2018-01-20 17:59:00

የጥር 13/2010 ዓ.ም. ዘጥምቀት ወይም አስተርዮ 1ኛ ሰንበትን ምንባባት እና አስተንትኖ በክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ


የጥር 13/2010 .. ዘጥምቀት ወይም አስተርዮ 1 ሰንበትን ምንባባት እና አስተንትኖ በክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ

 

የእለቱ ምንባባት

1. ዕብ.21-10

ስለዚህ ከሰማነው ነገር ስተን እንዳንወድቅ፣ ለሰማነው ነገር አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባናል። ምክንያቱም በመላእክት በኩል የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነና ማንኛውም መተላለፍና አለመታዘዝ ተገቢውን ቅጣትከተቀበለ፣ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከእርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን። እግዚአብሔርም በምልክት፣ በድንቅና በልዩ ልዩ ታምራት እንዲሁም እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ስለ ዚሁ ነገር መስክሮአል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ኢየሱስ ወንድሞቹን መሰለ

ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም፤ ነገር ግን አንዱ በሌላ ስፍራ እንዲህ ብሎ መስክሮአል፤“ታስታውሰው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ታስብለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው”ከመላእክት ጥቂትአሳነስኸው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት፤ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት።

እግዚአብሔር ሁሉን ከበታቹ ሲያስገዛለት፣ ያላ ስገዛለት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ጥቂት እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ፣ የሞትን መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናየዋለን።

ሁሉ ነገር ለእርሱና በእርሱ የሚኖር እግዚአብሔር፣ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት፣ የድነታቸውን መሥራች በመከራ ፍጹም ሊያደርገው የተገባ ነበር።

 

1ዩሐ51-12

እግዚአብሔር ልጅ ማመን

ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፤ አባትንም የሚወድ ሁሉ ልጁንም እንደዚሁ ይወዳል። እግዚአብሔርን ስንወድና ትእዛዛቱን ስንፈጽም የእግዚአብሔርን ልጆች እንደ ምንወድ በዚህ እናውቃለን፤ እግዚአብሔርን መውደድ ትእዛዛቱን መፈጸም ነውና። ትእዛዛቱም ከባድ አይደሉም፤ ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሸንፈውም እምነታችን ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በስተቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማነው?

በውሃና በደም የመጣው ይህ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ በውሃና በደም እንጂ በውሃ ብቻ አልመጣም። የሚመሰክረውም መንፈስ ነው፤ መንፈስ እውነት ነውና። ስለዚህ ሦስት ምስክሮች አሉት። እነርሱምውሃውና ደሙ ናቸው፤ ሦስቱም ይስማማሉ። የሰውን ምስክርነት ከተቀበልን፣ የእግዚአብሔር ምስክርነት ከዚያም ይልቃል፤ ይህ ስለ ልጁ የሰጠው የእግዚአብሔር ምስክርነት ነውና። በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ሁሉ በልቡ ምስክር አለው፤ ማንም እግዚአብሔርን የማያምን ሁሉ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

 

.ሐዋ.1034-38

ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤ “እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ በርግጥ ተረድቻለሁ፤ ነገር ግን እርሱን የሚፈሩትንና ጽድቅን የሚያደርጉትን ሁሉ ከየትኛውም ወገን ቢሆኑ ይቀበላቸዋል። እግዚአብሔር፣ የሁሉ ጌታ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የላከውም የሰላም የምሥራች መልእክት ይኸው ነው። ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በመላው ይሁዳ የሆነውን ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።

ዩሐ 21-13

ኢየሱስ ውሃን የወይን ጠጅ አደረገ

በሦስተኛው ቀን፣ በገሊላ አውራጃ፣ በቃና ከተማ ሰርግ ነበር፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር። 3የወይን ጠጅ ባለቀ ጊዜም የኢየሱስ እናት፣ “የወይን ጠጅ እኮ አለቀባቸው” አለችው። ኢየሱስም፣ “አንቺ ሴት ሆይ፤ ምን አድርግ ትይኛለሽ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም” አላት።

እናቱም በዚያ የነበሩትን አገልጋዮች፣ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው።

በአይሁድ የመንጻት ሥርዐት መሠረት፣ ከሰባ አምስት እስከ አንድ መቶ ዐሥራ አምስት ሊትር የሚይዙ ከድንጋይ የተሠሩ ስድስት ጋኖች በዚያ ነበሩ። ኢየሱስ አገልጋዮቹን፣ “ጋኖቹን ውሃ ሙሏቸው” አላቸው፤ እነርሱም፣ ጋኖቹን እስከ አፋቸው ሞሏቸው። እርሱም፣ “ከላዩ ቀድታችሁ ለድግሱ ኀላፊ ስጡት” አላቸው።

እነርሱም እንዳዘዛቸው አደረጉ። የድግሱ ኀላፊም ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውሃ ቀመሰ፤ ሆኖም ከየት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር። እርሱም ሙሽራውን ለብቻው ጠርቶ፣ “ሰው ሁሉ በመጀመሪያ የሚያቀርበው ጥሩውን የወይን ጠጅ ነው፤ እንግዶቹም ብዙ ከጠጡ በኋላ መናኛውን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቈይተሃል” አለው። ኢየሱስም ይህን የታምራዊ ምልክቶቹ መጀመሪያ በገሊላ አውራጃ በቃና ከተማ አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።

 

የጥር 13/2010 ዓ.ም. ዘጥምቀት ወይም አስተርዮ 1 ሰንበትን ምንባባት እና አስተንትኖ በክቡር አባ ግርማቸው ተስፋዬ

በክርሰቶስ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዲሁም መልካም ፈቃድ ያላችሁ ሁሉ ዛሬ እንደ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓትአቆጣጠር  ዘጥምቀት ወይም አስተርዮ 1ኛ ሰንበትን እናከብራለን ፡፡

ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ዛሬ ለዕብራውያን በፃፈው መልእክት አማካኝነት እያንዳንዳችንን ይጎበኘናል፡፡

እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የኦሪትን መጻሕፍት የሕይወታቸውንም መመሪያ ሲሰጣቸው በእርሱ መንፈስና በመላእክቱ አማካኝነት ያከናውን ነበር፡፡ እግዚአብሔር በቡሉይ ኪዳንን ሕግ ያስተማረው በመላእክትና በተለያዩ ዓበይትና ንዑሳን ነቢያቶች ቢሆንም ሕዝቡ ሕጉን ተቀበሉት እንጂ በሕይወታቸው አልተገበሩትም፡፡ በሐዋርያት ሥራ 8፣53 እንዲህ ይላል  በመላእክት አማካኝነት የተሰጣችሁንም ሕግ ተቀበላናችሁ እንጂ አልጠበቃችሁትም፡፡ በአዲስ ኪዳን ዘመን ግን እግዚአብሔር  ሕግን የሰጠውና ያስተማረው በአንድ ልጁ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ዕብ.1፡2 በዚህ በመጨረሻው ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን ይላል፡፡   

ይህ የእርሱ መንፈስና የመላእክት የነቢያት ተግሣፅና ትምህርት የሰዎችን ልብ ሙሉ በሙሉ ሊገዛ ባለመቻሉ አምላክ ራሱ ወደ ምድር መጥቶ ይህንን ተግሣፅን ይህንን ትምህርት አስተማረን፡፡ 

ስለዚህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መመጣቱ የመዳናችን አብሳሪ ብቻ ሣይሆን የመዳናችንም ምክንያት ነው የመዳናችንም መሠረት ነው፡፡፡፡

ምክንያቱም በእርሱ ሞት እኛ ዘለዓለማዊ ክብርን አገኘን፣ እርሱ ባስተማረን በቅድስና ጐዳና እንድንራመድ አደረገን፣ የደህንነትን መንገድ ከፈተልን፣፣  እርሱ ወዳለበት ወደ ዘላዓለማዊ ክብር ጠራን፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ ቀኝ በክብር የተቀመጠውን ብዙ መከራንና ስቀይን ከተቀበለ በኃላ እንደሆነ ሁሉ እኛም ይህንን ዘለዓለማዊ ክብር ለመቀዳጀት ብዙ ተጋድሎን እንድናደርግ ይጋብዘናል ዘወትር ከኃጢአት በመራቅና ሰይጣንንና ክፉ ሥራውን ያለማቋረጥ እንድንዋጋው ይጠይቀናል ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንደሚናገረው ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የምትወስደው መንገድ ጠባባ መሆኗን ተናግሯል ስለዚህ በዚች ጠባብ መንገድ ማለፍ መቻል አለብን፡፡

በዚች ጠባብ መንገድ ላይ መራመድ የምንችለው መንፈሳዊ ሕይወታችን በጸሎትና በተጋድሎ የተገንባ ከሆነ ብቻ ነው፡፡  ሕይወታችንን በጸሎትና በተጋድሎ ለመንገንባት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ወሳኝነት አለው፡፡

እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ይወዳል በፍቅርና በደስታ እንድንኖራም ይፈልጋል  ለዚህም ደግሞ ጸጋና በረከቱን ዘወትር በምሥጢራቱ አማካኝነት ያድለናል፡፡

በምሥጢራቱ አማካኝነት የሚያድለንን ጸጋ ተቀብለን በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ በፍቅር መመላለስ የእያንዳንዳችን ኃላፊነት ነው፡፡  እግዚአብሔር ይወደናል ብለናል እግዚአብሔር እንደወደደን እኛም መውደዳችንን ማረጋገጥ አለብን፤

ቅዱስ ሕዋርያው ዬሐንስ በመልእክቱ (1ዩሐ.5፡1-12) ሲናገር እግዚአብሔርን መውደዳችንን የምናረጋግጠው ለትዕዛዞቹ ተገዢ ስንሆን ብቻ ነው  ትዕዛዞቹን ፈፅምን ማለት ደግሞ እግዚአብሔርን ብቻ ሣይሆን በእርሱ አርአያ የተፈጠሩተነ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ሁሉ አከባርን ወደድን ማለት ነው፡፡ዩሐ. 14፡15 “እግዚአብሔርን ከምንምና ከማንም በላይ መውደድ ማለት ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በአርአያ ሥላሴ አምሳል የተፈጠሩትን ሁሉ ዘርና ቀለም ሳንመርጥ ሃብታምና ደሃ ሳንል ልክ እንደራሳችን አድርገን መውደድ ማለት ነው”

ቅዱስ ሐዋርያው ዩሐንስ እንዳለው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚጓዝ ሁሉ ሕይወት እንዳለው ይናገራል፡፡  ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የማይጓዝ ደግሞ ሕይወት የለውም ምክንያቱም ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ጋር የሚጓዝ የእርሱን ቃል ይፈፅማል የዘለዓለም ሕይወት ወራሽ ይሆናል፡፡ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የማይጓዝ ግን የራሱን የግሉን ፈቃድ ብቻ ይፈፅማል በዚህም ምክንያት ዘወትር በኃጢያት ውስጥ ይኖራል፡፡  የኃጢያት ክፍያ ደግሞ ሞት ነውና ዘለዓለማዊ ቅጣትን ወራሽ ይሆናል፡፡  ዘለዓለማዊ ሕይወትን ከመውረስ ራሱን ያገላል፡፡

ስለዚህ ቅዱስ ሐዋርያው ዩሐንስ እንደሚለን በዘለዓለማዊ ሕይወት ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን ዘወትር ከእግዚአብሔር ጋር አብረን መጓዝ እንዳለብን ይመክረናል፡፡ ምክንያቱም እርሱ ሕይወት ነውና ሁሌም ልጆቹን በሕይወት ጎዳና ይመራልና፡፡

የዛሬው የዩሐንስ ወንጌል 2፡1-13 የሚናገረው የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያው ተዓምር የሆነውን ውኃን ወደ ወይንጠጅ የመለወጥ ተዓምር ነው ፡፡

በዚህ በቃና ዘገሊላ ተዓምር ላይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትልቅ ድርሻ አላት አምላክ ሰውሆኖ ሲመጣ በውስጧ የተሸከመችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዛሬም የጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ  የመጀመሪያው ተዓምር እንዲገለጥ ምክንያት ሆናለች “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” ብላ ስለእነርሱ አማለደች፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም የሁላችን እናት ናትና የእያንዳዳችን ጭንቅ ይገባታል የእያንዳዳችንን ጥያቄና ልመና ይዛ በአምላካችን ፊት ቆማ ታማልደናለች፡፡

እመቤታችን ድንግል ማርያም ይህን ቃል ስትናገር በልጇ አምላክነት ሁሉን ቻይነት ተማምና ለአገልጋዮቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው” እነርሱም አደረጉ ከበፊቱ የበለጠ ወይን ጠጅም ሆነ፡፡  ይህ የቃና ሰርግ የውኃው ወደ ወይን ጠጅ መለወጥ በውስጡ ብዙ ነገሮችን የያዘ ነው፡- ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በይፋ ሐዋርያዊ ሥራውን መጀመሩን  ፤ የእግዚአብሔርንም ክብር በምድር ላይ መገለጡን እንዲሁም ሐዋርያቶቹም በእርሱ ላይ ያላቸው እምነት መጨመሩን ያበሥረናል፡፡

ይህ ሁሉ የሆነው በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ጠያቂነት በእርሷ አማላጅነት ነው፡፡ ዛሬም እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ይህንን የማማለድ ሥራዋን ቀጥላለች ለእያንዳዳችን ከልጇ ጸጋና በረከትን ታሰጠናለች በችግራችን ሁሉ ከእኛ ጋር አብራ ትቆማለች ስለዚህ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥም ከዘለዓለም እስከ  ዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን፡፡

 








All the contents on this site are copyrighted ©.