2018-02-22 11:35:00

“የተጠማም ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግም ሁሉ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ”


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በየወቅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ሱባሄ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ከባለፈው እሁድ ምሽት ማለትም ከየካቲት 11/2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 16/2010 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሱባሄ ለማድረግ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አራቺያ በሚባል ስፍራ በሚገኘው “ ዲቪኒ ማዬስትሮ” በሚባል የሱባሄ ምስጫ ማዕከል በመገኘት ስቡባሄ እያደርጉ እንደ ሆነ ቀድም ሲል መግለጻችን ያትወሳል።

የእዚህ ሱባሄ መሪ የሆኑት በፖርቹጋል ዋና ከተማ በሌዝቦን የሚገኘው የካቶሊክ ዩንቬርሲቲ ምክትል ድይሬክተር የሆኑ፣ በነገረ መልኮት አስተምህሮ ጠበት የሆኑ፣ ገጣሚ እና ደረሲ አባ ጆዜ ቶሌንቲኖ በሚባሉ ካህን እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እርሳቸው በእዚህ ሱባሄ ላይ ለተሳተፉት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እና የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ያደርጉትን የመጀመሪያ አስተንትኖ እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን።

በዩሐንስ ርዕይ ውስጥ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የተጠቀሰው የኢየሱስ ቃልየተጠማም ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግም ሁሉ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድየሚለው ነው። (ዩሐንስ ራዕይ 2217) በእዚህም መሰረት የእግዚኣብሔር ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሰጠውንየተትረፈረፈ እና ነጻ የሕይወት ስጦታ እንደ ሚሰጥ እና ለእዚህም ለእግዚኣብሔር ልጅ ጥሪ ዛሬ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል። ኢየሱስ "ያልተሟላን እና ገና እያደግን መሆናችንን በሚገባ ስለሚረዳ እርሱ እኛን ወደ ኃዋላ ስበው የሚያቆሙንን ብዙ ዓይነት መሰናክሎች እንዳሉብን እና እንድንዘገይ የሚያደርጉን ብዙ ፈተናዎች እንደ ሚገጥሙን ስለሚረዳ ይህንን ጥማችንን ለመቁረጥ ቃል ይገባልናል።

እኛ "ለምንጩ በጣም ቅርብ የሆንን ብንሆንም ነገር ግን ይህንን ምንጭ ለማግኘት በጣም ርቀን እንሄዳለን። በምኞት እና በጥማት መካከል የሚገኝ  ነገር አለ፣ ይሄውም መስዋዕት እና ርቀት፣ የምናደርገው ጉዞ እና ንቃት የሚባሉ ነገሮች ናቸው ስለእዚህም አሁን ራሳችንን መጠየቅ የሚገባን ጥያቄ መሆን የሚገባው እኛ ለእግዚኣብሔርን ፍላጎት አለን ወይ? ጥማታችንን በቅጡ ለይተን እናውቃለን ወይ? እነዚህን ጥማቶቻችንን በዝርዝር ለይተን ለማወቅ ጊዜ አለን ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች በማንሳት ለራሳችን ምላሽ መስጠት ይኖርብናል። ጥማት አካላዊ የሆነ ፍላጎታችን ነው፣ ጥማት እኛ ውስን የሆንን ሰዎች መሆናችንን እንድንረዳ የሚያደርገን ነገር ነው፣ ጥማት በጣም ወደ ከፋ ነገር ውስጥ እንዳንገባ ምልክት የሚሰጠን ነው። ጥማችን እስትንፋሳችን እንዲቆራረጥ ያደርጋል፣ ይፈትነናል ያሟጥጠናልም። እኛ ለመዋጋት ያለንን አቅም ያሳጣናል፣ ተገለን እንድንቆይ ያስገድደናል። ጣማት በጣም ውስን እንድንሆን ያደርገናል። ራሳችንን ከጥማችን  ማላቀቅ ቀላል እንዳልሆነ እንገነዘባለን "ረሃብ እና ጥማትእነዚህ ነገሮች "ዘላለማዊ ባዶነትየሚገለጽባቸው ምልክቶች ናቸው። ከመጠን በላይ በሆነ ጭንቀት ውስጥ በማስገባት የሰው ልጆች ስር እንዳይኖራቸው ያደርጋል፣ በቤታችንም ውስጥ ከሌሎች ጋር ግንኙነት እንዳናድርግ እንቅፋት ይሆናል፣ በባዶነታችን ውስጥ እንድንጠፋ ያደርገናል፣ መንገዳችንን በሚገባ እንዳንጓዝ ያደርገናል።

ይህም በዛሬው ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይ የሰው ልጆች ጥማት ነው። በሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ በሆኑ መሰረታዊ ነገሮች አለመርካት፣ ትክክለኛ እና እውነተኛ የሆኑ ውሳኔዎችን ለማድረግ የመቸገር ጥማት። በዛሬው ወቅት በስፋት በዓለማችን የሚታየው የሰው ልጆች ለቁሳዊ ፍጆታዎች ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ብቻ አይደለም፣ መነፈሳዊ የሆነ ጥማትም ጭምር እንጂ! ይህም መንፈሳዊ ጥማት ለቁሳዊ ነገሮች ያለንን ጣማት በሚገባ እንድንረዳ ያደርገናል። አሁን ያለው የማኅበረሳባችን ክፍል የፍጆታ ተጠቃሚነት ደስታ ለማግኘት የመለኪያ መስፈርት አድርጎ በማቅረብ ወደ ምኞት ወጥመድ ውስጥ የሰው ልጆችን ሕይወት ይከታል፣  ሁል ጊዜ ያንን ጥማታችንን ለመወጣት በየእየ ሱቁ ደጃፍ ላይ ባሉት መስታዎቶች ውስጥ በሚገኙ ቁሳቁሶች ላይ በማፍጠጥ፣ በመግዛት፣ አንድ ቁስ የሆነ ነገርን በማግኘት፣ ቁሳቁስ ለሆኑ ነገሮች ከፍተኛ ቦታን በመስጠት ጊዜያችንን እናባክናለን። ይህም በስጣችን ያለውን ባዶነት ያባብሰዋል።

ለቁሳቁስ ነገሮች ያለን ፍላጎት ለሌላ ነገር እንደ ሚጎለን ያሳየናል፣ አሁንም ብሆን ለቁሳዊ ነገር እንደ ጎደለን እንዲሰማን ያደርጋል እንጂ ለቁሳዊ ነገሮች ያለንን ጥማት አይቆርጥም። በእዚህም አጋጣም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠማ ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግም ሁሉ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድበማለት ጥሪ ያቀርብልናል።

እኛ ከመንፈሳዊ ሕይወታችን እየሸሸን መሆናችንን ሳንረዳ ወይም ሳንውቅ በሌላ እለታዊ አስተሳሰብ እንድንወሰድ የሚያደርጉን ብዙ መንገዶች አሉ። በጣም በተራቁቁ ምክንያቶች እንወሰዳለን እነርሱ ሕይወታችንን ይበክሉዋታል ጉልበትም ያሳጡናል። በውስጣችን ያለውን በጥልቀት የሚገኙውን ባዶ ቦታ በመመልከት ይህንን ጥማታችንን በሚገባ ለመቁረጥ የሚያስችሉ ነገሮችን በእውነተኛ መንገድ ማግኘት እንችል ዘንድ እውነተኛ ውሳኔ ማድረግ ይገባናል። ስለእዚህም እርምጃዎቻችንን እናዘግያቸው፣ በእውነት የሚያስፈልጉን ነገሮች ምን መሆናቸውን በጥንቃቄ እንመልከት፣ በእመነት መቀመጫ ላይ በመቀመጥ፣ ለቁሳዊ ነገሮች እና ኢኮኖሚያዊ ለሆኑ ጉዳዮች ለማሰብ ሳይሆን የሕይወታችንን ጥያቄዎች ማሰብ እንጀምር።ከሰዎች ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ያለንን ጥማት፣ ሰዎች እንዲቀበሉን እና እንዲወዱን ያለንን ፍላጎት እና ጥማት እናስብ። እነዚህን ነገሮች በጥልቀት በማሰብ እና ጸጋን ለመጠየቅ ተጠርተናል። ይህ ደግሞ በጣም ከባድ የሚባል ነገር አይደለም፣ ጥማታችንን በእግዚኣብሔር ላይ እንድርግ።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ይህ ቀደም ሲል ያቀረብንላችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የእርሳቸው የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች በጋራ በመሆን ይህንን የያዝነውን የዐብይ ጾም ወቅት አስመልክተው በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አራቺያ በሚባልበት ስፍራ በሚገኘው ዲቪኒ ማዬስትሮ በተባለው የሱባሄ መስጫ ማዕከል ተገኝተው እያደርጉት በሚገኘው ሱባሄ ላይ አባ ጆዜ ቶሌንቲኖ የተባሉ ካህን በዩሐንስ ወንጌል 4:4-23 ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር በተገናኘበት ወቅት ውሃ አጠጭኝ ብሎ በጠየቀው ጣያቄ ዙሪያ ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን ስብከት ነበር።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.