2018-01-09 09:16:00

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰብአሰገል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጸበት የአስተሪዮ በዓል መታሰቢያ በቫቲካን ተከበረ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 14.5 ሚልዮን ተከታይ ባለው የቲውተር ገጻቸው በጥር 30/2010 ዓ.ም. ባስተላለፉት ምልእክታቸው እንደ ገለጹት ደስታ፣ ጸሎት እና ምስጋና ሕይወታችንን እውንተኛ በሆነ መልኩ መኖር እንድንችል የሚረዱን ሶስት መንገዶች ናቸው ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በጥር 29/2010 ዓ.ም. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ በጥር 16/2017 ዓ.ም. በደመቀ መልኩ ተከብሮ ማለፉን መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ እለት ደግሞ አሁንም ይህንን የጎጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ በጥር 28/2010 ዓ.ም.  በኢትዮጲያ የገና በዓል ዋዜማ ዕለት ማለት ነው በማቴዎስ ወንጌል 2:1-12 ላይ የተጠቀሰው በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን፣ ኢየሱስ በቤተልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ ጠቢባን ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” በማለት ሰብአሰገል ወደ ቤቴሊሔም የሄዱበት የአስተሪዮ ወይም ሕጻኑ ኢየሱስ ለሰብአሰገል የተገለጸበት ቀን መታሰቢያ በደመቀ ሐይማኖታዊ ስነ-ስረዓት ተከበሮ ማለፉ ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ በዚሁ በአስተሪዮ ወይም ሕጻኑ ኢየሱስ  ለሰብአሰገል የተገለጸበት መታሰቢያ ቀን ላይ ከማቴዎስ ወንጌል 2፡1-12 ተወስዶ በተነበበው ቃል ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው እናቀርበዋለን አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የአስተሪዮ ወይም ሕጻኑ ኢየሱስ ለሰብአሰገል የተገለጸበት የመታሰቢያ በዓል ቀን ላይ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማቴዎስ 2:1-12) ኢየሱስን ወደ ዓለም በመጣበት ወቅት የተደርገለትን አቀባበል እና ለዓለም ራሱን የገለጠበት ሦስት ባሕሪያትን ለእኛ ያቀርባብልናል። እዚህም በደስታ ተሞልቶ መፈለግ፣ ቸልተኝነት እና ፍርሃት የሚባሉት ባሕሪያት ናቸው።

ሰብአሰገል መሲሁን  በደስታ መፈለግ አልታከቱም ነበር። ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜየተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልናሲሉ ጠየቁ” (ማቴ 2:2) በጣም ረጅም የሚባል ጉዞ አድርገዋል። አሁን ደግሞ በታላቅ ጉጉት አዲስ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የተኛበትን ሥፍራ ትክክለኛ ቦታውን ለምዋቅ በጉጉት ፍለጋቸውን ቀጥለዋል። ይህንንም  ሥፍራ በትክክል እንዲነግራቸው በማሰብ ወደ ንጉሥ ሄሮደስ ዘንድ ሄደው ይጠይቁታል። እርሱም የካህናት አለቆችንና የአይሁድ ሃይማኖት መምህራንን በሙሉ ሰብስቦ፣ ክርስቶስ የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው። 

ይህ በደስታ የተሞላ የሰብአሰግል ፍለጋ የካህናት አለቆችንና የአይሁድ ሃይማኖት መምህራንን ከነበራቸው የግዲየለሽነት ባሐሪ ጋር ይቃረናል። እነርሱም በነብያት የተጻፉትን መጽሐፍት በሚገባ ያወቁ ስለነበረ ኢየሱስ የተወለደበት ትክክለኛ ሥፍራ የማወቅ አቅም ነበራቸው። በእዚህም ምክንያት እነርሱም፣በይሁዳ ቤተልሔም፤ ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፎአልና አሉ” (25) ይሁን እንጂ ወደ እዚያ ሥፍራ ለመሄድ አልተመቻቸውም ነበር። ቤተልሔም እነርሱ ከነበሩበት ሥፍራ በጣም ጥቂት ኪሎሜትሮች ርቃ የምትገኝ ሥፍራ ብትሆንም እነርሱ ግን መነቃነቅ አልፈለጉም።

ከእዚህም የከፋው ደግሞ የሄሮድስ ባሕሪ ነውእርሱ ይባስ ብሎ ይህ የተወለደው ሕጻን ስልጣኑን የሚንጥቅበት መስሎት ስለተሰማው በጣም ደንግጦ ነበር። ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑን በምስጢር አስጠርቶ በማነጋገር ኮከቡ የታየበትን ትክክለኛ ጊዜ ተረዳ። ጠቢባኑንም ወደ ቤተልሔም ልኮ፣ሂዱና ሕፃኑን ፈልጉ፤ እኔም ደግሞ ሄጄ እንድሰግድለት፣ እንዳገኛችሁት ወደ እኔ ተመልሳችሁ የት እንዳለ ንገሩኝአላቸው (ማቴዎስ 2:7,8) በእርግጥ ሄሮድስ ሕጻኑ የተወለደበትን ሥፍራ ማወቅ የፈለገው ለሕጻኑ ለመስገድ ፈልጎ ሳይሆን ነገር ግን ባለአንጣ አድርጎ ስለቆጠረው ሊገለው ፈልጎ ነበር እንጂ።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ (ማቴዎስ 21-12) በደስታ መፈለግ፣ ችልተኝነት እና ፍርሃት የሚሉት ሦስት ባሕሪያት ተጠቅሰዋል። እኛም ከእነዚህ ከሦስቱ ባሕሪያት መካከል የትኛውን መውሰድ እንዳለብን መምረጥ ይኖርብናል።

የራስ ወዳድነት መንፈስ የኢየሱስ በሕይወታችን ውስጥ ለመኖር መምጣቱ እንደ ማስፈራሪያ አድርገን እንድንቆጥር ይገፋፋን ይሆናል። በዚህም መንፈስ የተነሳ የኢየሱስን መልእክት ላለማዳመጥ ወይም ደግሞ እርሱ የሚነግረንን መልእክት ሰምተን ዝም ለማለት እንሞክራለን። አንድ ሰው ሰብዓዊ የሆኑ ፍላጎቶችን ለምሳሌም በጣም ምቹ የሆኑ አመለካከቶችን፣ የክፋት ዝንባሌዎችን፣ በሚከተልበት ጊዜ ኢየሱስ እንደ እንቅፋት ሆኖ ይታየዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የቸልተኝነት ፈተና ዘወትር በእኛ ውስጥ ይገኛል። ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን እያወቅን እርሱ አዳኝ እንዳልሆነ አድርገንኢየሱስ አዳኝ መሆኑን ብናውቅም እንዳልሆነ አድርገን ለመኖር እንመርጣለን።  ከኛ የክርስትና እምነት ጋር በጥብቅ  ከመወዳጀት ይልቅ የዓለምን መርሆዎች እንከተላለን፣ ይህም የእብሪተኛነት  ዝንባሌን  የስልጣን እና የሐብት ጥማት እንዲኖረን ያደርጋል።

ይልቁኑም እኛ በደስታ እርሱን መፈለግ እንዳለብን እና አልፊ በሆኑ ሁኔታዎችም ውስጥ ሳይቀር ኢየሱስን ለማግኘት ዝግጁ መሆን እንዳለብን  ሰብአሰገልን ያሳዩንን አብነት ለመከተል ተጠርተናል።  እሱን ለማምለክ መፈለግ፣ እርሱ ጌታችን መሆኑን እንድናውቅ እና እርሱን ለመከተል የምያስችለንን ትክክለኛውን መንገድ የሚያመለክት እርሱ ብቻ መሆኑን ለማወቅ መሻት ይኖርብናል። እንዲህ ዓይነት አመለካከት ካለን ኢየሱስ በእውነት እኛን ያድነናል፣ እኛ አስደሳች ሕይወት ልንኖር ይችላል፣ በእምነት በመፈለግ እና በተስፋ በእግዚአብሔርና በወንድሞቻችን ላይ ያለንን ፍቅርን ማሳደግ እንችላለን።

በምድር ላይ ምጽሐተኞች ለሆንን ለእኛ ጨረቃችን የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ በአማላጅነቷ ትርዳን። የእናትነት እገዛዋ ሁሉም ሰዎች እውነተኛ ብርሃን የሆነውን ክርስቶስን በመከተል ዓለማችን በሰላም እና በፍትህ ጎዳና ላይ ትራመድ ዘንድ በአማላጅነቷ ትረዳን ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.