2017-12-12 16:29:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


የስብከተ ገና ጊዜያት ያንን በሕይወታችን ካለ መለዘብ ምክንያት ትዕቢት የሚያኖርብን አባጣ እና ጎርባጣው፡ ጠማማውን በውስጣችን የሚፈጥረው ባዶነት ሁሉ ለይተን በማወቅው ለሚመጣው ኢየሱስ ቦታውን የምናመቻችለት ወቅት ነው  ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. እኩለ ቀን ከውስጥ እና ከውጭ የመጡት ምእመና በተሰበሰቡበት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከሐዋርያዊ መስኮት ሆነው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ በላቲን የሊጡርጊያ ባሕረ ሐሳብ መሰረት ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 1 ከቁጥር 1-8 የተወሰደውን ምንባብ አስደግፈው ሲሆን፡ በዚህ ሁለተኛው እሁድ የስብከተ ገና በአንደኛው ምንባብ ነቢይ ኢሳያስ (ምዕ. 40, 1-5፤ 9-11)፡ ሕዝቡን ከግዞት ነጻ ተላቆ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለስ ያበስራል። ይኸንን ነጻነት ለመቀዳጀት፥ ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት የልቡን ባዶነት እና ኃጢኣቱንም ሊታመንና ሊናዘዝ እንደሚገባው ያሳስባል።

አለ መጸለያችን ወይንም ደግሞ ብዙ ካለ መጸለያችን በሕይወታችን የሚከሰት ባዶነት፡ በዚህ በምጽአት ጊዜ በጸሎት እጅግ በተጋጋለ መንፈስ ተበራተን፡ ለመንፈሳዊ ሕይወት ትልቅ ስፍራ በመስጠት፡ ባለንጀራንን  በተለይ ደግሞ እጅግ በድኽነት ለተጎሳቆለው ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ድጋፍ ለሚያሻው ወንድማችንን እንደሚገባው ካለ ማፍቀራችን የሚፍጥርብን ባዶነት የምጽአት ወቅት ሌሎች ለሚያፈልጋቸው ነገር ሁሉ ትኵረት እንዲኖረን የሚያነቃቃን ወቅት በመሆኑ በዚህ ፍቅር በመትጋት ባዶነቱን እንዲወገድ ለማድረግ ለመልካም ተግባር የምንነቃቃበት ወቅት ነው፡ ይኽ ደግሞ ልክ እንደ ዮሐንስ መጥመቅ፡ በዚህ በምጽአት ወቅት በዚያ በብዙዎች ምድረ በዳ በሆነው በደነደነው ልብ ውስጥ የተስፋን መንገድ የምናቀናበት ጊዜ ነው።

ነቢይ ኢሳያስ ይላሉ ቅዱስ አባታችን፡ ትዕቢታችንን እኔ ባይነታችንን ሁሉ እንፈታ ዘንድ ያሳስበናል። ትዕቢት እኔነት ባለበት ልብ ውስጥ ጌታ ሊገባ አይችልም። ምክንያቱም ይኽ ዓይነቱ ልብ በትዕቢት እና በእኔነት ተሞልቷልና። ስለዚህ ዝቅ ማለት ይገባና። ገራገሮች ትሁታን ሆነን መጮኽ ሳይሆን ማዳመጥ ይገባናል። ለዘብ ብሎ መናገር ያስፈልጋ፡ እንዲህ ባለ ጸባይ ልዝብ እና ትሑት ለሆነው ጌታ መምጣት እራስን ማሰናዳት ነው፥ ያሉት ቅዱስ አባታችን በማስከተል ከሚመጣው ጌታ ጋር ሱታፌ እንዳይኖረን የሚያግደን ሁሉ መቅረፍ ይኖርብናል። ይኸንን በደስታ መከወን ማለት ደግሞ ለሚመጣው ጌታ እራስን ማዘጋጀት ይሆናል።

በአንድ ወዳጃችን መጎብኘትን ስንጠባበቅ ልባችንን በሃሴት እናሰናዳለን። በተመሳሳይ መልኩም ለሚመጣው ጌታ በደስታ ልባችንን እናሰናዳ። ጎዶሎነትችንን በጸጋው እንዲሞላው ታምነን ዕለት በዕለት ተግተን እንጠባበቀው።

የምንጠባበቀው መድኅን በልባችን ውስጥ ያንን የመንጻት የአዲስ ሕይወት እና የነጻነት ምንጭ የሆነውን የእግዝአብሔር ፍቅር ያፈሳል፡ ብለው የለገሱት አስተንትኖ፥ ቅድስት ድንግል ማርያም ለክርስቶስ መምጣት ሁለመናዊ ኑረትዋን በዚያ ሕይወቷን በጸጋ በሞላው መንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ ፈቅዳ እንዳሰናዳች ሁሉ እኛም በዚህ ማርያማዊ መንፈስ ለሚመጣው ጌታ እራሳችንን እናሰናዳ ብለው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።
All the contents on this site are copyrighted ©.