2017-12-27 15:18:00

የቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ሰማዕት የሆነው የቅ. እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል በቫቲካን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።


የጎርጎስሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅብረሰቦች ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በደማቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተከብሮ ማለፉን ቀደም ሲል መገለጻችን ይታወሳል። በታኅሳስ 17/2010 ዓ.ም. እለት ደግሞ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ሰማዕት በመባል የሚታወቀው የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል ተዘክሮ ማለፉ ያታወቃል። ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙትን ስብከት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የዚህን ስብከት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ መወለዱን ካከበርን ቡኃላ ዛሬ ደግሞ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ሰማዕት የሆነውን ቅዱስ እስጢፋኖስ ወደ ሰማይ መወልዱን እንናክብራለን። በአንድ በኩል ሲታይ በሁለቱ ክስተቶች መካከል ምንም ትስስር ያለ ባይመስልም እውነታው ግን የሚያሳየን በጣም ጠንካራ የሆነ ትስስር እንዳለ ነው።

ባለፈው ሰኞ በተከበረው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ላይ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በታወጀው የእግዚኣብሔር ቃል ላይ “ቃል ሥጋ ሆነ፣ በመካከላችንም አደረ” (ዩሐንስ 1፡14)  የሚለውን አንብበናል። ቅዱስ እስጢፋኖስ የሕዝቡን መሪዎች አናውጡዋቸው ወይም አስጨንቁዋቸው ነበር፣ ምክንያቱም “በመንፈስ ቅዱስ እና በእመንት ተሞልቶ” (ሐዋ. ሥራ 6፡15) ስለነበረ ነው። በጣም ጥልቅ የሆነ እመንት የነበረው እና እግዚኣብሔር በአዲስ መልክ በሕዝቦቹ መካከል እንደ ሚኖር ይመሰክር ነበር፡ እውነተኛው የእግዚኣብሔር ቤተ መቅድስ ኢየሱስ እንደ ሆነ ያውቅም ነበር፣ ከሐጢአት በቀር እኛን በመምሰል፣ ይህ ዘለዓለማዊ የሆነ ቃል በመካከላችን ለማዳር መጣ። ነገር ግን እስጢፋኖስ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተመቅደስ ይጠፋል ብሎ በመስበኩ የተነሳ ተከሰሰ። በእርሱም ላይ ተቃቶ የነበረው ክስ “ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያጠፋና ከሙሴ የተቀበልነውን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።” (የሐዋ. ሥራ 6፡14) የሚል ክስ ነበረ።

በእርግጥ ይህ የኢየሱስ ምልእክት ምቹ የሆነ መልእክት አይደለም፣ እኛንም ምቾት እዲሰማን አያደርግም፣ ምክንያቱም ዓለማዊነትን የተላበሰ ሃይማኖታዊ ስልጣንን እና ሕሊናንም ስለ ምያነሳ ነው። እርሱ ከመጣ ቡኃላ ግን፣ መንፈሳዊ ለውጥ ማድረግ፣ አስተሳሰባችንን መቀየር፣ የባለፈው ጊዜ አስተሳሰቦችንም አውልቀን መጣል ይኖርብናል። እስጢፋኖስ እስከ መጨረሻው የሕይወቱ ፍጻመ ድረስ የእመንቱን ማዕለቅ ሙሉ በሙሉ በእየሱስ ላይ ጥሎ ነበር። እርሱ በሕይወቱ ማብቂያ አከባቢ ላይ “እስጢፋኖስም እየወገሩት ሳለ፣ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ነፍሴን ተቀበላትየሚለውን እና ከዚያም ተንበርክኮ፤ በታላቅ ድምፅ፣ጌታ ሆይ! ይህን ኀጢአት አትቍጠርባቸውብሎ ከጸለየ  በኋላም አንቀላፋ (የሐዋ. ሥራ 7፡59,60)። ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተናገራቸው “አባት ሆይ፤ መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ” (ሉቃስ 23፡46) ብሎ የተናገረው እና “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” (ሉቃስ 23፡34) ለሚሉት የኢየሱስ ቃላት እስከ መጨረሻ ድረስ እስጢፋኖስ ታማኝ ነበረ። እነዚህ የእስጢፋኖስ ቃሎች ልከሰቱ የቻሉት የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ምድር መጥቶ ስለ ሞተ እና ከሙታን ስለተነሳ ብቻ ነው፡ ከእነዚህ ክስተቶች በፊት ግን እነዚህ ቃላት በሰውኛ አንደበት ለመግለጽ የምከብዱ ቃላቶች ነበሩ።

እስጢፋኖስ መንፈሱን እንዲቀበል ኢየሱስን ይለምነው ነበር። በእርግጥ ከሞት የተነሳው ክርስቶስ ጌታ ነው፣ እናም እርሱ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የሚገኝ ብቸኛው ሸምጋይ ነው፣ እኛ በሞታችን ጊዜ እና ሰዓት ብቻ ሳይሆን በሁሉም የህይወት ዘመናችንም ጭምር ሸምጋያችን ነው። ያለ እርሱ ምንም ነገር ማድረግ አንችልም። ስለዚህ እኛ ሕፃኑ ኢየሱስ በተኛበት በግርግም ፊት ለፊት ቆመን እንዲህ ብለን መጸለይ እንችላለን፣ "ጌታ ኢየሱስ ሆይ መንፈሴን ወደ እናንተ አቀርባለሁ እና ተቀበለኝ" ብለን እንጸልይ። ምክንያቱም የእኛ የመኖር ሕልውናችን መልካምና ከወንጌል ጋር የተጣመረ እንዲሆን እንዲረዳን ነው።

ኢየሱስ በመካከላችን የሚገኝ አስታራቂ የሆነ አምላክ ነው፣ ከአብ ጋር ብቻ ሳይሆን እኛን እርስ በእርሳችን እንድንታረቅ ያደርገናል። እርሱ ከወንድሞቻችን ጋር ኅብረት እንዲፈጥር፣ ሁሉንም ግጭቶችና ቅሬታዎች በማስወገድ እንድንኖር የሚረዳን የፍቅር ምንጭ ነው። ለእኛ ሲል የተወለደው ኢየሱስ እንዲረዳን እና እነዚህ ሁለት ማለትም አብን ማመን እና ባልንጀራን መውደድ የሚሉ የማይነጣጠሉ ባሕሪያትን እንድንላበስ እንዲረዳን ልንጠይቀው ይገባል፣ ምክንያቱም እነዚህ ሁለት ባሕሪያት ሕይወታችንን የሚቀይሩ እና ሕይወታችን የበልጡኑ ያማረ እና ፍሬያማ እንዲሆን ስለሚያደርጉት ነው።

የአዳኛችን እናት የሰማዕታት ሁሉ ንግሥት ለሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጸሎታችንን እናቅርብ፣ ምክንያቱም ኢየሱስ የሕይወታችን ጌታ መሆንን እንድንቀበል እና በጥንካሬ የተሞላን የእርሱ መስካሪዎች እንድንሆን፣ ቅዱስ ወንጌልን በታማኝነት በመመስከራችን የተነሳ  የሚደርስብብን መከራ በጥንካሬ መጋፈጥ እንችል ዘንድ ስለምትረዳን ነው።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.