2018-01-11 16:29:00

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ቺሊ እና ፔሩ የምጓዘው ደስታንና ወጌልን ይዤ ነው ማለታቸው ተነገረ።


ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ቺሊ እና ፔሩ የምጓዘው ደስታንና ወጌልን ይዤ ነው ማለታቸው ተነገረ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ቺሊ እና ፔሩ የምጓዘው ደስታንና ወጌልን በመያዝ፣ ከእግዚአብሔር የሚገኘውን ሰላም ከሕዝቡ ጋር ለመጋራት እና ይህን ተስፋ ለማረጋገጥ ነው ብለዋል።  ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን ይፋ ያደረጉት በቪዲዮ ምስል ባሰራጩት መልዕክታቸው ነው። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጥር 7 እስከ ጥር 14 ቀን 2010 ዓ ም ወደ ቺሊ እና ፔሩ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው ይታወቃል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሁለቱ አገሮች ሕዝቦች በላኩት በመልዕክታቸው፣ የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ጊዜ መቃረቡን ተናግረው፣ በአካል ለመገናኘት ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል፣ በጉብኝታቸው ቀናት ከሁለቱ አገሮች ሕዝቦች ጋር ሆነው፣ የእግዚአብሔርን አለኝታነት፣ የእርሱን ርሕራሄ እና ምሕረት አብሬአችሁ ለመመልከት ነው በማለት ልባዊ ሰላምታቸውን ልከዋል።

የሁለቱንም አገሮች ሕዝቦች ታሪክ በሚገባ አውቀዋለሁ ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልዕክታቸው፣ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ባለው እምነት፣ በሕብረተሰቡ መካከል ለተቸገሩትና ለተገለሉት ሰዎች ለሚያሳየው ፍቅር፣ በሕብረት እግዚአብሔርን ማመስገን እፈልጋለሁ ብለዋል።

የተሳሳተ እና የማይጠቅም ባሕል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣት የሚያሳስብ ነው ያሉት ቅዱስነታችው፣ ደስታችሁንና ሐዘናችሁን፣ ችግራችሁንና ብሩህ የሆነ የወደፊት ተስፋችሁን ከእናንተን ጋር ለመካፈል እፈልጋለሁ። ብቻችሁ እንዳልሆናችሁ፣ ከእኔ ጋር በመሆን መላዋ ቤተክርስቲያ ከጎናችሁ ቆማ እንደምትመለከታችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

እጅግ አስፈላጊ የሆነውንና ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ የሚመጣውን እውነተኛ ሰላም ከእናንተ ጋር በመሆን መመልከት እፈልጋለሁ። ይህ ሰላም ደግሞ ለሕዝባችን አንድነትና አብሮ ለመኖር መሰረታዊ የሆነ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን ስጦታ ነው። ይህን ሰላም ሳናቋርጥ እግዚአብሔርን መጠየቅ ያስፈልጋል። ደስታን የሚሰጥ የእምነታችን ስጦታ ስለሆነ ይህን ስጦታ ወደ ሌሎችም እንድናዳርስ፣ ከሌሎች ጋር መጋራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ከሞት ከተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘታችን ለእኛ ተስፋን ሰጥቶናል። በዓለማዊ ነገሮች ላይ ተስፋ ማድረግ አንፈልግም፣ ዓይኖቻችንም አርቆ በመመልከት የእግዚአብሔርን ምህረት መፈለግ ይኖርባቸዋል። ከውድቀታችን ሊያነሳን የሚችል የእግዚአብሔር ምሕረት ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን አለኝታነት በመገንዘብ፣ ከሌሎች ጋር የወንድማማችነት እና የጓደኝነት መንፈስ እንዲኖረን፣ በአንድ እምነትና በአንድ ተስፋ ላይ መቆም ያስፈልጋል።   

ስለዚህ ሐዋሪያዊ ጉብኝቴን እና የልባችን መሻት በሙሉ የላቲን አሜሪካ እናት ለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አደራ እንስጥ። እርሷ አማላጃችንና ወደ ልጇ የሚያደርሰንን መንገድ የምታሳየን እናታችን ናት ብለው፣ የሁለቱም አገር ሕዝቦች በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው አደራ ብለዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.