2017-12-21 09:08:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በታኅሳስ 08/2010 ዓ.ም. በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ያደርገቱን አስተንትኖ


ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በታኅሳስ 08/2010 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርገቱን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ባለፉት ሳምንታት የሰንበት ቀናት በስርዓተ አምልኮአችን ወቅት ነቅቶ መጠበቅ የሚለው ባሕርህ ምን ማለት እንደ ሆነ እና  የጌታን መንገድ በትክክል ማዘጋጀት ምን ማለት እንደ ሆነም ጭምር በአጽኖት ገልጾልናል። በዛሬው በሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት (የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የምህራባዊያን የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት የስርዓተ አምልኮ ደንብ እና አቆጣጠር መሰረት ማለታቸው ነው) በዛሬውየደስታ ሰነበትበመባል በሚታወቀው በሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት ደግሞ ደስታን በምልአት እንድንቀበል የሚያደርገንን መፈስ ቅዱስን እንድንቀበል ይጋብዘናል። በዛሬው ቀን ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሦስት ባሕሪያትን በመከተል የጌታን መምጣት እንድናዘጋጅ ይጋብዘናል። (. ሐዋሪያው ጳውሎስ 1ተሰሎንቄ 516-24) ይህንን በሚገባ አዳምጡ፣ ሦስት ባሕሪያት አሉ።  “ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁየሚለው የመጀመሪያው ባሕሪ ሲሆንሳታቋርጡ ጸልዩየሚለው ደግሞ ሁለተኛው፤ “በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑአመስግኑ የሚለው ደግሞ ሦስተኛው ባሕሪ ነው። ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ።

የመጀመሪያውን ባሕሪ ስንመለክትሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁየሚለውን እናገኛለን። ሁል ጊዜ ድስ ይበላችሁ በማለት ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ያሳስበናል። ይህም ምንም እንኳን አድንድ አድን ጊዜ ነገሮች እኛ እንዳስብናቸው እና እና ባቀድነው መሰረት የማይሄዱ ቢሆንም እንኳን ደስተኞች ልንሆን ይገባል እንደ ማለት ነው። በዚህ ረገድ ጥልቅ የሆነ ደስታ አለ፣ ይህም ሰላማችን ነው ማለት ነው። ይህም የውስጥ ደስታ ነው። ሰላም የደስታ ምንጭ ነው፣ በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ መከራዎች እና ስቃዮችን እናሳልፋለን፣ ይህንንም ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው። በዙሪያችን ያለው እውነታን ስንመለከት ልክ የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንደሚያስታውሰን እና መጥምቁ ዮሐንስ የተናገረለት ምድረበዳ ባዶ ዓይነት በመሆን ብዙ ጊዜ የማይረባ እና ደረቅ ይመስላል (የዩሐንስ ወንጌል 123)  ነገር ግን የመጥምቁ ዩሐንስ ቃላቶች እንደሚያሳዩት ይህ ምድረ በዳ ሰዎች የሚኖሩባት መሆኑን በእርግጠኝነት እንድንቀበል ያደርገናል፣ እናንተ የማታውቁት ግን በመካከላችሁ ቆሟል በማለት ይናገራል። ይህም ነቢዩ ኢሳያስ እንዳለው ሰለሚመጣው የአብ መልእክተኛ ስለሆነው ስለ እየሱስየጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ለድኾች የምሥራች እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛል። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል፤ የተወደደውን የእግዚአብሔርን ዓመት፣ የአምላካችንንም የበቀል ቀን እንዳውጅ፣ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል” (ኢሳያስ 61:1-2) በማለት ይናገራል። እነዚህንም ቃላት ኢየሱስ በናዝሬት በሙክራብ ውስጥ በነበረበት ወቅት በተመሳሳይ መልኩ ተናግሮዋቸው ነበር (በሉቃስ 416-19) ላይ እንደ ተጠቀሰው። ይህም የኢየሱስ ምድራዊ ተልእኮው ከኃጢኣት ነጻ ለማውጣት እና በግላችን ወይም ደግሞ የማኅበራዊ ሕይወታችን ከፈጠረው የባርነት ቀንበር ነጻ ሊያወጣን እንደ መጣ ያስያል። እርሱ ወደ እዚህ ምድር የመጣው የሰው ልጆች የተገፈፉትን የእግዚኣብሔር ልጅ የመሆን መብታቸውን እና ነጻነታቸውን መልሰው እንዲጎናጸፉ ለማድረግ እርሱ ቢቻ ሊያጎናጽፈን የሚችለውን ደስታ ለመስጠት ጭምር ነው የሚመጣው።

መሲሁ እስኪ መጣ መጠበቅ የሚኖረው ደስታ የሚመነጨው በታማኝነት በሚደረግ ጸሎት ላይ የተመሰረተ ነው ይህም ሁለተኛው ባሕሪ ነው። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስሳታቋርጡ ጸልዩይለናል። በጸሎት አማካኝነት ከእውነተኛ ደስታ ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ወደተጠበቀ ግንኙነት መግባት እንችላለን። የክርስቲያን ደስታ አይገዛም፣ በፍጹም ሊገዛ አይችልም። ደስታ ሊመጣ የሚችለው የደስታችን ምክንያት ከሆነ እምነትና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከተገናኘን ብቻ ነው። በተጨማሪ በክርስቶስ ውስጥ ሥር መዘርጋት ስንጀምር እና ይበልጡኑ ለእርሱ ቅርብ እየሆንን እንሄዳለን፣ ምንም እንኳን በእየለቱ ሕይወታችን በግጭቶች መካከል የሚያልፍ ቢሆንም እንኳን ውስጣዊ እርካታን እናገኛለን። በዚህ ምክንያት አንድ ክርስትያን ኢየሱስን ከተገናኘ በኋላ በአደጋ ላይ ወይም ውስጥ የሚገኝ ነብይ መስሎት ሊሰማው አይችልም። ነገር ግን ከሌሎች ጋር ሊካፈለው የሚችል ደስታ ይኖረዋል፣ ይህም ደስታ ወደ ሌሎች በመዛመት የሕይወት ጎዞ እንዳይዳከም ያደርጋል።

ሦስተኛው በቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ የተገለጸው ባሕሪበማናቸውም ሁኔታ አመስግኑየሚለው ሲሆን ይህም ለእግዚአብሔር ማሳየት የሚገባንን በምስጋና የተሞላ ፍቅር የሚያሳይ ነው። እርሱ ለእኛ በጣም መልካም ነው፣ እኛም በአንጻሩም እርሱ እያደረገልን የሚገኘውን መልካም ነገሮች ለምሳሌም መሐሪ የሆነውን ፍቅሩን፣ ለእኛ የሚያሳየውን ትዕግስት እና መልካምነት በመረዳት ለእርሱ ምስጋና ማቅረብ እንደ ሚገባን እንድናውቅ ተጠርተናል።

ደስታ፣ ጸሎት እና ምስጋና መጭውን የገና በዓል በሚገባ ለማክበር እንድንችል የሚረዱን ስባሕሪያት ናቸው። ደስታ፣ ጸሎት እና ምስጋና እነዚህ ሦስቱ ነገሮች በጣም አስፈላጊዎች ናቸው። እስቲ ሁላችሁ ከእኔ ጋር ደስታ፣ ጸሎት እና ምስጋና የሚሉትን ቃላት አብራችሁ በሉ። በዚህ በሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት እነዚህን ነገሮች ሁሉ በተግባር ላይ ማዋል እንችል ዘንድ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማሪያምን የእናትነት አማላጅነቱዋን እንማጸናለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምየደስታችን ሁሉ ምንጭ ናት ይህም የሆነበት ምክንያት የኢየሱስ ወላጅ እናት ስለሆነች ብቻ ሳይሆን ሁሌም በቀጣይነት ወደ እርሱ ስለምትመራን ነው። 

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስነታቸው በእለቱ የአውሮፓዋዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የላቲን ስርዓተ አምልኮ ተከታይ በሆኑ ክርስቲያኖች ዘንድ በተከበረው ሦስተኛው የስብከተ ገና ሣምንትን ምክንያት በማድረግ በእለቱ በተነበቡት የእግዚኣብሔር ቃል ላይ አስተንትኖን ካደረጉ ቡኃላ  ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በቅድሚያ በእለቱ እርሳቸው 81ኛ የልደት ቀናቸውን አክብረው የነበረ ሲሆን በዚህ ይህንን የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው በእለቱ የእግዚኣብሔር ቃል ላይ የሚያደርጉትን አስተንትኖ ለመከታተል የተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች “እናኳን ለልደት በዓል በሰላም አደረሶት” የሚለውን ዝማሬ በጋራ አሰምተው የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸውም በእለቱ ያስተላለፉትን መልእክት የጀመሩት ሕዝቡ ይህንን “እናኳን አደረሶት” የሚለውን ዝማሬ በመቅረቡ መደሰታቸውን በመግለጽ እና ለዚህም ምስጋናቸውን በማቅረብ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

በመቀጠልም በቅርቡ ከአንድ ወር በፊት በናይጄሪያ ኢጎሪያኪ በሚባል ስፍራ ይኖሩ የነበሩ 6 መናንያን ባልታወቁ ሰዎች ምክንያት ታግተው መወሰዳቸው የሚታወቅ ሲሆን በናይጄሪያ የሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት እነዚህ ከገዳማቸው በአስገዳጅ ሁኔታ ታፍነው የተወሰዱ እንስት ገዳማዊያት እንዲለቀቁ ያስተላለፉትን መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ሚደግፉት የገለጹ ሲሆን በዚህም ሂደት ውስጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነቷ ይታከልበት ዘንድ “ጸጋ የሞላሽ ማሪያም ሆይ” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ደግመዋል። ቅዱስነታቸው በመቀጠል በዚያ የነበሩ ምዕመናን አመስግነው፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጸሎቶች መካከል ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን መላኩ ገብሬል ማሪያምን ያበሰረበትን የምስራች ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደግሙ ቡኃላ ቡራኬን ሰጥተው እና መልካሙን ሁሉ ለምዕመናን ተመኝተው መሰናበታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.