2018-03-26 15:56:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “በአሁኑ ወቅት ዓለም ያጣውን የክርስቶስን ደስታ በእልልታ አስተጋቡ!”


የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 16/2010 ዓ.ም. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት የሆሳዕና በዓል በታላቅ መነፍሳዊነት መከበሩ ይታወሳል። ይህ የሆሳህና በዓል በተመሳስይ መልኩ በታላቅ መንፈሳዊነት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከ50ሺ በላይ ወጣቶች በሚበዙበት ምዕመናን በተገኙበት እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ተገልጹዋል። በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በርከት ያሉ ምዕመናን በተለይም ደግሞ  እምነት፣ ወጣቶች እና በጥሪ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ በሚል መሪ ቃል ወጣቶች ላይ ትኩረቱን ያደርገ እና በመጪው ጥቅምት 2011 ዓ.ም. ለሚካሄደው የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት 15ኛ አጠቃላይ መደበኛ ጉባሄ ቅድመ ዝግጅት ይሆን ዘንድ ከመጋቢት 10-15/2010 ዓ.ም. ድረስ በሮም ሲካሄድ በነበረው ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣጡ በርካታ ወጣቶች በእዚሁ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ መሳተፋቸውም ተገልጹዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ለማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ከማርቆስ ወንጌል 14 ላይ ተወስዶ በተነበበው ኢየሱስ የሚጠብቀውን የመከራ ጽዋ ለመጠጣት በታላቅ ክብር ወደ እየሩሳሌም መግባቱን በሚገልጸው የወንጌል ክፍል ላይ ተምስርተው አድርገውት የነበረውን የወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። የዛሬው ስረዓተ አምልኮ በደስታ እና በምስጋና ዝማሬ ኢየሱስን ከሚያመስግኑ ሰዎች ጋር እንድንሆን ይጋብዘናል፣ የሚጣፍጥ ደስታ እና ነገር ግን የኢየሱስን ሕማማት የሚገልጸው ታሪክ ከተነበበ በኃላ ግን መራራ የሆነ ጣዕም እንዲሰማን ያደርጋል። በእዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ የደስታ እና የስቃይ ታሪክ የሚገናኙበት ታሪክ ይመስላል፣ እንደ አንድ ደቀ-መዝሙር በእለታዊ ኑሮዋችን የሚገጥሙንን  ስሕተቶች እና ስኬቶች የሚያሳይ ታሪክ ሲሆን ምክንያቱም ስሜትን ለመቆጣጠር የሚረዳ እና ዛሬ በእኛም በእዚህ ዘመን በምንገኝ ሰዎች ዘንድ የተለመዱ ግጭቶችን፣ እና ለመውደድ ያለን ብቃት፣ ለመጥላት ያለንን ፍላጎት በመገምገም ለመልካም እሴቶች መስዋዕት ለመሆን እና በተጨማሪም ስይመቸን ሲቀርከደሙ ነጻ ለመሆን እጆቻችንን መታጠብ፣ በተጨማሪም የመክዳት እና ችላ ማለት የመሳሰሉ ስሜቶች የሚገኙበት ነው። በእዚሁ የኢየሱስን የመጨረሻ የእዚህ ምድር ቆይታን በሚያሳየው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እንደ ተገለጸው በኢየሱስ አማካይነት የታየው ከፍተኛ ደስታ ለሌልቾ ግን ጥሩ የሆነ ስሜት አንዳይሰማቸው ያደርገ እና ያበሳጫቸው ክስተት ነበር።

ኢየሱስ በእራሱ ሕዝብ ታጅቦ ወደ ኢየሩሳሌም በሚገባበት ወቅት በእልልታ እና በዝማሬ ተከቦ ነበር። ይህንን እልልታ እና ዝማሬ ኃጢኣታቸው ይቅር የተባለላቸው ሰዎች፣ ከለምጽ የተፈወሱ ሰዎች፣ ወይም ደግሞ ጠፎቶ ከተገኙ በጎች መካከል የነበሩ ሰዎች የእነዚህ እና እነዚህን የመሳሰሉ ሰዎች በአንድነት የሚያስመት ድምጽ ሊሆን እንደ ሚችል እናስብ። ሰዎች ሁሉ የሚያውቁት ኃጢያተኛ ሰው ወይም አንድ ንጹህ ያልሆነ ሰው ከእነዚህ መካከል ሊገኝ ይችል ይሆናል፣ምን አልባትም ከሰዎች ሁሉ ተገለው በየመንገዱ የሚኖሩ ሰዎች ዝማሬ እና ጩኸት ሊሆን ይችል ይሆናል። ከስቃያቸው እና ከመከራቸው በእርሱ ርኅራኄ የተፈወሱ  እና እርሱን ተከትለው የወጡ የወንዶች እና የሴቶች ድምጽ ሊሆን ይችላል። ይህ ቀጣይነት ባለው መልኩ በወቅቱ በተገለሉ ሰዎች እና በኢየሱስ አማካይነት ሕይወታቸው የተቀየረ ሰዎች አማካይነት የተደረገው እልልታ እና ዝማሬበጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!በማለት አስተግብቶ ነበር። ሰብዐዊ መብታቸውን መልሰው እንዲጎናጸፉ እና ተስፋ እንዲኖራቸው ላደረጋቸው ሰው እንዴት ነው ታዲያ የማይዝምሩት? ይህም የኃጢኣታቸውን ይቅርታ በማግኘታቸው የተነሳ በእርሱ ያመኑ እና ተስፋ ይደርጉ ሰዎች የደስታ ድምጽ ነው። እነዚህ ሰዎች ይጮኸሉ። ይደሰታሉ። ይህም ታላቅ ደስታን ፈጥሮባቸዋል።

ይህ የደስታ ስሜት ራሳቸውን እንደ ጻድቅ የሚቆጥሩ እና ለህግ እና ለሥርዓታዊ ሕጎችታማኝለሚመስሉ ሰዎች ግን የማይመች፣ ግራ የሚያጋባ እና አጸያፊ የሆነ ተግባር ነበር። በህመም፣ በመከራ እና በስቃይ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ስሜታቸው ገንፍሎ መውጣቱን የሚያሳይ ደስታ ነው። ነገር ግን ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎችቹን ስነ-ስረዓት የሌላቸው ሰዎች አድርገው ይቆጥሩዋቸው ነበር። የማስታወስ ችሎታቸውን አጥተው ለነበሩ ሰዎች እና ብዙ እድሎች አምልጦዋቸው ለነበሩ ሰዎች ሁሉ የማይረሳ ታላቅ ደስታ ነው። ራሳቸውን ለማመቻቸት እና ለማረጋጋት ለሚሞክሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ምሕረት እና ደስታ ምን ያህል ለመረዳት ከባድ ነው! በራሳቸው ኃይል ለሚታመኑ እና ከሌሎቹ እንደሚበልጡ ለሚያምኑ ለእነዚህ ሰዎች ደስታን ማካፈል ምን ያህል ከባድ ነው።

እናም የእዚህ ዓይነት ፍርሃት ከያዛቸው ሰዎች ነው ይህስቀለው ስቀለውየሚለው ጩኸት የመነጨው በእዚህ ምክንያት ነው። ይህም ጩኸት ቀጣይ የሆነ ውስጣዊ ጩኼት አልነበረም፣ ነገር ግን በሐሰት የተመሰቃቀል፣ በሐሰት ምስክሮች ምክንያት ተነሳስተው የተሰበሰቡ ሰዎች ጊዜያዊ ጩኸት ነበረ እንጂ። በሂደቱ ከነበረው እውነታ የተወዳዳሪነት መንፈስ ተፈጥሮ፣ የውድድር ጩኸት ምንጭ ሆነ። እውነታውን ለመደበቅ እና ለራሳቸው ጥቅም የሚመች ሁኔታ በመፍጠር እና ይህንን ግባቸውን ለማሳካት የሚሆናቸውን መሰሪ የሆኑ ሐሳቦችን በመፍጠር ሌሎች ሰዎች "የመያዝ" ችግር ምንም አልገጠማቸውም ነበር። ይህም ሐሰተኛ የሆነ ዘገባ ነው። የሌሎችን ጩኸት ለመጫን እና የራሳቸው የተንኮል ድምጽ አጉልቶ እንዲሰማ ለማድረግ የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች ሁሉ ማለፍ የሚችሉ ምንም ነገር የማያግዳቸው ሰዎች ናቸው። ይህ ጩኸት የመነጨው እውነታውን በመሸፋፈን እና ይህንንም ያደርጉት የኢየሱስ ግጽታን በማጠልሸት እንዲጠናቀቅ በሚያስችላቸው ሁኔታ በማቀድ ኢየሱስን እንደ አንድክፉየሆነ ሰው አድርጎ በመሳል ነበር። ይህም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን በማዋረድ አቋማቸውን ለማጽናት የሚፈልጉት ሰዎች ድምጽ ነው። ከእነዚህራሳችን ብቃት አለን” ከሚሉ፣ በኩራት የተሞሉ እና በትዕቢት የተወጠሩ ሰዎች በዶለቱት ሴራ አማክይነት ያለምንም ችግር ይህስቀለው ስቀለውየሚል ድምጽ መጣ።

እናም በእዚህ ምክንያት መጨረሻ የሕዝቡ የደስታ ድምጽ ፀጥ ብሏል፣ ተስፋቸው ጨልሙዋል፣ ሕልማቸው ከንቱ ሆኑዋል፣ ደስታቸው በኖ ጠፍቱዋል፣ በመጨረሻም ልባቸው እንዲታወር በማድረግ ደግነታቸው ወይም ለጋስነታቸው ቀዘቀዘ። የሕዝቡን ሕበረት እንዲቀዘቀዝ የሚያደርግ፣ ሐሳባቸውን የሚያጨልም፣ ለሚያዩት ነገር ምንም ደንታ እንዳይኖራቸው የማያደርግራስህን ብቻ አድንየሚል ጩኸት. . .ርኅራኄን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የፈለገ ጩኸትይህ ጩኸት የመነጨው ራሱን እንደ ደካማ አድርጎ ካቀረበው ከእግዚኣብሔር ርኅራኄ ነው።

እነዚህን የሚጮኹትን ድምጾች ለማስታገስ እጅግ ጥሩ የሆነው መድኃኒት ወደ ክርስቶስ መስቀል መመልከት እና እርሱ በመጨረሻው ሰዓት ከጮኸው ጩኸት ጋር ማመሳከር ያስፈልጋል። ኢየሱስ የሞተው ለእኛ ለእያንዳንዳችን ያለውን ፍቅር ጩኾ ከገለጸ በኃላ ነው፣ ለወጣቶች፣ ለአረጋዊያን፣ ለቅዱስናን እና ለኃጢኣተኞች በእርሱ ዘመን ለነበሩ ሰዎች እና በእኛም ዘመን ላሉ ሰዎች ያለውን ፍቅር በመግለጽ ነው። በእርሱ መስቀል ሁላችን በመዳናችን የተነሳ ይህንን በወንጌል የሚገኘውን ደስታ ማንም ሰው ልያመክነው አይችልም፣ ምክንያቱም ሁላችንም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም እንኳን ከእግዚኣብሔር መልኮታዊ ምሕረት እይታ ውጪ ልንሆን በፍጹም አንችልም። መስቀሉን መመልከት ማለት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ምርጫዎቻችንን እና ድርጊቶቻችንን በመመልከት ራሳችንን እንድንጠይቅ ማድረግ ማለት ነው። በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በመጥፋት ላይ ያሉትን ሰዎች ወይም በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለማዳን ያለንን ስሜት ማነቃቃት ማለት ነው።

ወንድሞች እና እህቶች ልባችን ምን እያሰበ ይገኛል? ኢየሱስ የልባችን ውስጥ ደስታና ውዳሴ ምንጭ መሆኑ ይቀጥላል ወይስ ለኃጢአተኞች፣ ለተናቁ እና ለተረሱ ሰዎች ቅድሚያ መስጠታችን ያሳፍረናል?

እናንተ ወጣቶች ኢየሱስ በእናንተ ውስጥ የሚያነሳሳው ደስታ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ይረብሻችኃል፣ ምቾት ይነሳችኃል? ምክንያቱም ደስተኛ የሆነ አንድ ወጣትን መበጥበጥ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ነው። ደስተኛ የሆነ አንድ ወጣትን መጫን ወይም መበጥበጥ በጣም አስቸጋሪ ነው።

በእዚህ ረገድ እናንተ በሉቃስ ወንጌል 1939-40 ላይ እንደ ተጻፈውበሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያንም ኢየሱስን፣መምህር ሆይ፤ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው እንጂአሉት።እርሱም፣ “እላችኋለሁ፤ እነርሱ ዝም ቢሉ፣ ድንጋዮች ይጮኻሉአላቸውየሚለውን ድምጽ የመወከል አለባችሁ።

ወጣቶችን ዝም ማሰኘት የሚለው አመለካከት ከብዙ ጊዜ ጀምሮ የነበረ ፈተና ነው። በእዚህም ረገድ ፈሪሳዊያን ኢየሱስን በወቅቱ የነበሩ ሰዎችን ዝም እንዲያስኝ እና እንዲያረጋጋቸው ጠይቀውት ነበር።

ወጣቶች እንዳይጮኹ ለማድረግ እነሱን ለማደንዘዝ እና እንዲተኙ ለማድረግ የሚረዱ ብዙ ዓይነት መነገዶች አሉ። ወጣቶች ጥያቄ እንዳያነሱ እና ለውይይት መንገድ እንዳይከፍቱ ዝም ለማሰኘት እና እንዳይታዩ ለማድረግ የሚያስችሉ ብዙ ዓይነት መነገዶች አሉ። በአጠቃላይዝም በላችሁ ኑሩ!የሚል ድምጽ በከፍተኛ ሁኔታ ይታያል። ወጣቶች ተሳታፊ እንዳይሆኑ ለማድረግ የሚያስችሉ ብዙ መንገዶች አሉ። ተረጋግተው እንዳይኖሩ በማድረግ ሕላማቸውን በመጨለም፣ ምስኪኖች እንዲሆኑ እና በሐዘን ውስጥ እንዲወድቁ . . .ማድርገ የመሳሰሉ በዙ መንገዶች አሉ። በእዚህ የሆሳዕና በዓል በሚከበርበት ወቅት ኢየሱስ ቀደም ሲል ለፈሪሳዊያን፣ ዛሬ ደግሞ ለእኛ የተናግረውን እነዚህ እናኳን ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉየሚለውን ድምጽ በድጋሚ መስማት መልካም ነገር ነው።

የተወደዳችሁ ወጣቶች በመጪው ዐርብስቀለው ስቀለውየሚለውን ጩኼት የማስተጋባት ፈተና ውስጥ እንዳትገቡ አሁን በዛሬው የሆሳዕና እለተ ስንበት ላይ የደስታ ድምጻችሁን ማሰማት ወይም ካለማሰማት መምረጥ የእናነት ፈንታ ነው፣ ዝም ብሎ የመቀመጥ እና ያለመቀመጥ ምርጫ የእናንተ ነው። እኛ ትላልቆች እና አረጋዊያን የምንባል ብዙን ጊዜ በሙስና ውስጥ የተዘፈቅን ሰዎች ዝም ብንል፣ ዓለም ዝም ቢል እና ደስታውን ቢያጣ እንኳን እስቲ ልጠይቃችሁ እናንተ ግን ትጮኻላችሁ አይደል”? (በወቅቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የነበሩ ሰዎች በተለይም ወጣቶች አዎን በማለት ይመልሳሉ!)

እባካችሁን ድንጋዮች ስይጮኹ በፊ ከአሁኑ ለመጮኽ ወስኑ!!

 








All the contents on this site are copyrighted ©.