2017-12-18 16:37:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 81ኛው ዓመት ዕድሜያችውን አከበሩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. 81ኛው ዓመተ ልደታቸውን አከበሩ፡ ቅዱስነታቸው የልደት ቀናቸውን ያከበሩት በቅድስት ማርታ የልጆች ጤና ጥበቃ መርጃ ማኅበር የሚረዱት ሕፃናት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ባዘጋጁላቸው የመልካም የልደት ቀን መግለጫ ሥነ ስርዓት በመሳተፍ ሲሆን። በዚህ አጋጣሚም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሳረጉት ጸሎተ መልእከ እግዚኣብሔር የተሳተፉት ከውጭ እና ከውስጥ የመጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በአንድነት እንኳን ለ 81 ዓመት እድሜ አደረስዎት በማለት ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ማስተጋባታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ከመላ ዓለም ለቅዱስነታቸው የተላለፈው የደስታ መግለጫ መልእክት

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ለቅዱስነታቸው የመልካም የትውልድ ቀን መልእክት በማስተላለፍ በመላይቱ በኢጣሊያ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ስም ልባዊ ቅርበታቸውን ጸሎታቸውንም ታማኝነታቸውንም እንዳረጋገጡላቸው ለማወቅ ሲቻል። የኢጣሊያው የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ያስተላለፈው የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት ታዛዥነታቸውን የሚያረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር በኢጣሊያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የዚያ የሚሰገወው ፍቅር ተጨባጭ ምስክር ትሆንም ዘንድ ቅዱስነታቸው በሚያሳርጉት ጸሎት ያላቸው እርግጠኛነት መግለጣቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ያሰራጨው ዜና ያመለክታል።

የረፓብሊካዊት ኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ሰርጆ ማታረ ባስተላለፉት ምልእክት፥ ከልብ የመነጨ ሰላምታ በማቅረብ፡ ምእመናን እና መልካም ፈቃድ ያላቸው ሁሉ የእርሷ ሥልጣናዊ ትምህርት በቅርብ በመከታተል እግብር ላይ ለማዋልም የሚያደርገው ጥረት በኢጣሊያ ሕዝብ ስም ልመሰክርልዎት እወዳለሁ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢጣሊያ የርእሰ ብሔር ሕንጻ የፈጸሙት ይፋዊ ጉብኝት አስታውሰው፡ ይኽ ጉብኝትም በኢጣሊያ እና በአገረ ቫቲካን መካከል ያለው ግኑኝነት ጥልቅ እና አብነታዊ መሆኑን የሚመሰክር ነው ማለታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላም መረጋጋት ወንድማማችነት ፍትሕ እንዲሰፍን በሚያካሂዱት ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉብኝት ሁሉ ድምጽ ለሌለው ድምጽ በመሆን የሚያስተላልፉት ጥሪ ሁሉም በጽናት እና ካለ ምንም ፍርሃት ሰብአዊ ፍጡር ለመቀራረብ ለመደጋገፍ ብሎም ተፈጥሮን ለመንከባከብ የሚያነቃቃ ነው ብለው፡ በሚያደርጉት ግኑኝነት ስለ ሚሰጡት ሕንጸት በኢጣሊያ ሕዝብ ስም ምስጋና በማቅረብ ደግመው እንኳን ለ 81ኛው የልደት ቀን አደረስዎች ማለታቸውንም ይጠቁማል።

ባለፈው ዓመት ቅዱስ አባታችን 80 ዓመታቸው ባከበሩበት ዕለት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ማዕድ ቤት የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመቀበል አብረው ማእድ በመቋደስ እንዳከበሩት የሚታወስ ሲሆን፡ እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. ነሐሴ 17 ቀንም በኢጣሊያ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ሥር ከሚታቀፉት ታዳጊ ወጣቶች ጋር በማክበር፡ ወጣት ትውልድ የጋራ ጥቅም በመሻት ረገድ በምሕረትና በሰላም በመተባበር እና በመተሳሰብ ጎዳና እንዲበረታ አሳስበው እንደነበር ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ 78ኛውን ዓመት ልደታቸው ያከበሩበት ዕለት በረቡዕ ቀን በመዋሉ ምክንያት በዚያኑ ዕለት በሰጡት ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የተሳተፉት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ከውስጥ እና ከውጭ የመጡት ምእመናን ጋር በመሆን ሲያከብሩ ለክብራቸው የዚያች የትውልድ አገራቸው አርጀንቲና መግለጫ የሆነውን የታንጐ ዳንስ ትርኢት እንደቀረበላቸው እና እ.ኤ.አ. ታሕሳስ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. የልደታቸው ቀን በቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ማዕድ ቤት ከጎዳና ተዳዳሪ ወንድሞቻችን ጋር የቍርስ ማእድ በመቋደስ እንዳከበሩትም ያስታውሳል።

ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የልጆች ጤና ጥበቃ መስጫ ማኅበር የሚረዱት በቤተሰቦቻቸው በበጐ አድራጎት አባላት እና በጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች የተሸኙት ክተለያዩ ሃይማኖቶች እና አገሮች የተወጣጡ ሕፃናት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ባዘጋጁላቸው የመልካም የልደት ቀን መግለጫ ሥነ ስርዓት በመሳተፍ ሕፃንቱ ለክብራቸው ያቀረቡላቸ መዝሮች ባህላዊ ሸብሸቦ ከተከታተሉ በኋላ ባሰሙት ንግግር፥

የሕፃናት ደስታ ትልቅ ኃብት ነው

ከሕፃናት ሕይወት እና ፊት ሃሴት እና ፈገግታ እንዳይለይ ሁላችን እንደ የኃላፊነታቸው ልንከላከልላቸው ይገባናል። ልክ እንደ አንድ ለም መሬት የተዘራለትን አባዝቶ እንደሚያፈራ ሁሉ ሕፃናትም ለም መሬት ናቸው። አደራ ምግባረ ክፋት አንዝራባቸው፡ ሁላችን የተወለድንበት ቀን ስናከብር ይኸንን በጥልቅ ማስተዋል ይኖርብናል። አደራ ሕፃናትን የሚያሳዝን የሚያስተክዝ ነገር አንፍጠርባቸው። ሁሌ ሃሴት የሚታይባቸው እንዲሆኑ አደራ ወላጆች በእነሱ ፊት የመከባበር የመተሳሰብ እና የፍቅር መስካሪያ ሆነው እንዲገኙ አደራ፡ ምንም ቢሆን በሕፃናት ፊት ከክፉ ምግባር እንቆጠበት።

ከአያቶቻቸው ጋር እንዲገናኙ እንዲወያዩ አድርጉዋቸው፡ ሕፃናት እና አያቶች በእድሜ ጠርዝ የተራራቁ ናቸው ሆኖም፡ ሕፃናቱ ኢተዘክሮ ሆነው እንዳይቀሩ ከዚያ ተዘክሮ ከሆነው ከኅብረተብ ክፍል ጋር እንዲገናኙ እንዳርግ፡ የእምነት የባህል የሕይወት ገጠመኝ ታሪክ በተመለከተ በእድሜ የገፋው የኅብረተሰብ ክፍል ትልቅ ሃብት ነውና፡ በሕፃናት እና በአዛውንቱ መካከል ግንኙነት እንዲኖር እናዳርግ፡ የአንዲት አገር መጻኢ አለ ተዘክሮ ጨለምተኛ ይሆናል።

ሕፃናቱም ከአያቶቻቸው ጋር መወያየትን ያፍቅሩ። በእድሜ ከገፉት ከኅብረተሰብ አባላት ጋር መወያየትን ውደዱ። እናንተም ወላጆች እና አያቶች እምነትን አስተላልፉላቸው፡ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ከእግዚአብሔር ጋር መወያየትን አስተምሯቸው  አደራ ካሉ በኋላ ሕፃናቱ ላዘጋጁላቸው የመልካም ልደት ቀን መግለጫ ትርኢት አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.