2017-12-18 16:41:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኤኳዶር ርእሰ ብሔር ተቀብለው አነጋገሩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ለይፋው ጉብኝት አገረ ቫቲካን የገቡትን የኤኳዶር ርእሰ ብሔር ለኒን ሞረኖ ጋርሲስን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቅ።

ርእሰ ብሔር ለኒን ቦልታይረ ሞረኖ ግራሰስ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከተሰናበቱ በኋላ፡ በቅድስት መንበር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ በሆኑት በሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፓውል ሪቻርድ ጋላገር ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አመለከተ።

ቤተ ክርስቲያን በኤኳዶር በጤና ጥበቃ በትምህርት ዘርፍ በልማትና በሁለንተናዊ ሰብአዊ እድገት ዘርፍ የምትሰጠው አገልግሎት የተዋጣለት ከመሆኑም ባሻገር ማኅበረሰብ ለተደቀነበት ወቅታውያን ተግዳረቶችን ሁሉ በመጋፈጥ ብሩሕ መጻኢ ለመጫር የሚያስችለው መንገድ በማመላከቱም ረገድ የምትሰጠው አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑ የኤኳዶር ርእሰ ብሔር ገልጠው፡ በኤኳዶር የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለአገር እና ለሕዝብ እድገት የምትሰጠው አስትወጽኦ የሚደነቅ ነው፡ የኤኳዶር ቀደምት ተወላጆች ሰብአዊ መብትና ክብር ባህላቸው እንዲከበር እና ተፈጥሮ በመንከባከብ ረገድ የእያንዳንዱ ዜጋ እና እንደ ማኅበረሰብም የአገሪቱ ዜጋ ያለበትን ኃላፊነት በመጠቆም ለጋራ ጥቅም በጋራ ተግቶ ለመሥራትም ጭምር በቅድስት መንበር እና በኤኳድረ መንግሥት መካከል የሚደረገው ትብብር በበለጠ ከፍ ለማድረግ የሁለቱ አገሮች ፍላጎት መሆኑ በተካሄደው ግኑኝነት መገለጡ የጠቆመው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያይዞ፥ በመጨረሻም አንገብጋቢ በሆኑት ብሔራዊ ክፍል ዓለማዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ ነክ ጉዳዮች ላይ ፍትሕ ሰላም እና የሁሉ እድገት ማነቃቃት በተሰኘው ዝክረ ነገር የሓሳብ ልውውጥ መካሄዱም አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.