2018-03-14 14:15:00

"አባታችን ሆይ! የሚለው ጸሎት ለእግዚኣብሔር ልጆች ብቻ የተሰጠ ጸሎት ነው" ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች  በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በጥር 7/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ በተከታታይ አድርገው የነበረ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን፣ ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ዙሪያ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ በእዚሁ የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትርጉም ያቸውን ክፍሎች በማንሳት አስተምህሮ ማድረጋቸውን ከቅድም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

የእዚህን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእዚህም መሰረት ቀደም ባሉት ጊዜያት በመስዋዕተ ቅዳሴ የመግቢያ ስነ-ስረዓት ላይ ስላለው የኑዛዜ ጸሎት፣ በመቀጠልም አሁንም በመስዋዕተ ቅዳሴ የመግቢያ ስነ-ስረዓት ላይ ስላለው የመግቢያ ጸሎት አንስተው ሰፊ የሆነ ትንታኔ መስጠታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእዚያም በመቀተል ባደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ደግሞ ከእዚሁ የመግቢያ ጸሎት በመቀጠል የሚገኘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባትን በተመለከተ ሰፊ አስተምህሮ አድርገው እንደ ነበረ መዘገባችን ይታወሳል።

በእዚህም መሰረት የእግዚኣብሔር ቃል በሕይወታችን የሚያደርገው ጉዞ በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ቃል ከጆሮዋችን ወደ ልባችን ከልባችን ወደ እጃችን በመጓዝ መልካም ተግባራትን እንድናከናውን ይረዳናል ማለታቸውምን መዘገባችን ይታወሳል።  በጥር 30/2010 ዓ.ም. ባደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በእዚሁ በስረዓተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ዙሪያ እያደርጉት የሚገኘውን የተምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ሰለምነበቡት የእግዚኣብሔር ቃላት እና በመቀጠልም በእዚህ በእግዚኣብሔር ቃል ላይ መስረቱን ስላደርገው ስብከት በማንሳት ጥልቅ የሆነ አስተምህሮ አድርገው እንደ ነበረ መዘገባችን ይታወሳል።  በየካቲት 7/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ያደረጉት አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል የነበረ ሲሆን በእዚህም መስረት በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ከሚነበቡት የምጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት እና በእነዚህ ምንባባት ላይ ተመርኩዘው ከሚሰጠው ስብከት በመቀጠል ባለው የቅዱስ ቁርባን መስዋዕት የማቅረብ ስነስረዓት ዙሪያ ጠለቅ ያለ አስተምህሮ ማድረጋቸውን መገለጻችን ይታወሳል።

በየካቲት 14/2010 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ይህንን የዐብይ ጾም ወቅት አስመልክቶ በእየአመቱ እንደ ምያደርጉት አመታዊ ሱባሄ ለማድረግ በሮም ከተማ አቅራቢይ ወደ ሚገኘው አራቺያ ወደ ሚባልበት ስፍራ በመሄዳቸው የተነሳ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አለማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በየካቲ 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመስዋዕተ ቁርባን ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል። ባልፈው ሳምንት በየካቲት 28/2010 ዓ.ም. ያደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ጀምረውት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል የነበረ ሲሆን በመስዋዕተ ቁርባን ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ አስትምህሮ ማድረጋቸው ይታወቃል።

በዛሬው ቀን ማለትም በመጋቢት 05/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም በመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዛሬው እለት አስተምህሮዋቸው ከመስዋዕተ ቁርባን ጸሎት ቀጥሎ በሚገኘው “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት እና ከእዚያም “ቅዱስ ቁራብን የመቁረስ ስነ-ስረዓት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 05/2010 ዓ.ም. ያደርጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“እነርሱ ግን፣ “ምሽት እየተቃረበ፣ ቀኑም እየመሸ ስለ ሆነ ከእኛ ጋር እደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ ስለዚህ ከእነርሱ ጋር ለማደር ገባ።አብሮአቸውም በማእድ በተቀመጠ ጊዜ እንጀራውን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ሰጣቸው። በዚህ ጊዜ ዐይናቸው ተከፈተ፤ ዐወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ” (የሉቃስ ወንጌል 24:29-31)

 

የተከበራቸው ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አርፈዳችሁ።

በመጨረሻው ራት ላይ ኢየሱስ እንጀራውን እና የወይን ጠጅ አንስቶ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረበ "እንጀራውን እንደቆረሰ" እናውቃለን። ይህም ድርጊት በተመሳሳይ መልኩ በመስዋዕተ ቅዳሴ ውስጥ ኢየሱስ ካስተማረን ጸሎት በመቀጠል በሚገኘው “እንጀራውን የመቁረስ ስነ-ስረዓት” ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ይፈጸማል። በእዚህም መልኩ ከምዕመናኑ ጋር “አባታችን ሆይ” የሚለው ጸሎት ከተጸለየ ወይም ከተዘመር በኃላ ቅዱስ ቁርባንን የመካፈል ስነ-ስረዓት ይጀምራል። ይህ ጸሎት ከብዙ የክርስቲያን ጸሎቶች መካከል አንዱ ሳይሆን ነገር ግን  ለእግዚአብሔር ልጆች ብቻ የተሰጠ ጸሎት ነው። በእርግጥ በተጠመቅንበት ቀን "አባታችን" በክርስቶስ ኢየሱስ ጥምቀት ወቅት ተከስተው የነበሩትን ተመሳሳይ ስሜቶች በመላክ በውስጣችን አስጨብጦናል። ጌታችን እና አምላካችን ባስተማረን እና ባዘዘን መልኩ “አባታችን ሆይ” በማለት እግዚኣብሔርን እንጠራለን ምክንያቱም እኛም እንደ ልጆቹ በድጋሚ በውኃ እና በመንፈስ ቅዱስ ስለተወልድን ነው። ይህም ለማንም በተመሳሳይ መልኩ የተሰጠ መብት አይደለም። ይህም “እንደ ገና የፍርሀት ባሪያ የሚያደርጋችሁ መንፈስ ሳይሆን፣አባ አባትብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋልና” (ሮሜ. 8፡15)። እስቲ ከእዚህ ኢየሱስ ካስተማረን “አባታችን ሆይ!” ከሚለው ጸሎት በተሻለ መልኩ ወደ ቅዱስ ቁርባን ምስጢር ሊያደርሰን እና ከኢየሱስ ጋር ሊያገናኘን የሚችል የተሻለ ጸሎት ምን አለ? ይህ አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ከመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ውጭ በጥዋት እና በማታ ጸሎት ውስጥ ይጸለያል። በዚህ መልኩ ሲጸለይ የእግዚኣብሔር ልጆች መሆናችንን እና ከባልንጀሮቻችን ጋር የወንድማማችነትን ስሜት በሚያንጸባርቅ መልኩ በማደርግ ቀናችንን የክርስትና ቅርፅን በማላበስ አስተዋፅኦ ያደርጋል

በእዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረን ጸሎት ውስጥ “የእለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን” በማለት ለየት ባለ ሁኔታ በቅዱስ ቁርባን መልክ የሚሰጠውን እንጀራ በመጥቀስ እኛ የእግዚኣብሔር ልጆች እንደምሆናችን መጠን ለመኖር የሚያስፈልግን የሕይወት እንጀራ እንደ ሆነ እንገልጻለን። “በደላችንን ይቅር በልልን” በማለት የተማጽኖ ጸሎት በማቅረብ በእዚህም መልኩ እኛ የእግዚኣብሔርን ምሕረት ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንን በመግለጽ እኛም የበደሉንን ሰዎች ይቅር ለማለት ዝግጁዎች እንደ ሆንን እናሳያለን ማለት ነው። በእዚህም መልኩ "አባታችን ሆይ!" በማለት ልባችንን ለእግዚአብሔር በመክፈት ለወንድማማችነት ፍቅር ያዘጋጀናል። በመጨረሻም ከእግዚኣብሔር እና እንዲሁም ከወንድም እህቶቻችን የሚለያየንን ክፉ ነገር እንዲያስወግድልን “ከክፉ ሁሉ ሰውረን” በማለት እግዚኣብሔርን በድጋሚ እንጠይቃለን። እነዚህም ለቅዱስ ቁርባን እኛን ለማዘጋጀት የሚያስችሉን ለእኛ በጣም ጥሩ ልመናዎች መሆናቸውን በሚገባ እንገነዘባለን።

“አባታችን ሆይ!” የሚለው ጸሎት ከተጠናቀቀ በኃላ ካህኑ “ጌታ ሆይ ከክፉ ነገሮች ሁሉ አድነን በዘመናችን ሰላምን ስጠን” በማለት የተማጽኖ ጸሎት ምዕመኑን ሁሉ በመወከል ያቀርባል። ከዚያም ሰላምታ የመሰጣጠት ሥነ-ሥርዓት ይካሄዳል፣ በእዚህም በቀዳሚነት ሰላም ሰጪ የሆነው ክርስቶስ ብቻ እንደ ሆነ ይገለጻል፣ ይህ ክርስቶስ የሚሰጠን ሰላም ዓለም እንደ ሚሰጠን ዓይነት ሰላም እንዳልሆነ - ቤተ ክርስቲያን በኅብረት እና በሰላም እንድታድግ የሚያደርግ ሰላም እንደ ሆነ፣ ይህም በእግዚኣብሔር በጎ ፈቃድ የሚሰጥ የሰላም ዓይነት እንደ ሆነ በሚገልጽ መልኩ፣ ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ ሰላምታ የመለዋወጥ ስነ-ስረዓት በምዕመኑ ዘንድ ይደርጋል፣ በእዚህም “የቤተ ክርስቲያን ኅብረት እና የጋራ ፍቅርን ከገለጽን በኃላ ወደ ቅዱስ ቁርባን ምስጢር እንቀርባለን። በላቲን የስርዐተ-አምልኮ ደንብ መሰረት “ይህ ሰላምታ የመለዋወጥ ስነ-ስረዓት ከሚስጢረ ቅዱስ ቁርባን በፊት የሚደረግ ሲሆን በእዚህም በሰላም ወደ ቅዱስ ቁርባን ምስጢር እናመራለን። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ “የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?” (1 ቆሮንጦስ 10:16-17, 11,29) በማለት ስለሚገስጸን  ወደ ጌታ እራት ከመቅረባችን በፊት እርስ በእርሳችን በወንድማማችነት ፍቅር ሰላም መፍጠር ይገባናል። የክርስቶስ ሰላም የወንድማማችነት ፍቅር በማያሳይ እና በደልን ከፈጸመ በኃላ ይቅርታን በማያደርግ ልብ ውስጥ የኢየሱስ ሰላም በፍጹም ስር ሊሰድ አይችልም።

ሰላም የመባባል ስነ-ስረዓት ከጥንት ከሐዋሪያት ዘመን አንስቶ የቅዱስ ቁርባን እንጄራ ከመቆረሱ በፊት ይህንን ምስጢር ለማክበር የሚደረግ የመገለጫ ምልክት ነው። የጌታ እራት የሚበላበት ምክንያት ጌታ በሕማማቱ ዋዜማ ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር ከበላው እራት ጋር ስለሚዛመድ እና ከትንሳሄውም በኃላ ደቀ-መዛሙርቱ የሚያውቁት በእዚሁ መልኩ እንዲሆን በማሰብ ነው። በእዚህም መልኩ ወደ ሄማዉስ ይሄዱ የነበሩትን ደቀ-መዛሙርትን ማስታወስ እንችላለን፣ በመንገድ ላይ ከሙታን ከተነሳው ከኢየሱስ ጋር እንዴት እንደ ተገናኙ በገለጹበት ወቅት “እንጀራን አንስቶ በቆረሰበት ወቅት” (ሉቃስ 24:30-31.35) እንደ ተጠቀሰው በእዚያን ወቅት እንዳወቁት መግለጻቸው ይታወቃል።

ይህ በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት እንጄራን የመቁረስ ስነ-ስረዓት “የእግዚኣብሔር በግ” በሚለው መጥምቁ ዮሐንስ በማግሥቱ፣ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶእነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዩሐንስ 1:29) ከሚለው የተወደ መማጸኛ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ በግ የሚለው ቃል አዳኝ የሚለውን ቃል ያመለክታል (አስተር 12:1-14. ኢስያስ 53:7, 1ጴጥሮስ 1:19, ራዕይ 7:14)። በቅዱስ ቁርባን ለዓለም ሕይወትን ለመስጠት በተቆረሰው እንጀራ አማካይነት ምዕመኑ ይህ እንጄራ የእግዚኣብሔር እውነተኛ በግ የክርስቶስ አዳኙ እንደ ሆነ በማመን “ምሕረትህን ስጠን ሰላምህን ስጠን በማለት የተማጽኖ ጸሎት ይቀርባል።

“ምሕረትህን አሳየን” “ሰላምህን ስጠን” የሚሉት ሁለቱ የመመጸኛ  ጸሎቶች “አባታችን ሆይ” ከሚለው ጸሎት አንስቶ ቅዱስ ቅርባን የመቁረስ ስነ-ስረዓት መክከል የሚገኙ የመማጸኛ ጸሎቶች ሲሆኑ እነርሱም ከወንድሞቻችን እና ከእህቶቻችን ጋር ኅብረት እና መግባባት መፍጠር ወደ ሚያስችለን ምንጭ ወደ ሆነው የቅዱስ ቁርባን ምስጢር እንድንቀርብ ወይም እንድንሳተፍ ያደርገናል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.