2017-12-12 16:47:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፡ በኢየሩሳሌም አዳዲስ የዓመጽ ድርጊቶች እንዳይከስቱ ጥሪ አቀረቡ


ቅድስት መንበር በመካከለኛው ምስራቅ በተለይ ደግሞ በዚያች በመላ ዓለም ለሚገኙት ክርስቲያኖች አይሁዶች እና ሙስሊሞች ቅድስት ከተማ በሆነቸው በኢየሩሳሌም ክልል ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እና ሂደቱን በቅርብ እየተከታተለቸው መሆንዋ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ የጠቀሱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ፥ በክልሉ ባለፉት በመጨረሻ ቀናት ውስጥ ተከስቶ ያለው ውጥረት እና ግጭት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅርብ በመከታተል ጥበብ እና አስተዋይነት የተካነው ውሳኔ እና በተለይ ደግሞ የሁሉም አገሮች ኃላፊነት በዚህ እጅግ አስቸጋሪ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ለዚያች እግጅ ለምትሰቃየው አገር ሕዝቦች ሰላም ፍትህና ደህንነት እንዲረጋገጥ የሚያደርግ የጋራ ውሳኔ ለማረጋገጥ እንዲቻል ሁሉም ተግቶ እንዲጸልይ ጥሪ ማቅረባቸው ገልጠዋል።

በክልሉ ተከስቶ ባለው ሁኔታ ዙሪያ ለመወያየት አረብ ሊግ፡ የእስልምና የትብብር ማህበር እናም ሌሎች የተለያዩ ዓለም አቀፍ ማኅበራት አስቸኳይ ስብሰባ እየጠሩ መሆናቸው የጠቀሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅድስት መንበር ቅዱስ አባታችን የሁሉም አቢያተ ክርስቲያን መንፈሳዊ የበላይ ሥልጣን በቅድስት መሬት የክርስቲያን ማኅበረሰብ መንፈሳዊ የበላይ ሥልጣን ጭምር የሚያንጸባርቀው ቅድስት መሬት ህልው ሕጋዊ ሁነት የሚያከብር ውሳኔ እንዲከበር ያቀረቡት ጥሪ ዋቢ በማድረግ፡ ለዚያ ክልል ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችለው በእስራኤልና በፍልስጥኤም መካከል የሚደረገው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠው ሁለቱም ሉአላውያን ጎረቤት አገሮች መልከዓ ምድራዊ ቅዋሜ የሚያመላክተው ውሳኔ ላይ የጸና  የሰላም ስምምንት ብቻ ነው የሚለው ሓሳብ እንዳሰመረበት ጂሶቲ አስታውቋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ትራምፕ እየሩሳሌም የአገረ እስራኤል ርእሰ ከተም ብለው ይፋዊ እውቅና ከሰጡበት ዕለት ጀምሮ በፍልስጥኤም ክልል ተከስቶ ያለው ግጭት አሁኑም እየቀጠለ ሲሆን የፍልስጥኤም የዜና ምንጮች እንደሚያመልክቱትም እስከ አሁን ድረስ ከእስራኤል የመከላከያ ኃይል ጋር እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ አራት ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች 1,250 ደግሞ መቁሰላቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፥ የርእሰ ብሔር ትራምፕ ውሳኔ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ አገሮች እየካሄደ ሲሆን፡ አንሳ የዜና አገልግሎት እንደገለጠውም በሊባኖስ ርእሰ ከተማ በይሩት በሚገኘው በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡከ መንግሥት ሕንፃ አቅራቢያ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄድ የነበረውን ህዝብ ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ መጠቀማቸው ይጠቁማሉ።
All the contents on this site are copyrighted ©.