2017-12-28 14:19:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ በሮም ከሚገኙት የሕግ ታራሚዎች የተላከላቸውን የብርሃነ ልደቱ መልካም ምኞት መግለጫን መልዕክት ተቀበሉ።


ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ከተማ፣ ረቢቢያ ከሚገኙት የሕግ ታራሚዎች የተላከላቸውን የብርሃነ ልደቱ መልካም ምኞት መግለጫን መልዕክት ተቀበሉ።

የማረሚያ ቤቱ አባላት ለቅዱስነታቸው በላኩት የመልካም ምኞት መልዕክታቸው፣ በየዕለቱ የሚያጋጥመንን መከራ በእግዚአብሔር ምስጢራዊ ፍቅር በመታገዝ እንቋቋማለን። በፍቅር የተሞላ ልባዊ ምኞታችንን እያቀረብን በመካከላችንም ይህ ፍቅር እንዲበዛልን እንመኛለን ብለዋል።

የዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ከታራሚዎቹ መልዕክት ጋርም የቫቲካን ሬዲዮ የጣሊያንኛ ቋንቋ አገልግሎት ክፍል መልካም ምኞት፣ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዲደርሳቸው መደረጉን ታውቋል። ታራሚዎቹ ከቫቲካን ሬዲዮ የጣሊያንኛ ቋንቋ አገልግሎት የተሰጣቸውን ዕድል ተጠቅመው ለአድማጮቹና መላው ቤተሰቦቻቸው መልካም ምኞታቸውን መላካቸው ታውቋል። የቅድስት መንበር የመገናኛ መምሪያ ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሞንሲኞር ዳሪዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ እና በቫቲካን ሬዲዮ የጣሊያንኛ ቋንቋ አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት ሉካ ኮሎዲ በሕብረት ይህን ዕድል እንዳመቻቹላቸው ታውቋል።

በሌላው ላይ የፈጸሙትን ትልቅ በደል ወይም ክፋት በማሰብ የሚጸጸቱ አሉ። በአመጽና በክፋት በተሞላ ሕብረተሰብ መካከል ስለ ይቅርታ እና ምሕረት መወያየት ቀላል አይደለም። መላው ቤተሰብን ጭካኔ በተሞላ መንገድ የገደለን እንዴት ይቅር ማለት ይቻላል? በዚህ ምክንያት የብርሃነ ልደቱ በዓል በማረሚያ ቤት ውስጥ ሊሚገኙት ሰዎች፣ የሰሩትን የጭካኔ ድርጊት እንዲያስታውሱናን እንዲጨነቁ የሚያደጋቸው ወቅት ነው። ታራሚዎቹ በፈጸሙት ወንጀል ተጸጸተው፣ እንደ ራሳቸው በብቸኝነት ሕይወት ውስጥ ለሚገኙት እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦችም በሙሉ የብርሃነ ልደቱን መልካም ምኞት ልከውላቸዋል።

የቫቲካን ሬዲዮ የጣሊያንኛ ቋንቋ አገልግሎት ባመቻቸው የብርሃነ ልደቱ መልዕክት መለዋወጫ መንገድ በኩ  ምንም እንኳን ታራሚዎቹ ልባቸው በሰሩት ወንጀል ያዘነ ቢሆንም ከዚያ ልብ ውስጥ ፍቅርና ተስፋ ሊመነጭ ይችላል ብለዋል የፕሮግራሙ አስተባባሪ የሆኑት ሉካ ኮሎዲ።

የቫቲካን ሬዲዮ የጣሊያንኛ ቋንቋ አገልግሎት ክፍል፣ “ወንጌል በልባችን” በተሰኘው የሬዲዮ ዝግጅቱ፣ የማረሚያ ቤቱ አባላት የተመቻቸላቸውን ዕድል ተጠቅመው ከልብ የመነጨ የፍቅርና የተስፋ መልዕክቶቻቸውን ማስተላለፍ መቻላቸውን ገልጿል። የአገልግሎት ክፍሉ አስተባባሪው አክለው እንደገለጹት ማረሚያ ቤቶች ወንጀለኞችን በአንድ ኣዳራሽ ውስጥ ጠብቆ የሚይዝ ብቻ ሳይሆን የመልካም ልብ ማፍለቂያም ጭምር እንደሆነ አስረድተው፣ ታራሚዎቹ ሐሳባቸውን፣ መልካም ምኞታቸውን፣ ጭንቀታቸውንና የወደፊት ተስፋቸውንም በይፋ መግለጽ የሚችሉበት ሥፍራ ሊሆን እንደሚል ገልጸዋል።       

      

   








All the contents on this site are copyrighted ©.