2017-12-27 13:14:00

የቅድስና ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር የቅዱሳት ትሩፋት እውነተኛነቱን እና እቃቤውንም ጭምር የሚመለከት አዲስ መመሪያ አጸደቀ


የቅድስና ጉዳይ ተንክባካቢ ቅዱስ ማኅበር፥ የቅዱሳት ትሩፋት እውነተኛነት የማጣራት ሂደት የሚመለከት እና እቃውቤውንም ጭምር የሚያስገነዝብ አዲስ መመሪያ አዘል ሰነድ ማወጣቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ይኽ ቅዱሳት ትሩፋት በቤተ ክርስቲያን፡ እውነተኛነት እና ዕቃቤ” በሚል ርእስ ሥር የቅዱስና ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ያወጣው አዲስ መመሪያ በማስመልከት በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በምትገኘው ስተውበንቪል ከተማ ባለው በፍራንቸስካውያን መንበረ ጥበብ የቲዮሎጊያ ድኅረ ምረቃ የሚከታተለው ቢሮ አስተዳዳሪ የሥርወ ወይንም የቀኖናዊ እና የሥሩዕ ቲዮሎጊያ መምህር የቲዮሎጊያ ሊቅ ፕሮፈሰር ሚካኤል ሲሪላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሂዱት ቃለ ምልልስ፥

ይኽ የቅዱስና ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በቅርቡ የቅዱስት አጽም እና ቅዱሳት ትሩፋት አያያዝና እንክብካቤ ዙሪያ ይፋ ያደረገው አዲስ መመሪያ የቅዱሳት ትሩፋ እውነተኛነቱን ለይቶ ለማወቅ የሚደረገው የማጣራት ሂደት ሊከተለው የሚገባው ያሠራር እና የምርምሩ ሂደት በትክክል በማስቀመጥ፡ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አንድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ከዛም ብፁዕ በመጨረሻም ቅዱስ ብላ ለማወጅ ክምትከተለው ጥልቅ የምርምር ጥናት ጋር በተስተካከለ ደረጃ ቅዱሳት ትሩፋት እውነትኛን ለመለየት ከዛም ቅዱሳት ትሩፋቶችን ያከባበር እና የመንከባከቡ ጉዳይ እንዴት  መሆን እንዳለበት የሚያመላክት ሰነድ መሆኑ ገልጠው፡ ስለዚህ ቅዱሳት ትሩፋቶች እና ቅዱሳት አጽም ሁሉ እውነተኛነታቸውን በስነ ምርምር በተደገፈ አሠራር ጭምር መለየት ያስፈልጋል።

ቅዱሳት ትሩፋት የእግዚአብሔር አሳቢነት የሚያረጋግጥ ጸጋ ወይንም ስጦታ ነው። ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት እና በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከጥንት ጀምሮ ማእክላዊ ሥፍራ አለው። የቅዱሳት ቅዱስ አጽም እና ቅዱሳት ትሩፋት ክብርና አክብሮት እንሰጣለን ከዚህ አንጻር እውነተኛነቱን በጥናቃቄ ለይቶ በማወቅ ተገቢ እንክብካቤ ምስጠት ለቤተ ክርስቲያን እና ለምእመናን ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ ግልጽ ነው።

የቅዱስና ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ያወጣው አዲስ መመሪያ፥ የቅዱስት ትሩፋት እወነተኛነታቸውን ለይቶ ለማቀብ የሚደረገው አሠራር በጣም ጥናቄ እና የተገባ ምርምር የሚያሻው ነው።  እውነተኛነቱ ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ተገቢ እቃቤ መስጠት እንደሚገባ የሚያመላክት ግልጽ እና አዳዲስ ሃሳቦችን ያካተተ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳት ትሩፋቶች ዙሪይ ሊከሰቱ የሚችሉትን አወዛጋቢ ጥያቄዎች እና የቅዱሳት ትሩፋት ያልሆነውን ሁሉ ቅዱስ ትሩፋት ነው የሚለው የተሳሳተ እማኔ እንዳይኖር ለማድረግ የሚያበቃ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። 
All the contents on this site are copyrighted ©.