2018-01-19 11:06:00

ትክክለኛው አንድነት ሊፈጠር የሚችለው “ዓመጽ አልባ የሆነ፣ ፖሌቲካን ለሰላም” በመጠቀም ብቻ ነው


ቅዱስነታቸው በመቀጠል ከቺሊ ዋና ከተማ ሳንቲያጎ 674 ኪሎሜትሮች ርቃ በምትግኘው እና የቺሊ ቀደምት ተዋላጆች የሚኖሩባትን ቴሙኮ በሚባል ስፍራ በመገኘት ብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው የተገልጹዋል። ቴሙኮ ከቺሊ ክፍለ ሀገራት አንዱዋ የሆነቺው የአራውቺያና ዋና ከተማ መሆኑዋም የተገለጸ ሲሆን በእዚህ ክፍለ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች የቺሊ የቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች ዘር እንደ ሆኑ ይታወቃል። ቺሊ በእፔን ቅኝ ግዛት ሥር በወደቀችበት ወቅት እነዚህ የቀድሞ ተወላጅ ሕዝቦች ከወራሪዎች ጋር ከፍተኛ ጦረነት መግጠማቸውን ከታሪክ ማሕደር ለመረዳት የሚችላ ሲሆን፣ አሁኑም ቢሆን የቀድሞ ባሕላቸውን እና ቋቋቸውን ጠበቀው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው። በእዚህም ምክንያት አንድ አንዴ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ከሌሎች የቺሊ ተወላጆች ጋር በትደጋጋሚ መጋጨታቸው የተለመደ ክስተት ሲሆን እነዚህ  የቺሊ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች ይህ ግጭት የሚፈጠረው “ባሕላችንን እና ቋንቋችንን” ጠብቀን እንዳኔድ የሚያደርጉ ተግዳሮቶች በሚገጥሙን ወቅት ነው ብለው እንደ ሚያሙንም ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።

በእዚች ከተማ ሁለት ታላላቅ ዩኒቬርሲቲዎች የሚገኙ ሲሆን አንደኛው ዩኒቬርሲቲ ቤካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር የሚተዳደር እንደ ሆነም ተገልጹዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቺሊ በሚያደርጉት 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኚታቸው ትኩረት ሰጥተው አንደኛው መዳረሻቸው ካደርጉት የቺሊ ክፍለ ሀገራት ውስጥ ይህቺ የቴሙኮ ከተማ ስትሆን ቅዱስነታቸው በእዚያው ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴን ማስረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ በእርሳቸው መሪነት ባስረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት በዩሐንስ ወንጌል 17፡21 ላይ ኢየሱስ የተናገረውን “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ”የሚለውን በማጣቀሻነት በመውሰድ የቴሙኮ ቀድመት ሕዝቦች ከሌሎች የቺሊ ነዋሪ ከሆኑ ሕዝቦች ጋ ሕብረት መፍጠር እንደ ሚገባቸው እና ማንኛውንም ዓይነት ጥያቄዎቻቸውን እና ሐሳባቸውን ኃይል በተቀላቀለው መልኩ ከማድረግ መቆጠብ እንደ ሚኖርባቸው ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው በእዚህ የአራውቺያና ክፍለ ሀገር መገኘታቸው  እና የእዚህን ክፍለ ሀገር ውብ የሆነ መልክዕ ምድር በማየታቸው እጅግ እንደ ተደሰቱ ገልጸው “የእዚህ ሀገር ውብ የሆነ የመሬት ገጽታ እኛን ይህንን ወደ ፈጠረው ወደ እግዚአብሔር ያነሳል፣ በእያንዳንዱ ፍጡር ውስጥ እጆቹን ሥራ ለማየት ቀላል ነው ካሉ ቡኃላ ከእዚህ ቀደም የኖሩ የማሕበረሰብ ክፍሎች ይህንን ውብ የሆነ ተፈጥሮ ማየት በጣም ይወዱ እንደ ነበረ ከገለጹ በኃላ እርሳቸውም ቢሆኑ ይህንን ውብ የሆነ መልክዕ ምድር በጣም እንደ ወደዱት፣ ይህንንም ለመጎብኘት በመታደላቸው በጣም መደሰታቸውን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ የቀደሞ የማፑኬ ሕዝቦች ዘር ከሆኑ አንድ አንድ ተወላጆች ጋር መገናኘታቸውን በማስታወስ በስብከታቸው ወቅት እንደ ተናገሩት “አሁን እዚህ ተሰብስባችሁ መስዋዕተ ቅዳሴን በምትሳተፉበት በአሁኑ ወቅት ሁለት ዕእይነት ስሜት እንደ ሚሰማችሁ ለመገመት እችላለሁ ካሉ በኃላ በቀዳሚነት በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በመሳተፋችሁ እግዚኣብሔርን እያመሰገናችሁ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በሐዘን እና በጭንቀት ስሜት ውስጥ እናዳላችሁ ያሰማኛል ብለዋል።

ሐዘናችሁ እና  ጭንቀታችሁ የመነጨው ይህ የእናንተ የማፑኬ ግዛት በተደጋጋሚ በደረሰባችሁ የሰብዐዊ መብት ጥሰት ምክንያት የተንገላቱ ብዙ ዘመድ አዝማዳቹ እያሰባችሁ በመሆኑ የተነሳ ነው ካሉ በኃል በእዚህም አጋጣሚ የእዚህ ጥቃት ሰለባ በመሆን ለተሰቃዩ እና ብሎም ለሞቱ ሰዎች ይህንን መስዋዕተ ቅዳሴ እያቀረብን፣ አሁንም ቢሆን በኢፍትሀዊ ተግባራት የተነሳ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ጥሰት እየደረሰባቸው የሚገኙ ሕዝቦችን ቁስሎች እግዚኣብሔር ይፈውስ ዘንድ በእዚሁ መስዋዕተ ቅዳሴ እንማጸናለን፣ ካሉ ቡኃላ በመስቀል ላይ ራሱን የሰዋው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ እና ሕመም የእነዚህንም ሰዎች ስቃይ እና ሕመም ይፈውስ ዘንድ እንደ ሚማጸኑም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን ሁሉም እኩል ይሆኑ ዘንድ ወይም ሁሉም ተመሳሳይ ይሆኑ ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ አለመጸለዩን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ መሆን ወይ ሕብረት መፍጠር ማለት ልዩነቶችን ማስወገድ ማለት እንዳልሆነ ቅዱስነታቸው አብክረው ገለጸዋል።

አንድነት አሉ ቅዱስነታቸው አንድነት "በግዳጅ የሚፈጠር ነገር አይደለም፣ እንዲሁም የተወሰኑ ሰዎችን በማግለል የሚፈጠር ሕብረት አለመሆኑን” በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ ለአባቱ ያቀረበው እና የጠየቀው አንድነት ሁሉንም ባህሎች ያካተተ፣ እና እያንዳንዱ ባሕል «ለእዚህች በበረከቶች የተሞላች ምድር» የሚያደርገውን የበኩልን አስተዋጾ ከግምት ባስገባ መልኩ እንደ ነበር ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

“አንድነት ልዩነቶችን አቅፎ የያዘ መሆን እንደ ሚገባው፣ በግለሰብ ይሁን በማኅበረስብ ደረጃ  በመጠሪያ ስማቸው የተነሳ በደል እና ወቀሳ ሊደርስባቸው በፍጹ እንደ ማይገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው አንድነት ሊመስረተ የሚገባው “በመከባበር እና ሕብረትን በመፍተር” ላይ የተመሰረተ መሆን እንደ ሚገባው ገልዋል።

አንድነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁለት ዓይነት ዓመጾች ይገኛሉ በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው በመጀመሪያ ደረጃ አንድነት በፍዙም ተግባራዊ ሊሆኑ አይችልም፣ አማላይ ከሆኑ ወይ እንዲሁ ለይስሙላ የተቀመጡ  ስምምነቶችን ከመቀበል ተጠንቀቁን ከሚል ጽንሰ-ሐሳብ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ምክንያት የሚፈጠር ዓመጽ ተስፋን እንደ ሚያጨልም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ “የሌሎችን ባሕል ባላከበረ መልኩ የሚፈጠር አንድነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና በእዚህም ምክንያት የተነሳ የሰው ነብስ በሚነሳው ዓመጽ የሰው ልጆችን ክቡር የሆነ ነብስ እንደ ሚቀጥፍ የገለጹት ቅዱስነታቸው የእዚህ ዓይነቱ አመጽ ደግሞ አንድነትን አደጋ ላይ የሚጥል የዓመጽ ዕእይነት መሆኑንም ቅዱስነታቸው አብራርተዋል።

በእነዚህ ሁለት ዓይነት ዓመጾች አንድነት ለመፍጠር መሞከር መልኩ የሚፈጠረው "እንደ የእሳተ ገሞራ የሚታፈው የድንጋይ ቅላጭ በመንገድ ላይ ያገኘውን ሁሉንም ነገሮች የሚያቃጥል” ሁሉ ዓመጽን በማስነሳት አንድነት ለመፍጠር መሞከር እጅግ አደገኛ መሆኑን ቅዱስነታቸው አውስተዋል።

ትክክለኛው አንድነት ሊፈጠር የሚችለው “ዓመጽ አልባ የሆነ፣ ፖሌቲካን ለሰላም” በመጠቀም ብቻ ሊሆን እንደ ሚገባው የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህም መሰረት በቺሊ የሚኖሩ ቀደምት ሕዝቦች “አንድ እንሆን ዘንድ የሰላም ተዋኒያን አድርገን” የሚለውን ጸሎት ወደ ኢየሱስ ማቅረበ እንደ ሚገባቸው ከገልጹ በኃላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.