2017-12-27 14:46:00

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በድምቀት ተከበረ


የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በታኅሳስ 15/2010 ዓ.ም. በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5:30 ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመሩት እና በርካታ ካህናት ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ በመስዋዕተ ቅዳሴ ተክብሮ ማለፉ ተገልጹዋል። በእለቱ ቅዱስነታቸው በእርሳቸው መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ማሪያም “የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው” የሚለውን በሉቃስ ወንጌል በ2:7 ላይ የተጠቀሰውን በማስታወስ ስብከታቸውን የጀመሩ ሲሆን ወንጌላዊው ሉቃስ በቃሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የዓለም ብርሃን የሆነውን ልጇን መውለዱዋን ግልጽ በሆነ መልኩ አስቀምጦልናል ብለዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእለቱ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደው ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

ማሪያምየበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው በእነዚህ ወጥ እና ግልጽ በሆኑ ቃላት አማክይነት ወንጌላዊው ሉቃስ ወደ እዚያ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ኢየሱስን የወለደችበት ቅዱስ ወደ ሆነው ምሽት የእኛን ልብ በመውሰድ የዓለምን ብርሀን የሆነውን ኢየሱስ ለእኛ እንደ ሰጠች በዚህም አጋጣሚ እስከ መጨረሻ እለታችን ድረስ ታሪካችንን የሚቀይር ክስተት ውስጥ እኛን እንዳስገባችን ቀለል ባለ መልኩ የሚትርክ ታሪክ ነው። በዚያ ምሽት የተፈጠረው ነገር ሁሉ የተስፋችን ሥር መሰረት ሆነ።

እስቲ ትንሽ ወደኃላ እንመለስ። ንጉሡ ባስነገረው አዋጅ መሰረት ማርያምና ዮሴፍ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ተገደዋል። ሕዛባቸውን፣ ቤታቸውን እና መሬታቸውንም ሳይቀር ትተው በመሄድ ይህንን አስገዳጅ የሆነ አዋጅ ማለትም የሕዝብ ቆጠራ ለመተግበር እና ለመቆጠር ይሄዳሉ። ይህም አዲስ እና ወጣት ለሆኑ ባለትዳሮችና በተለይም ደግሞ እርሷ የመውለጃዋ ጊዜ በመቃረቡ የተነሳ የሚደረግ ጉዞ በመሆኑ  ቀላል ወይም ምቹ የሚባል ጉዞ አይደለም፣ ሀገራቸውን የግድ መልቀቅ ነበረባቸው። ልባቸው ግን በተስፋ እና በጉጉት ተሞልቶ የነበረ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት ልጃቸው ሊወለድ በመድረሱ የተነሳ ነው። ይሁን እንጂ መኖሪያቸውን ለቀው መሄድ ስለነበረባቸው ይህም ሁኔታ አለመረጋጋቶችና አደጋዎችን በመደቀኑ የተነሳሳ ያስጨነቃቸው ጉዳይ ነበረ።

በእዚያም በጣም አስቸጋሪ የሆነ ነገር ልገጥሟቸው እንደሚችል ተሰማቸው። ወደ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ ይቺ ከተማ ለእነርሱ የማትሆን እና ያልጠበቁት ሀገር መሆኑን መገነዘብ ጀመሩ፣ ለእነርሱ የሚሆን ምንም ቦታ አልነበራቸውምና።

ሁሉም ነገር አስቸጋሪ ነበር። ማሪያምም አማኑሄልን በዚሁ ሁኔታ ወለደች።  የእግዚአብሔር ልጅ በከብቶች ጋጣ ውስጥ የተወለደው የሚኖርበት የራሱ የሆነ ቦታ ስለሌለው ነው።ወደ ራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም” (ዩሐንስ 1:11)

በዚያም ጨለማ በሆነ ከተማ ውስጥ፣ ከሩቅ ሀገር ለሚመጡ እንግዶች የሚሆን ስፍራ አልነበረም፣ ጨለማ በተንሰራፋበት ከተማ ውስጥ፣ በጨለማ የተዋጠች ከተማ፣ በዛን ጊዜ በሌሎች ላይ ጀርባዋን በማዞር እና ሌሎችን ችላ በማለት እራሷን ብቻ ማደላደል የምትፈልግ ከተማ ትመስላለች ... በትክክልም እንዲሁ ነበር የሆነው። የእግዚአብሄር ፍቅር በዚያ ጨለማ ውስጥ ቅጽበታዊ በሆነ መልኩ ይህንን ሁኔታ በሚቀይር መልኩ ቦግ ብሎ በራ።

በቤተልሔም ሀግራቸውን፣ ሀብታቸውን፣ ሕልሞቻቸውን ትተው ለመጡ ሰዎች ትንሽ የመቆያ ሥፍራ ተከፈተላቸው። ሌላው ቀርቶ የዚያች ከተማ የባለቤትነት ስሜት ለሚሰማቸው እና በዚያም ለሚኖሩ ሰዎች ሳይቀር ተጨባጭ በሆነ መልኩ አስፈሪ ሁኔታን ፈጠረ።

ሌሎች በርካታ ተመሳሳይ የሆኑ ሁኔታዎች በዮሴፍና በማሪያም ፈለግ ወይም ታሪክ ውስጥ ተከስተዋል። አስገዳጅ በሆነ መልኩ ከየሀገራቸው የሚፈናቀሉ ቤተሰቦች በዛሬው እኛ ባለንበት ዘመን እየተመለከትነው የሚገኝ ሐቅ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከእናት ሀገራቸው በፍቅዳቸው ሳይሆን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ተገደው ሲሰደዱ እናያለን፣ ይህን በተመለከተ በርካታ የሆኑ አጋጣሚዎችን እናያለን፣ ሰዎች በተስፋ፣ የወደፊት ኑሮዋቸውን በማሰብ ወዳጅ ዘመዶቻችውን ትተው ሲሰደዱ እናያለን። በብዙ አጋጥሚዎች ይህ ስደታቸው በተፋ የተሞላ ነው፣ ይህም ተስፋ ለወደፊቱ ጉዞዋቸው ስንቅ ሆኖላቸው ነበረ።   ሌሎች በርካታ ሰዎች ግን ይህ ስደት አንድ መጠሪያ ስም ብቻ አለው፣ ይህም ሕልውና የሚለው ነው።  ስልጣንን ለመጫን እና ሀብታቸውን ለማጨድ ብቻ የሚትጉ ግዞትን በማፋፋም የንጹሃንን ደም ማፍሰስ ምንም ደንታ የማይሰጣቸው ብዙ ሰዎች አሉ።

ምንም ቦታ ያልነበራቸው ማሪያም እና ዮሴፍ ዛሬ እኛ የዜግነት ሰነድ የሌለን ሰዎች ተምሳሌት የተጎናጸፉ የመጀመሪዎቹ ሰዎች ናቸው። የእርሱ ድህነትና ትሕትና የሚያተኩረው እና የሚያሳየው፣ የደከሙትን እና ደካሞችን በማክበር እና በመደገፍ እውነተኛው ኃይል እና እውነተኛ ነፃነት ያሳያሉ።

በዚያ ምሽት ለመወለድ ምንም ቦታ የሌለው ሰው በከተማው ጎዳናዎች ለሚኖሩ ሰዎች ተሰብኳል። ይህ የምሥራች ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከው ደግሞ ለእረኞች ነው። በሥራቸው ባሕሪ ምክንያት ከማኅበረሰቡ ውጪ ለመኖር ተገደው ነበር።  የኑሮ ሁኔታቸው እና የሚኖሩበት ስፍራ ሳይቀር በሃይማኖታዊ የመንፃት ስርዓቶች በሚሰቱበት ስፍራ እና መንፈሳዊ ተግባሮች ከሚከናውኑባቸው ስፍራዎችም ሳይቀር መግባት እንድዳይችሉ እገዳ ተጥሎባቸው ነበር። በዚህም ምክንያት እንደ ርኩስ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር። ቆዳቸው፣ ልብሳቸው፣ ሽታቸውም የአነጋገራቸውም ሁኔታን ሳይቀር መነሻ በማድረግ እነርሱ ያላቸው እነዚህ ባሕሪያት በሙሉ አለመተማመንን አስከትሉዋል። እረኞቹ የተገለሉ  በርከት ያሉ ወንድ እና ሴቶችም ነበሩበት። በአማኞች መካከል የሚገኙ አረማዊያን፣ በቅዱስና መካከል የሚኖሩ ኃጢያን፣ በዜጎች መኃል ያሉ መጤዎች ተደርገው ይቆጠሩም ነበር። በአንሩ ግን አረማዊነት፣ ኃጢያተኛነት፣ እና የባእድ ስሜት ለሚሰማቸው ለእነዚሁ እረኞች መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፤አትፍሩ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች አምጥቼላችኋለሁና።  ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነውበማለት ለመጀመሪያ ጊዜ አበሰራቸው።

ዛሬ ማታ እንድንካፈል የተጠራነው ደስታ ይህ ነው። እንድናከብረው እና ለማወጅ የተጠራነው ይህንን ደስታ ነው። እግዚአብሔር በቸርነቱ እና ምህረቱ እኛ አረማዊያንን፣ ኃጢአተኞችን እና የባእድ ሀገር ሰዎችን  ያቀፈበት ደስታ ነው፣  እኛም ተመሳሳይ ነገር እንድናደርግ ይለምናል።

በዚህ ምሽት የምናውጀው እምነት እርሱ በሌለበት መስሎ በሚታዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ  እግዚአብሔር እንደሚገኝ ያረጋግጥልናል። እምብዛም የማይታወቅ፣ በከተማዎቻችን እና በአካባቢያችን የሚጓዙ እና በየበሩ ላይ በመቀመጥ በምንገላቱ ስደተኞችም መኃል እርሱ ይገኛል።

ይህ ተመሳሳይ እምነት ለአዲሶቹ ማህበራዊ ራዕይ ቦታ እንድንሰጥ ያነሳሳናል። እናም በዚህ አዲስ ምድር ላይ ምንም ቦታ እንደሌላቸው ሆኖ እንዲሰማቸው የማይፈልጉ አዳዲስ ተግዳሮችን  ለመጋፈጥ መፍራት የለብንም። የገና በዓል የበጎነትን ኃይል ወደ በጎ አድራጊ ኃይል ለማሸጋገር፣ ለአዳዲስ የበጎ አድራጎት ፈጠራ ኃይል መብቃት ማለት ነው። በጎ አድራጊነት ተፈጥሮአዊ  ነገር ነው።

በቤተልሔም በስጦታ መልክ በተሰጠን ሕጻን ልጅ ተነሳስተን እኛን ከተጠናወተን የግድየለሽነት መነፈስ መጥተን   መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች ዓይኖቻችንን እንዲንከፍት ይረዳናል። የርኃራኄ ስሜታችን ያነቃቅልናል። ወደ ከተማዎቻችን፣ ወደ በሮቻችን ወደ ሕይወታችን  ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ የተቻለንን እንድናደርግ ጥሪ ያቀርብልናል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.