2018-04-16 15:58:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ባልንጀራችንን መጉዳት እግዚኣብሔርን እንደ ማሳዘን ይቆጠራል” ማለታቸው ተገለጸ።


የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳኤ በዓል ከተከበረ እነሆ ሦስተኛው ሳምንት ላይ እንደ ምንገኝ ይታወቃል። ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ሦስተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት በታላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 07/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባስሙት ስብከት እንደ ገለጹት ባልንጀራችንን መጉዳት እግዚኣብሔርን እንደ ማሳዘን  ይቆጠራል ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 07/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በእዚህ ሦስተኛው የፋሲካ ሰንበት ቀን የእርሱ የነበሩ ደቀ-መዛሙርት በሙሉ በአንድነት ተሰብስበው በነበረበት ወቅት ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ተገልጦላቸው እንደ ነበረ በመኣከልነት ተገልጾ ይገኛል። ይህም በተለይም ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርቱ በመገለጥ እንደገና "ሰላም ለእናንተ ይሁን!" በማለት ሰላምታ አቅርቦላቸው እንደ ነበረ ቅዱስ ወንጌል ይመሰክራል። ሰላም ለእናንተ ይሁን በማለት ሰላምን የሚሰጠን ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ነው። ይህም ውስጣዊ የሆነ ሰላምን እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በምናደርገው ግንኙነት የምንመስርተው ዓይነት ሰላም ነው። ወንጌላዊው ሉቃስ ያቀረበው ምስክርነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ከሙታን መነሳቱን ያሳያል። ኢየሱስ በመንፈስ ብቻ አልነበረም የተገለጠው። በእርግጥ ይህ ታሪክ ኢየሱስ በመንፈስ ብቻ አለመገለጡን በማውሳት ሙሉ በሙሉ ከሙታን የተነሳው ከእውነተኛ አካሉ ጭምር እንደ ሆነ ያሳያል።

ደቀ-መዛሙርቱ  እርሱን ባዩ ወቅት ደንግጠው በፍርሀት መዋጣቸውን ኢየሱስ ተርድቶ የነበረ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት የትንሳሄውን ሁኔታ በወቅቱ እነርሱ ሊረዱት ያዳገታቸው እውነታ በመሆኑ የተነሳ ነው። እነርሱ ግን ደንግጠው በፍርሀት ተዋጡ፤ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ መንፈስ ብቻ አይደለም፣ በአካል እና በመንፈስ ነው የተገለጠው። ይህንን እንዲያምኑም ለማድረግ በማሰብእጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ እኔው ራሴ ነኝ። ደግሞም ንኩኝና እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና ዐጥንት የለውምና” (ሉቃስ 2439) በማለት ያስረዳቸውም በእዚሁ ምክንያት የተነሳ ነው። ይህ ደግሞ ደቀ-መዛሙርቱን ለማሳመን በቂ አልነበረም። ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ደቀ-መዛሙርቱ ከመደሰታቸው እና ከመገረማቸው የተነሳ ለማመን ተቸግረው እንደ ነበረ በመጥቀስ አንድ  የምያስገርም ነገር ይናገራል፣በፍጹ ሊሆን የማይችል ነገር ነው፣ በታላቅ ደስታ በፍጹም ይህ ነገር ሊሆን የማይችል ነገር ነው!ይሉ ነበር። እነርሱም ይህንን እውነታ በይበልጥ እንዲረዱት ለማድረግ በማሰብ ኢየሱስበዚያ ቦታ አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” አላቸው። እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራሽ ሰጡት፤ እርሱም ተቀብሎ በፊታቸው በላ (ሉቃስ 2441) ይህንንም ያደርገው እንዲያምኑ ለማድረግ አስቦ ነበር

የእርሱ ትንሳኤ እውነታ አፅንዖት የሰጠው አካልን በተመለከተ ክርስቲያኖች ያላቸውን የአመለካከት ገጽታ የሚያነጸባርቅ ነው፣ አካል እንቅፋት ወይም ደግሞ ነብሳችን የምትቀመጥበት እስር ቤት አይደለም። አካላችን በእግዚኣብሔር በመፈጠሩ የተነሳ አንድ ሰው በአካል እና በነብስ በሁለቱም ሕብረት ካልተዋቀረ ሙሉ ሰው ነው ለማለት አንችልም። ሞትን ድል በማድረግ በአካል እና በነፍስ ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ስለ አካላችን አወንታዊ አስተሳሰብ ሊኖረን እንደሚገባን ያስገነዝበናል። አካላችን ኃጢያት እንድንሰራ አጋጣሚ የሚፈጥር ወይም መሳሪያ ሊሆን ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን ኃጢአት በአካላችን ድክመት የተነሳ የሚከሰት ነገር ሳይሆን ነገር ግን ከእኛ ግብረ-ገብ ድክመት የመነጨ ነው። አካላችን ከነብሳችን ጋር ሕብረት በመፍጠር የእርሱን አርዕያ እና አምሳያን ለመግለጽ ከእግዚኣብሔር የተሰጠን ድቅ ስጦታ ነው። ስለዚህ እኛ የእኛንም ሆነ የሌሎችን ሰዎች አካል ታላቅ ክብር ልንሰጥ እና እንክብካቤ እንድናደርግ ተጠርተናል።

በማንኛውም መንገድ በባልንጀራችን እና በራሳችን አካል ላይ የምናደርሰው ጉስቁልና፣ ቁስል ወይም ግፍ ፈጣሪ በሆነው በእግዚኣብሔር ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው። በዛሬው ቀን በተለየ ሁኔታ በአካላቸው ላይ በተለያየ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰባቸው የሚገኙ በተለይም ልጆች፣ ሴቶች እና በአረጋውያን ለማሰብ እፈልጋለሁ። በእነዚህ ሰዎች አካል ውስጥ እኛ የክርስቶስን አካል እናገኛለን። የቆሰለውን፣ የተፌዘበትን፣ የተዋረደውን የተገረፈውን እና የተሰቀለውን ክርስቶስን እናገኛለን። ኢየሱስ ፍቅርን አስተምሮናል። ይህም ፍቅር በእሩስ ትንሳሄ ከኃጢኣት እና ከሞት በላይ ኃይል ያለው መሆኑን በመግለጽ አሁን እኛ ባለንበት ዓለማችን ውስጥ በባርነት ቀነበር ስር ወድቀው አካላቸው እየተጎዳ ያሉትን ሰዎች በሙሉ ለማዳን ይፈልጋል።

አቅመ ደካማ በሆኑት ሁሉ ላይ በተደጋጋሚ በኃያላኑ አማክይነት አሁን ባለንበት ዓለማችን እየተነሰራፋ ባለው ጭቆና እና መንፈሳችንን አንቆ በያዘው ለቁሳዊ ነገሮች ብቻ የምናሳየው ፍላጎት የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እነዚህን ነገሮች በጥልቀት እንድንመለከት እኛን በመጋበዝ በታላቅ አግራሞትና ደስታ ከሙታን የተነሳውን ክርቶስ እንድንገናኝ ይጋብዘናል። 

እርሱ በታሪክ ውስጥ በዘራቸው ወደ አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር መጓዝ የሚያስችሉንን ነገሮች ብቻ መርምረን የምናውቅ ሰዎች እንድንሆን ይፈልጋል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በእዚህ መነገድ ላይ በምናደርገውን ጉዞ እንድትረዳን እና በእናትነት አማላጅነቷ ከእኛ ጋር ትሆን ዘንድ በመተማመን እንማጸናለን።

 

“የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ! ይበልሽ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና!” ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች ቀደም ሲል ያነበባችሁትን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌላ ላይ መስረቱን አድርጎ ከነበረው አስተንትኖ ካሰሙ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስትስትያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከሚቀርቡት የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበለሽ፣ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለመላው ዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በትላንትናው እለት በማዳጋስካር የብጽዕና ማዕረግ የተሰጠው፣ የአንድ ቤተሰብ አባት የሆነ፣ ክርስቶስን ጀግንነት በተሞላ መልኩ ሰማዕት በመሆን ጭምር ክርስቶስን የመሰከረ ሉቺያኖ ቦቶቫዞ የሚባል ሰው የብጽዕና መረግ እንደ ተሰጠው ቅዱስነታቸው ገለጸዋል። ብጹዕ ሉቺያኖ ቦቶቫዞ ለጌታ ያለውን ታማኝነት በመግለጹ ብቻ የተነሳ ተይዞ መታሰሩን እና ከእዚያም መገደሉን የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም በጀግንነት የተሞላ ተግባሩ ለቤተ ክርስትያን እና ለእኛም ለእያንዳንዳችን እምነታችንን በታላቅ ጽናት እና ፍቅር መመስከር እንደ ሚገባን ያሳየን በመሆኑ የተነሳ ይህንን የብጽዕና ማዕረግ ለማግኘት በቅቱዋል ብለዋል።

ምንም እንኳን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግሮችን ለመፍታት በቂ የሆነ ሁኔታዎች ያሉት ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን አሁን ባለው የዓለም ሁኔታ በጣም መጨነቃቸውን በመግለጽ መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም በሶርያ እና በሌሎች የአለም ክፍሎች ውስጥ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው የጋራ ተግባር ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በዓለማችን ውስጥ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ያለማቋረጥ እንደ ሚጸልዩ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ሁሉችሁም በዓለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጸሎት እንድታደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

የዓለማችን የፖሌቲካ ኃይሎች በዓለማችን ውስጥ ሰላም እና ፍትህ ይሰፍን ዘንድ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ቅዱስነታቸው ጨማረው ጥሪ ካቀረቡ በኃላ እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትርሱ ብለው ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኃላ ተስናብተዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.