2017-12-12 16:44:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ የተፈጥሮ አየር መዛባት በተሳካ ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያበቃ ቆራጥ ውሳኔ ገቢራዊ ማድረግ


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 10 ቀን ቅዱስ አባታቸው ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከዚያ ከብዙ ሺ ምእመና በጋራ በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት መልአለከ እግዚአብሔር ባሳረጉበት ዕለት፡ በፈረንሳይ ርእሰ ከተማ የምንኖበት መሬት በሚል ርእስ ሥር በዚህ ሳምንት ከዚያ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ያካባቢ የአየር ንብረት መዛባት ለመቆጣጠር ርእስ ዙሪያ በመከረው ዓውደ ጉባኤ የተደረሰው የስምምነት ሰነድ ቀጥሎ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ መሆኑ በማስታወስ፡ እየታየ ያለው እጅግ አሳሳቢነ የሆነው የተፈጥሮ አየር መዛባት ለመቆጣጠር እንዲቻል፥ ሁሉም እንዲተጋ እና የተደረሰው የስምምነት የውሳኔ ሰንድ ገቢራዊ ማድረግ እንዲቻል ያለው ኃላፊነት ማደስ ይገባዋል የሚል ጥሪ በማቅረብ፥

ይኽ የሚካሄደው ዓውደ ጉባኤ እና ሌሎች የተፈጥሮ አየር ብከላ ለማስወገድ በተመሳሳይ አቅጣጫ የሚከናወኑት የተለያዩ ጅምሮች ሁሉ በእውነቱ ተገቢ ውጤት እንዲያስገኙ ለማድረግ ከተፈለገ ግልጽ በሆነ መልኩ ስለ ጉዳዩ ኵላዊ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያግዝ ብቻ ሳይሆን ድኽነትን ለመውጋት እና ሁለ መናዊ ሰብአዊ እድገት ለማጎናጸፍ ብሎም ለማነቃቃት የሚያስችል እንዲሆን እማጸናለሁ፡

እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ አስታውቋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.