2018-04-03 14:59:00

በፋሲካ በዓል ወቅት የተሰጠን የወንድማማችነት መንፈስ የክርስቲያኖች የሕይወት መገለጫ ሆኖ ሊቀጥል ይገባል


የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ባለፈው እሁድ በመጋቢት 23/2010 ዓ.ም. በድምቀት ተከብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 24/2010 ዓ.ም. ደግሞ መልኣኩ “ክርስቶስ ከሙታን ተንስቱዋል” በማለት ለማሪያም እና ለመቅደላዊት ማሪያም ያበስረበት ቀን በታላቅ መንፈሳዊነት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ  ቅዳሴ መከበሩ ታውቁዋል። በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት በፋሲካ በዓል ወቅት የተሰጠን የወንድማማችነት መንፈስ የክርስቲያኖች የሕይወት መገለጫ ሆኖ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ከፋሲካ በዓል ቀጥሎ የሚገኘው ቀንየመላእክት ሰኞበመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም መጠሪያ ያገኘው  ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምንጮች ጋር በተገናኘ መልኩ በጥንት ጊዜ ከነበረው  በጣም ውብ ከሆነ ባህል መሰረቱን ያደርገ ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ (ማቴዎስ 28:1-10, ማርቆስ 16:1-7, ሉቃስ 24:1-12) እንደ ተጠቀሰው ሴቶቹ ወደ ኢየሱስ መቃብር በሄዱበት ወቅት መቃብሩ ክፍት ሆኖ አገኙት። ከእዚህ ቀደም መቃብሩ በአንድ ትልቅ ድንጋይ ተዘግቶ ስለነበር ወደ መቃብሩ ውስጥ ለመግባት ፈርተው ነበር። አሁን ግን ክፍት ሆኖ አገኙት፣ ከመቃብሩ ውስጥምኢየሱስ በእዚህ ስፍራ የለም፣ ከሞት ተነስቱዋልየሚል ድምጽ ሰሙ።

እነርሱምክርስቶስ ከሙታን ተነስቱዋልየሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ አበሰሩ። ይህ የመጀመሪያክርስቶስ ከሙታን ተንስቱዋል” የሚለው የምስራች ቃል የእግዚኣብሔር መልእክተኞች ከሆኑት መላእክት የተነገረ የምስራች ቃል እንደ ሆነ ወንጌላዊያኑ በዋቢነት ይጠቅሳሉ። በእዚህ ረገድ መላእክቱ በእዚህ ሁኔታ ውስጥ መሳተፋቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ ትጉም የሚሰጠው ሲሆን የእግዚኣብሔር ቃል የነበረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጸነሰበት ወቅት የምስራችሁን ቃል ያመጣው መልኣኩ ገብረኤል እንደ ነበረ ሁሉ አሁንም  የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ ለማብሰር የሰዎች ምስክርነት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ የተነሳ በቀዳሚነት ያበሰረው የእግዚኣብሔር መላእክ ነው።   

አንድ በጣም አስደንጋጭ ወይም በጣም አስደናቂ የሆነ አንድ ነገር ለመግለጽ አንድ ለየት ያለ የበላይ አካል የምያስፈልግ ሲሆን ይህም የሚሆንበት ምክንያት ማንም ሰው ለመናገር የሚደፍረው ጉዳይ ባለመሆኑ የተነሳ ነው። ከእዚህም የመጀመሪያው የመላኣኩ ምስክርነት በኃላ ደግሞበእውነት ጌታ ከሙታን ተነስቱዋል ለስምዖንም ታይቱዋል” (ሉቃስ 24:34) የሚለው የደቀ- መዛሙርቱ ምስክርነት ደግሞ በተደጋጋሚነት ይቀጥላል። እንዴት ደስ የሚል የምስራች ዜና ነው። ሁላችንም አሁን በአንድ ድምጽበእውነት ጌታ ከሙታን ተነስቱዋልለማለት እንችላለን። ይህበእውነት ጌታ ከሙታን ተነስቱዋልየሚለው የመጀመሪያው  የምስራች ቃል አንድ የበላይ የሆነ ኃይል እና  የሰውን ጥበብ ይጠይቃል።

የዛሬው ቀን በዓል ከቤተሰብ ጋር በአንድ ላይ በመሰባሰብ የሚከበር በዓል ነው። ይህም የቤተሰብ ቀን ነው ማለት ነው። የፋሲካን በዓል ካከበርን በኃላ ከወዳጆቻችንና ከጓደኞቻችን ጋር መሰባሰብ  እንደሚያስፈልገን ይሰማናል። የወንድማማችነት መንፈስ የክርስቶስ ፋሲካ ፍሬ ውጤት በመሆኑ፣ በሞቱና በትንሳኤው፣ ሰዎችን ከእግዚአብሔር እና እንዲሁም እርስ በእርሳቸው እንዲለያዩ አድርጎ የነበረው ኃጢኣት ክርስቶስ ድል በማድረጉ የተነሳ ነው። ኃጢኣት ሁልጊዜም ቢሆን የሚከፋፍለን እና የጠላትነት መነፈስን እንደ ሚያመጣ እናውቃለን። ኢየሱስ የሰው ልጆችን የከፋፈለውን የጥል ግድግዳ በማፈረሰ እና ሰላምን በድጋሚ በማረጋገጥ፣ አዲስ የሆነ የወንድማማችነት መንፈስ እንዲረጋገጥ አድርጉዋል። በጥንት ጊዜ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች የነበራቸውን ዓይነት ወንድማማችነት እኛ ባልንበት በአሁኑ ዘመን ይህንን የወንድማማችነት መነፍስ በድጋሚ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ፈጽሞ የማይለያይ፣ ሁልጊዜም አንድነትን ለሚሰጠን ለክርስቶስ ስፍራ መስጠት ይኖርብናል። እውነተኛ ሕብረት እና ማህበራዊ ፍትህ ያለ ወንድማማችነት መነፈስ በፍጹም ሊረጋገጡ አይችሉም።  ያለ ወንድማማችነት መነፍስ አንድ የቤተ ክርስቲያን ወይም የሲቪል ማሕበረሰብ ለመመስረት አይቻልም፣ ምን አልባትም እንዲሁ ለእራስቸው ጥቅም ሲሉ ብቻ የተሰበሰቡ የሰዎች ስብስብ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው። ነገር ግን የወንድማማችነት መንፈስ የሚሰጠን ኢየሱስ ራሱ ነው።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳሄ አንድ አዲስ ነገር በዓለም እንዲከሰት አድርጉዋል፣ ይህም የውይይት እና የጓደኝነት መነፈስ ሲሆን ይህም ለክርስቲያኖች ከፍተኛ የሆነ ኃላፊነት ነው። በእርግጥ ጌታ ራሱእርስ በርሳችሁ ብት ዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ (ዩሐንስ 13:35) በማለት ተናግርዋል። ለዚህ ነው እንጊዲህ ለራሳችን በግል፣ በቡድን መለያየት የለብንም፣ ነገር ግን ለወንድሞቻችን በተለይም በጣም ደካማ፣ በጣም የተገፉትን የማኅበርሰብ ክፍሎችን እና ስደተኞችን ለመንከባከብ ሁሉንም ሰዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ነገሮችን እንድናደርግ ተጠርተናል። ዘላቂነት ያለው ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው የወንድማማችነት መነፈስ በመፍጠር ብቻ ሲሆን ፣ይህም ድኽነትን፣ ውጥረቶችን እና ጦርነቶችን፣ ሙስናን፣ በጠቃላይ ወንጀሎችን ለማስወገድ የሚቻለው የወንድማማችነት መንፈስ በመፍጠር ብቻ ነው።በእውነት ከሙታን ተነስቱዋልየሚለው የመልኣኩ ድምጽ በወድማማችነት መነፈስ እንድንኖር እና የመወያየት መንፈስ እንድናዳብር፣ መልካም የሆኑ ግንኙነቶችን ለመፍጠር እንድንችል፣ ለማኅበራዊ ፍትህ ያለንን ጭንቀት እንድናስወግድ ይርዳን።

በእዚህ በፋሲካ ወቅትየሰማይ ንግሥትእያልን የምንጠራርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በጸሎቷ እንድትረዳን እየተማጸንን በእዚህ የፋሲካ ወቅት እያንጸባርቅነው የምንገኘውን የወንድማማችነት እና የአንድነት መነፈስ የእኛ የክርስቲያኖች አንዱ የሕይወት የአኗኗር ዘይቤ ሆኖ እንዲቀጥል እና ከሰዎች ጋር የምናደርገውን ግንኙነት ይበልጥ እንድናሻሽል በአማላጅነቱዋ ትርዳን።








All the contents on this site are copyrighted ©.