የሚባሉት ውስጥ በቀዳሚነት የሚጥቀሰው የሰው ልጅ ሰብዐዊ ክብር የሚለውን ጽነሰ-ሐሳብ አብስተን ሰፋ ያለ አስተምህሮ ማቅረባችን የሚታወስ ሲሆን  በባልፈው ሳምንት ዝግጅታችን ደግሞ የጋራ ተጠቃሚነት የሚለውን  የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምሕሮ ሁለተኛ መርህ  በተመለከተ በመለከተ ከባልፈው ስምንት የቀጠል ዝግጅት  እንስደምጣችኃለን። አዘጋጅ እና አቅራቢ እኔው አባ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ ነኝ አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ አራት ዋና ዋና መርሆችን መሰረት በማድረግ የቤተክርስቲያኗን አስተምኅሮ ማሕበራዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረግ ይጀምራል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያም ማኅበራዊ አስተምህሮ መሰረታዊ መርሆዎች የሚባሉት ውስጥ በቀዳሚነት የሚጥቀሰው የሰው ልጅ ሰብዐዊ ክብር የሚለው ሲሆን፣ የጋራ ተጠቃሚነት፣ ኅበረት እና ድጎማ የሚሉት ናቸው።

ከእዚህ ቀደም ባስተላለፍናቸው ዝግጅቶቻችን የካቶሊክ ቤተክርስቲያም ማኅበራዊ አስተምህሮ አራቱ መርሆች መካከል የሰው ልጅ ሰብኣዊ ክብር የሚለውን መርህ ጠቅለል ባለ ሁኔታ ወደ እናንተ አድማጮቻችን ማድረሳችን የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው ማክሰኞ እለት ደግሞ የጋራ ተጠቃሚነት የሚለውን ሁለተኛውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ መርህ መመልከት መጀመራችን የሚታወስ ሲሆን የጋራ ተጠቃሚነት የሚለው ምርህ መነኛውም በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ የኑሮ ገጽታዎች በሙሉ ትርጉም ሊኖራቸው የሚችለው የተያያዙ እና የተቀናጁ ሲሆኑ ብቻ እንደ ሆነ የሚገልጽ ምርህ ሲሆን ይህም ሁሉም በማሕበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ የሰው ልጆች ሰብዕዊ ክብራቸው የተጠበቀ፣ ሕብረት ያላቸው እና በእኩልነት የሚታዩበት ማሕበረሰብ መመስረትን በቅድሚያ የሚመለከት መርህ መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል። በዛሬው እለት ዝግጅታችን ደግሞ የእዚህን የጋራ ተጠቃሚነት የሚለውን መርህ ባልፈው ስማንት ካቆምንበት በመቀጠል እንሰማችኃለን አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከውዲሁ እናጋዝባለን።

Break

በአጠቃልይ ይህ “የጋራ ተጠቃሚነት” የሚለው መሰረታዊ መርህ ሁላችንም አንዳችን ለአንዳችን ኃልፊነት ሊሰማን እንደ ሚገባን የሚያስታውሰን መርህ ነው።በማህበረሰባዊ ሁኔታዎች ውስጥ የእያንዳንዱ ግለሰብ እና የእያንዳንዱ ማህበረሰብ ፍላጎታቸውን መሙላቱን እና እምቅ ችሎታቸውን ለማኅበረሰቡ የጋር ተጠቃሚነት አሙጠው መጥቀማቸውን ማረጋገጥ እንችል ዘንድ ያሳስበናል። በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ቡድኖችና የሌሎች ቡድኖች መብትና ምኞት፣ እንዲሁም የመላው የሰው ልጅ ደህንነት ማሰብ እንደ ሚገባን የሚያሳበን መርህ ነው።

“የጋራ ተጠቃሚነት” የሚለውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ሁለተኛ መስረታዊ መርህ  በምናስብበት ወቅት ሁሉ ራሳችንን ለመጠየቅ የሚረዱ ቁልፍ ጥያቄዎች አሉ። "እያንዳንዱ ግለሰብ እና እያንዳንዱ የማኅበረሰብ ክፍል የማኅበረሰቡ የጋራ ጥቅሞች ተካፋይ ነው ወይ? ወይስ ደግሞ ከእዚህ የተገለሉ ግለሰቦች ወይም ደግሞ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሉ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።

2.1. በማኅበረሰቡ ውስጥ የጋራ ተጠቃሚነት ይሰፍን ዘንድ የማድረግ ሂደት የእያንዳንዱ ግለሰብ ኃፊነት ነው። የጋራ ጥቅምዎችና ፍላጎቶች በእያንዳንዱ ታሪካዊ ሂደቶች ውስጥ  በማህበራዊ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ከግለሰቡን እና መሠረታዊ መብቶቹን ከማክበር እና ከማስተዋወቅ ጋር የተያያዙ ናቸው። እነዚህ ፍላጎቶች ለሀገር ሰላም` ለመንግሥት ስልጣን መቋቋም፣ ጥሩ የሆነ የህግ መዋቅር እንዲኖር፣ለአካባቢ ጥበቃ እና ለሁሉም አስፈላጊ አገልግሎቶችን መስጠት፣ በተለይም የሰብአዊ መብቶችን፣ ምግብን፣ ለትምህርት፣ ለመጓጓዣ፣ መሠረታዊ የጤና እንክብካቤ፣ የመናገር እና ሐሳብን በነጻነት መግለጽ፣ እንዲሁም የሃይማኖት ነፃነት ጥበቃ ማድረግን ይመለከታል። በእዚህ ረገድ የጋራ ተጠቃሚነት የሚለውን ሁለተኛውን መሰረታዊ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በምንመለከትበት ወቅት መረሳት የሌለበት ጉዳይ ሊሆን የሚገባው የጋራ ተጠቃሚነት ሲባል በአንድ የተወሰነ ማኅበረሰብ ውስጥ ወይም በአንድ የተወስነ ሀገር ውስጥ ሊደረግ ሊኖር የሚገባው የጋራ ተጠቃሚነት ብቻ ማለት ሳይሆን በዓለማቀፍ ደረጃ ሳይቀር አንድ ሰው ለሰብአዊ ፍጡሩን ሁሉ እና ለመጪው ትውልድ የጋራ ጥቅም የሚሆን እውነተኛ ዓለም አቀፍ ትብብር ለማድረግ እያንዳንዱ ሀገር የሚጠበቅበትን ሁሉ ማድረግ እንደ ሚገባ መዘንጋት የለበት ጉዳይ ነው። የጋራ ተጠቃሚነት ሁሉንም የማህበረተሰብ አባላት የሚያካትት ጽንሰ ሐሳብ ነው፣ እያንዳንዱ ሰው እንደ የአቅሙ ለማኅበረሰቡ ልያደርገው የሚገባው አስተዋጾ እና በተቃራኒው ደግሞ ማኅበረሰቡ ለግለሰቡ ልያደርገው የሚገባው መላክ አስተዋጽን ያመለክታል። በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ እና በሀር አቀፍ ደረጃ በተጭማሪም በማኅበረሰብ ደረጃ በግለሰቦች መካከል በስፋት የሚስተዋለው የሀብት ክፍፍል ልዩነት አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የጋራ መኖሪያችን የሆነችው ምድራችን የምትሰተንን ገጸ በረከት ሁሉም የሰው ልጆች በእኩል ደረጃ ሊጠቀሙበት እንደ ሚገባ የበኩላችንን ኣምድረግ የሚጠበቅብን ሲሆን በሀግራቀፍ እና በማኅበርሰብ ደረጃ ስይቀር ፍትሃዊ የሆነ የሐብት ክፍፍል እንዲኖር የበኩላንን ድርሻ ማበርከት የግባናል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ቀደም ሲል ያስደመጥናችሁ የካቶሊክ ማኅበራዊ አስተምህሮ የተሰኘውን በአባ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ የተዘጋጀውን ሳምንታዊ አስተምህሮ ነበር። አብራችሁን በመሆን ስለተከታተላችሁን ከልብ እና መሰግናለን።

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.