2018-02-10 09:16:00

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በዝምታ መመልከት አንችልም ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በዝምታ መመልከት አንችልም ማለታቸው ተገለጸ።

ትናንት የቅድስት ጁሴፓ ባኪታ መታሰቢያ ዕለት ተከብሮ በዋለበት፣ በተመሳሳይ ዕለትም ዓለም አቀፍ የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ቀን እንደመሆኑ ይህን በማስታወስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅድስት ጁሴፒና ኢየሱስ ክርስቶስ ባመጣላት ብርሃን በመታገዝ ወደ ብርሃን መውጣቷን አስታውሰዋል።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ቀንን ምክንያት በማድረግ ባሰሙት ንግግር  ከጦርነት የሚሸሹትን፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑትን በምሕረት መንፈስ ተነሳስተን እንቀበላቸው ብለዋል። በማከልም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕገ ወጥ ዝውውር ተይዘው ሲሰቃዩ እና ክብራቸውን ሲገፈፉ በዝምታ መመልከት አይቻለንም ብለዋል። የሰው ልጆች ክብራቸውን ተገፍፈው የባርነት ሕይወት ሲኖሩ ማየት እጅግ ይከብዳል ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ትናንት ባሰሙት ንግግራቸው በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩት ወንጀለኞች በእጃቸው ተይዘው ያሉትን ሰዎች ከስደተኞችና ከጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር ያሳብባሉ ብለዋል። ይህ በመሆኑ ሕብረትን በማጠናከር ሕገ ወጥ የሆነውን የሰዎች ዝውውርን ለማስወገድና በሰው ሕይወት ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ማስቀረት እንደሚያስፈልግና በሌላ ወገንም በወንጀሉ የተሰማሩ ሰዎችን ልብ እግዚአብሔር እንዲቀይር መጸለይ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

“ሰዎች በነጻነት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ መቻል ያስፈልጋል” የሚለውን የዘንድሮ መሪ ቃል ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በርካታ ስደተኞች አደገኛ ጉዞን በማድረግ፣ ለባርነትና ለብዝበዛ እንደሚጋለጡ በመገንዘብ፣ ካሁን ወዲያ በባርነት መገዛት ይቅር፣ ነጻነት መንገስ ይገባል ብለዋል። ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በትመለከተ ጥናት እየተደረገ እንደሆነ አስታውሰው ይህም ጥናት ዘንድሮ ጉዳዩን አስመልክቶ ትናንትና ዛሬ በቫቲካን በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ግንባር ቀደም ርዕስ ሆኖ እንደሚቀርብ ገልጸዋል። በዚህ ጉባኤ ላይ የቤተ ክርስቲያን ተወካዮች፣ ከተለያዩ አገራት የተወጣጡ የፖሊስ ሰራዊት አባላት፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር የተሰማሩት ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጽኑ የሚቃወም የቤተ ክርስቲያን ድርጅትና፣ የታሊታ ኩም ዓለም አቀፍ ድርጅት አስተባባሪ የሆኑት ሲስተር ጋብርኤላ ቦታኒ ለቀርበላቸው ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት ለዘንድሮ አለም አቀፍ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ቀን የተመርጡት የውይይት ርዕሶች በጉዳዩ ላይ በስፋት እንድንወያይ ስላደረጉን እጅግ አስፈላጊ ሆነው አግኝተናል ብለዋል።

በአውሮፓ አገሮች ስደት እያስከተለ ያለው ቀውስ በገሃድ እየታየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በስደተኞች ጉዳይ ዙሪያ ለሚነሱት ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማፈላለግ በመንግሥታት ዘንድም ግንባር ቀደም የመነጋገሪያ ርዕሥ ሆኗል። በካቶሊካዊ ድርጅቶች፣ ማሕበራትና እንቅስቃሴዎች በሙሉ አዲስ የመፍትሄ ሃሳቦችን በማፍለቅ፣ ማሕበራዊ ኑሮ ሰላማዊ እንዲሆንና ፍትሕንም ለማንገሥ ድምጻቸውን ማሰማት ይጠበቅባቸዋል ተብሏ።








All the contents on this site are copyrighted ©.