2018-02-17 09:09:00

በፈረሳይ አገር በሉርድ ከተማ 70ኛ የተዓምር ምልክት መታየቱ ተሰማ።


በፈረሳይ አገር በሉርድ ከተማ 70ኛ የተዓምር ምልክት መታየቱ ተሰማ።

በፈረንሳይ አገር፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስትያን በምትገኝባት በሉርድ 70ኛ የተዓምር ምልክት መታየቱ ተሰማ።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቤተ ክርስትያኗ የታነጸችበትን 160ኛ ዓመት ክብረ በዓል በተከበረበት ዕለት ይፋ የሆነው መልዕክት እንደሚያስረዳው፣ ሰውነትን በሚያሰልል በሽታ ሲሰቃዩ የቆዩት የፍራንችስካዊያን ማህበር አባል የሆኑት ሲስተር ቤርናዴት ሞራው ከያዛቸው በሽታ ሙሉ በሙሉ መፈወሳቸውን ከሕክምና ባለሞያዎች ማረጋገጫ ካገኙ በኋላ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ሲስተር ቤርናዴት ስለ ሆነው ሁሉ በገለጹበት ንግግራቸው፣ በሃገረ ስብከታቸው በተዘጋጀው እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስትያን ወዳለበት ወድ ሉርድ ካደረጉት መንፈሳዊ ጉዞ መልስ፣ የእመቤታችንና የቅድስት ቤርናዴት ምስል ሲገለጽ ማየታቸውንና ከዚያ በኋላም በሰውነታቸው ሙሉ በሙሉ የፈውስ ስሜት እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ሲስተር ቤርናዴት እንዳስረዱት እስከ ሕይወቴ መጨረሻ የሚቀረኝን የሕይወት ዘመኔን በብቃት ለመጓዝ የሚያስፈልገኝን ሃይልንና ብርታትን  ጠይቄአለሁ እንጂ ለዓመታት ካሰቃየኝ ሕመም እፈወሳለሁ ብዬ ፈጽሞ አላሰብኩም ብለዋል። በእርግጥም ከያዘኝ በሽታ ሙሉ በሙሉ መፈወሴን ያወቅሁት ከዓለም አቀፍ የጤና ቢሮ ማረጋገጫ ካገኘሁ በኋላ ነው ብለዋል። 

ሲስተር ቤርናዴት በማከልም በሐምሌ 4 ቀን 2000 ዓ ም በሃገረ ስብከታቸው በተዘጋጀው እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስትያን ወዳለበት ወድ ሉርድ መንፈሳዊ ጉዞ በማድረግ በጸሎት ዝግጅቶች በመሳተፍ እና ምስጢራትን በመቀበል መልካም የሆነ መንፈስዊ ጊዜ እንደነበር አስታውሳለሁ ብለው በስፍራው በተከናወኑ መንፈሳዊ ዝግጅቶች በመሳተፍ፣ ለሕሙማን በተደረጉ የጸሎት እና የቡራኬ ስነ ስርዓቶች ተካፋይ  መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሉርድ በሚገኘው የእመቤታችን ቤተ ክርስትያን ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር ሆነን ባደርግሁት የሕብረት ጸሎቶችና ዝግጅቶች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላችን እንዳለ ይሰማኝ ነበር። በጸሎት ስነ ስርዓቶችም ለሌሎች ሕሙማንም የግል ጸሎት በማድረግ እነርሱንም አስታውሼአቸዋልሁ ብለዋል።

ሲስተር ቤርናዴት ንግግራቸውን በመቀጠል በሕይወቴ ፈጽሞ ስለ ተዕምራት ተናግሬ አላውቅም። ነገር ግን ከበሽታ ስለመፈወስ ብዙ ጊዜ እናገር ነበር ብለዋል። መላውን ሕይወቴን ከእግዜብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለኝ እርሱንም ለማገልገል ፍላጎት እንዳለኝ አውቃለሁ ብለዋል። በቅዱስ ቁርባን ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስን መገኘት በእውነት አምናለሁ። የቤተ ክርስትያን ሕይወት እና ቤተ ክርስትያንን ለማገልገል ትልቅ ምኞት አለኝ ብለውል።








All the contents on this site are copyrighted ©.