2017-12-12 16:31:00

ቅዱስ አባታችን ሰብአዊ መብትና ክብር ከኑክለር ጦር መሣሪያ መፍታት ጋር ጥምረት እንዳለው ገለጡ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት መልአከ እግዚብሔር ደግመው እንዳበቁ፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ክብር ቀን የሚዘከርበት ቀን መሆኑና በዚሁ ዕለትም የ 2017 ዓ.ም. የሰላም ኖበል ሽልማት ብቁ ተብለው ለሚመረጡት ሽልማቱ የሚሰጥበት ዕለት መሆኑ በማሰብ፡ ለዚህ የ 2017 ዓ.ም. የሰላም ኖበል ተሸላሚ እንዲሆን የተመረጠው ዓለም አቀፍ የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ቅነሳ እና እገዳ የተለያዩ ዘመቻ የሚያካሂደው ማኅበር ጠቀሰው፡ የሰብአዊ መብት እና ክብር ዋስትና ከኑክሊየር ጦር መሣሪያ እገዳ ጋር የተጣመረ መሆኑ የሚያስገነዝብ ምርጫ ነው እንዳሉ የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማርኮ ጉወራ አስታወቁ።

የሁሉም ሰብአዊ ፍጡር ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ሁሉም መትጋት ይኖበታ። በተለይ ደግሞ በዚህ በአሁኑ ወቅት ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ለሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ የሚደረገው ጥረት በዓለም የኑክሊየር ጦር መሣሪያ እንዲወገድ በሚደረገው ጥረት ሊደገፍ ይገባዋል።

የጋራ ቤታችን የሆነውን ተፈጥሮ ለመገንባት እግዚአብሔር የእርስ በእርስ መተባበር ብቃት አድሎናል። ነጻነት አስተዋይነት የተጸገውን ነን። ለሰላም እና ለሁሉም እውነተኛ እድገት አገልግሎት እንድንተጋ ዕደ ጥበብን ለመቆጣጠር ሰብአዊ ሥልጣናችን ውስንነቱን ለመኖር ብቃቱ የታደልን ነን እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ጉወራ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.