2017-12-21 08:24:00

"የመስዋዕተ ቅዳሴ ስርዓተ አምልኮ በዋነኛነት ሁለት መሰረታዊ የሆኑ ክፍሎችን ያካተተ ነው" ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተላዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚሁ መርሃግብር አንዱ አካል በሆነው በዛሬው እለት ማለትም በታኅሳስ 11/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ቀደም ሲል ባለፉት ሳምንታት በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ስያደርጉት የነበረ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የመስዋዕተ ቅዳሴ ስርዓተ አምልኮ በዋነኛነት ሁለት ዋና ዋና መሰረታዊ  ነገሮችን አጠቃሎ የያዘ እንደ ሆነ ገለጸው እነዚህም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተወስዶ የሚነበበው የእግዚኣብሔር ቃል እና የቅዱስ ቁርባን መስዋዕት መሆናቸውን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳማጥ ትችላላችሁ!

 ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ያደረጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ ወደ ቅዱስ ቁርባን ልብ መግባት እፈልጋለሁ። መስዋዕተ ቅዳሴ ሁለት ዋና ዋና መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች አጠቃሎ የያዘ ነው፣ እነዚህም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተወስዶ የሚነበበው የእግዚኣብሔር ቃል እና የቅዱስ ቁርባን መስዋዕት ናቸው። እነዚህንም ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን አንድ አድርጎ በማጣመር አንድ ወጥ የሆነ ስርዓተ አምልኮን ይፈጥራል። በአንዳንድ የመዘጋጃ ሥነ ሥርዓቶች ይጀመርና በሌሎች መደምደሚያዎች ይጠቃለል፣ ይህም ስርዓተ አምልኮ  ሊነጣጠል ባማይችል መልኩ አንድ አካል ይሆናል፣ ይህንንም በተሻለ መልኩ ለመረዳት ያስችለን ዘንድ በዚሁ የመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት የሚደረጉትን እያንዳንዱን ወቅቶችን ለመግለጽ እሞክራለሁ። መስዋዕተ ቅዳሴን በምልአት ለመኖር እንድንችል እና በውስጡ የሚገኙትን ውብ የሆኑ ነገሮች በሚገባ ማጣጣም እንችል ዘንድ እነዚህን በውስጡ የሚገኙትን ምልክቶች በሚገባ ለመረዳ ያስፈልጋል።

ምዕመናን ከተሰበሰቡ ቡኃላ መስዋዕተ ቅዳሴው በመጊቢያ ስርዓቶች በመስቀል ምልክት ይጀምር እና ሰላምታ ይከተላል ከዚያም የንስሐ ጸሎት ከተደረገ ቡኃላ “ኪሪዬ ኤልዞን” (ጌታ ሆይ ማረን ማለት ነው በአመሪኛ ) የሚለው ጸሎት ከተደገመ ቡኃላ ክቡር ለአምላክ የሚለው ጸሎት ይደገማል ከዚያም የመጊቢያ ጸሎት ይደረጋል። የእነዚህም ጸሎቶች ዋና ግብ “ምዕመናኑ በአንድነት በመሰብሰብ አንድ መኅበር እንዲመሰርቱ፣ በታላቅ እመንት የእግዚኣብሔርን ቃል ማዳመጥ እንዲችሉ እና መስዋዕተ ቅዳሴን በአግባቡ መከታተል እንዲችሉ ለማድረግ ነው።

እንደ ተለመደው የመግቢያ መዝሙር በሚዘመርበት ወቅት ካህኑ ከሌሎች ቧለሟሎቹ እና ዲያቆናት ጋር በመሆን በሁደት ወደ መነበረ ታቦት በመቅረብ የአምልኮ መግለጫ በሆነ መልኩ መነበረታቦቱን አጎንብሶ ከተሳለመ ቡኃላ በእጣን ያጥነዋል። እነዚህ መነፈሳዊ ምልክቶች ብዙ ጊዜ የምንረሳቸው ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ናቸው፣ ምክንያቱም ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻ ወይም እስከ ማብቂያው ድረስ መስዋዕተ ቅዳሴ “በመስቀል ላይ የተሰዋውን ክርስቶስን በመስዋዕትነት በማቅረብ፣ እርሱ መነበረ ታቦታ እንደ ሆነ፣ ለእኛ ሲል የተሰቃዬ እና ካህን መሆኑንም ጭምር በመግለጽ” ከክርስቶስ ፍቅር ጋር የምንገናኝበት ቢስጢር በመሆኑ የተነሳ ነው። በእርግጥ መነበረ ታቦት የክርስቶስ ተምሳሌት በመሆን “የቅዱስ ቁርባን የምስጋና መስዋዕት የማቅረቢያ” መኸከል ነው።

በመቀጠልም የመስቀል ምልክት ይደረጋል። (ይህም ማለት በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በማለት እናማትባለን ማለት ነው)። መስዋዕተ ቅዳሴውን በበላይነት የሚመራው ካህን ይህንን በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በማለት የመስቀል ምልክት በምያማትብበት ወቅት ምዕመናኑም እርሱን በመከተል ይህንኑ የመስቀል ምልክት ያማትባሉ፣ ይህንንም የሚያደርጉት መስዋዕተ ቃዳሴ ምልአት የምኖረው “በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ሲጀመር ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ነው። ሁሉንም ዓይነት ጸሎቶችን ማድረግ የምንጀምረው በቅድስት ስላሴ ስም ነው፣ ይህም በመሀላቸው ዘላለማዊ የሆነ ሕብረት እናዳለ ያሳያል፣ በዚህም ከመጀመሪያ ጊዜ አንስቶ እስከ መጨረሻ ጊዜ ድረስ የእግዚኣብሔር ፍቅር አንድ እና በቅድስት ስላሴ ላይ መሰረቱን ያደረግ እንደ ሆነ በመግለጽ፣ ይህም ፍቅር ለእኛ የተሰጠን በክርስቶስ መስቀል አማካይነት እንደ ሆነ ያሳያል። በእርግጥ የእርሱ የፋሲካ ምስጢር የቅድስት ስላሴ ስጦታ ነው፣ ቅዱስ ቁራባንም ሁል ግዜ የሚመነጨው ከዚሁ ከእርሱ ከተወጋ ልብ ውስጥ ነው።

ስለዚህ በመስቀል ምልክት ራሳችንን በምናማትብበት ጊዜ ምስጢረ ጥምቀት የተቀበልንበትን ቀን የማስታወስን አጋጣሚ ብቻ የሚፈጥርልን ሳይሆን ነገር ግን ያንን የምናቀርበውን ሥነ-መለኮታዊ ጸሎት ለእኛ ሲል በተሰቀለው፣ በመስቀል ላይ በሞተው፣ በክብር ከሙታን በተነሳው በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ነው።

በመቀጠልም ካህኑ "እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን" በማለት ሰላምታን ለምዕመኑ ሲያቀርብ ምዕመኑ ደግሞ “ከመንፈስም ጋር” በማለት ይመልሳል። እስካሁን ያለነው በመስዋዕተ ቅዳሴ የመጊቢያ ስርዓት ላይ በመሆናችን የተነሳ እነዚህ መንፈሳዊ ምልክቶች እና ቃላት ምን ማለት እንደ ፈለጉ መረዳት ይኖርብናል። በዚያ የሚገኙ ተሳታፊዎች መካከል “ስምምነትን” በመፍጠር በአንድ መንፈስ እና በተመሳሳይ መልኩ "ተነሳሽነት" በመፍጠር የሁሉንም የድምፅ ቃላቶች በማዋሃድ መልካም የሆነ ድባብ ከፈጠሩ ቡኃላ የዝምታ ጊዜን ተከትሎ ወደ "ዝምታ" ውስጥ ይከተናል። "በካህኑ ሰላምታ እና የሕዝቡ ምላሽ የቤተክርስቲያን ምሥጢርን ይሰብካሉ"። ስለዚህም በጋራ እምነት እና መሻት ከጌታ ጋር እና ከመላው ማህበረሰብ ጋር አንድነት መኖር መፈለጋችንን ያሳያል።

ይህ የዝምታ ወቅት ወዲያሁኑ ልብን የሚነከ ሁኔታ ይፍጥራል፣ ምክንያቱም ይህንን መስዋዕተ ቃዳሴ የሚመራው ካህን እያንደንዱ ሰው ራሱን እንዲመረምን እና ኃጢኣተኛ መሆኑን እንዲያውቅ ስለሚጋብዝ ነው። ይህም የንስሐ ጸሎት ነው። ይህም የሰራናቸውን ኃጢኣቶች ማሰብ የሚለውን ብቻ የሚወክል ሳይሆን ነገር ግን ከዚህ ዘለል ባለ ሁኔታ የሰራናቸውን ኃጢኣቶች በእግዚኣብሔር ፊት እና በበደልናቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ፊት፣ በትህትና እና በሀቀኝነት መንፈስ ልክ እንደ ትሁቱ ቀራጭ የነበረው ሰው (ሉቃስ 18፡9-14) አጢኣታችንን መናዘዝን ያካትታል። በእርግጥ ቅዱስ ቁርባን የፋሲካ ምስጢራዊ እሴቶችን የያዘ ነው፣ ይህም ማለትም የክርስቶስን ከሞት ወደ ሕይወት መተላለፍ ማለት ነው፣ በመጀመሪያ ማድረግ ያለብን ለእኛ ሞት መንስሄ የሆኑ ነገሮችን ለይተን በማውጣት ከእርሱ ጋር የትንሳኤው ተካፋዮች ሊያደርጉን የሚችሉ ነገሮችን መፍጠር የገባናል ማለት ነው። ይህ የንስሐ ጸሎት ምን ያህል አስፈላጊ እንደ ሆነ እንድንገነዘብ ያደርገናል። ይህንንም የተመለከቱ ጉዳዮችን በሚቀጥለው ሳምንት የትምህርተ ክርስቶስ አስትምሮዋችን በጥልቀት እንመለከታለን።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.