2017-12-07 17:09:00

55ኛው ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ ጥሪ የጸሎት ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልእክት


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ ጥሪ የጸሎት ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልእክት  በላቲን ሥርዓት አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሠረት የስክበተ ገና  ሳምንታት  መግቢያ የመጀመሪያ እሁድ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ ያደረጉት መልእክት፡ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው እናቀርባለን፡

ውድ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ

እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ወጣቶች ላይ ያተኮረው እርሱም ወጣት እምነት እና ጥሪ በሚል ርእስ ሥር 15ኛው መደበኛው ጠቅላይ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ይካሄዳል። በዚያኑ ወቅት እኛም በሕይወታችን ማእከል የሆነውን እግዚአብሔር ወደ እኛ የሚልበትን እና ይኽ ዘወትር የእግዚአብሔር እቅድ ለወንዶችና ለሴቶች የሚያቀርበው የደስታ ጥሪ በጥልቀት እንመለከታለን (የብፁዓን ጳጳሳት 15ኛው መደበኛው ጠቅላይ ሲኖዶስ፥ ወጣቶች እምነት እና ጥሪን ማስተዋል ሰነድ መግቢያ ተመልከት)።

በዚህ በ 55ኛው ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ ጥሪ የጸሎት ቀን ክንዋኔዎች ሁሉ ባጋጣሚ ወይንም ወጥ ባልሆኑት ሂደቶች ውስጥ የምንገባበት ሳይሆን የእኛ ኅላዌ በዓለም የመለኮታዊ ጥሪ ውጤት መሆኑ የምናስተውልበት ነው።

በዚህ ባለንበት አስጨናቂው ዘመንም ምሥጢረ ሥጋዌ (እግዚአብሔር ሥጋችን ለብሶ ወደ እኛ መምጣት) እግዚአብሔር ዘወትር ሊገናኘን ወደ እኛ የሚመጣ መሆኑ እና እግዚአብሔር በዚያ ረዥም አንዳንዴ አቧራማ በሆነው በሕይወት ጐዳና በእኛ ውስጥ ያለው የፍቅር የደስታ ምኞት (ናፍቆት) በማስተናገድ ወደ ደስታ ሊጠራን ከእኛ ጋር ነው። በዚያ ባለው ስብጥር እና ለእያንዳንዱ በሚሰጠው ልዩ፡ ግላዊ እና ቤተ ክርስቲያናዊ ጥሪ፡ እርሱም የተሰጠንን ጸጋ ፍርያማ እንድናደርግ የሚረዳን በዓለም የድኅነት መሣሪያ ሆነን እንድንገኝ የሚያደርገን ወደ ምሉእ ደስታ የሚመሰርቀን (እንድናቀና የሚመራን)  ከዚያ ከላየ ላይ የሚጠራንን ቃል ማዳመጥ ማስተዋል (ለይቶ መረዳት) እና መኖርን የሚጠይቅ ነው።

እነዚህ ሦስት ገጽታዎች ማለትም ማዳመጥ፤ ማስተዋል እና በሕይወት-መኖር  ለኢየሱስ ተልእኮ ጅማሬ መቃኖች ናቸው። እርሱም በጸሎት ቀናቶች እና በምድረ በዳው ትግል ውስጥ፤ በናዝሬት የሚገኘውን ሙክራብ በመጎብኘት ቃልን ያዳምጣል፤ እግዚአብሔር በኃላፊነት የሰጠውን ተልእከ ይዘት ያስተውላል ይኸ ከአብ የተሰጠው ተልእኮ “ዛሬ” ሊተገብር መምጣቱንም ያበስራል (ሉቃ. 4፡ 16-21 ተመል.)።

ማዳመጥ

የጌታ ጥሪ ልክ በዕለታዊ ተመኮሮዎቻችን እንደሚሆነው ሁሉ ሊሰማን ልናየው እና ልንነካው የሚያበቃን ተጨባጭ ማስረጃ እንደሌለው ከወዲሁ ሊሰመርበት ይገባል። እግዚአብሔር በነፃነታችን ላይ ምንም ጫና ሳያደርግ፡ በጽሞና በጥንቃቄ ወደ እኛ ይመጣል። እንዲህ በመሆኑም የእርሱ ድምጽ በበርካታ ጭንቀቶች እና አዕምሮአችንና ልባችንን በሚያሻቸው ነገሮች ሁሉ ታፍኖ ሊቀር ይችላል።

ስለዚህ ቃል እና ሕይወት በጥልቀት ለማዳመጥ ቅድመ ዝግጅት ያስፈልጋል። ዕለታዊ ሕይወታችንን ተመክሮዎችንን ልናተኩርባቸው እና  ክስተቶችን በእምነት ዓይን ማንበብን መማር እና ለመንፈስ ቅዱስ አግራሞት ክፍት መሆን ይጠይቃል።

በእራሳችን ውስጥ ታጥፈን የተዘጋን ከሆን፡ በዕለታዊ ልማዶቻችን እና  በእራስ ክበት ውስጥ ላይ በማተኮር  ጊዜውን ሌላውን ግድ ባለ መስጠት የሚያባክኑ በመሆን አበይት ነገሮች የማለም አጋጣሚውን የምናጣ ከሆን ለዚያ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖ በዚያ ብቸኛው እና ልዩ በሆነው ታሪክ ዋና ተወናያን እንድንሆን በማድረግ አብሮን ይኸንን ታሪክ ለመጻፍ በመሻት ለሚያቀርብልን ልዩ እና ግላዊ ጥሪ ለማዳመጥ የማይቻላቸው ሆነን እንቀራለ።

ኢየሱስም ተጠርቷ፡ ተልኳልም፡ ለዚህም ነው በጽሞና ልቦናውን ሰብሰብ ለማድርግ ያስፈለግው፡ በሙክራብ ቃሉን አዳምጧል አንብቧልም። በመንፈስ ቅዱስ ብርሃንና ኃይልም ተሞልቶ የገዛ እራሱን ግላዊ ሕይወት እና የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ የሚመለከት መሆኑ የቃሉም ሙላት ትርጉሙን ገልጦታል።

ጫጫታ እና ሁካታ በተሞላባቸው ለግፊቶች፡  እራስን በመስጠት ምክንያት የሚከስተው መዋከብ በሚታይበት  ዕለታዊ ሕይወት፡ የሚያጨናንቁ መረጃዎች  እግጅ በሚታይበት ኅብረተሰብ ውስጥ የተነከርን በመሆናችን ይኽ ዓይነቱ ዝንባሌ መኖር እጅግ ከቀን ወደ ቀን ከባድ እየሆነ መጥቷል። አንዳንዴ ከተሞቻችንን እና መንደሮቻችንን  የሚጫነው  ውጫዊ ሁካታ፡ አልፎ አልፎ የዚያ በውስጣችን ያለው  ቆም በማለት የአስተንትኖ ጣዕም እንዳናጣጥም የሚያደርግ በእርጋታ የሕይወታችን ክስተቶች እና ተግባሮቻችንን እንዳናስተነትን በታማኝ ልበ ግለት እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ዓላማ ለይተን እንዳናውቅ እና ለፍርያማ አስተዋይነት እንዳንተጋ የመበታተን እና የመደናገርን ነጸብራቅ ነው፡

ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት አለ ምንም ጫጫታ እና የሌሎችን ትኩረት በማይስብ መንገድ ይመጣል (ሉቃ. 17. 21 ተመል)። ስለዚህ ልክ እንደ ነቢዩ ኤሊያስ ፍሬውን ለመሰብሰብ እንዲቻል በመንፈሳችን ውስጥ ጠልቆ መግባትን እና ለዚያ ሊጨባጭ በማይቻለው ጽሞና በተካነው ለጥዑን የነፋስ ሽውታ ክፍት እንዲሆን በማረግ ብቻ ነው ለማስተናገድ የሚቻለው (መጽሓፈ ነገስት ቀዳማዊ 19,11-13)፡ 

መለየት (ማስተዋል)

ኢየሱስ በናዝሬቱ ሙክራብ ተገኝቶ ያንን ከነቢይ ኢሳያስ የተወሰደውን፥

“የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሠሩት መፍታትን ለታወሩት ማየትን እንዳውጅና ለተጨቈኑትንም ነፃ እንዳወጣ ልኮኛል። እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያድንበትን የጸጋ ዓመት እንዳስታውቅ ልኮኛል” (ሉቃ. 4, 18-19)።

የሚለውን ቃል በማንበብ፡ የዚያ የተላከበትን ዓላማ ይዘት በማስተዋል ለእነዚያ መሲሕን ይጠባበቁ ለነበሩት ያቀርብላቸዋል።

በተመሳሳይ መልኩም እያንዳንዳችን የራሱን ጥሪ ለይቶ ማወቅ የሚችለው “በዚያ ሰው ከሕይወት ሁኔታ በመጀመር መሠረታዊ ምርጫ የሚያደርግበት ከእግዚአብሔር ጋር የሚወያይበት እና የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ የሚያዳምጥበት በመንፈሳዊ አስተውሎ አማካኝንት ነው” (የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፤ 15ኛው ጠቅላይ መደበኛ ጉባኤ፤ ወጣት እምነትና የጥሪ ልይት, II, 2)።

በተለይ ደግሞ ክርስቲያናዊ ጥሪ ዘወትር ትንቢታዊ ይዘት እንዳለው እንገነዘባለን። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚመሰክረውም ነቢያት በዚያ አበይት ቁሳዊ መንፈሳዊ ግብረ ገባዊ (ሥነ ምግባራዊ) ቀውስ በሚታይበት ሁነት በእግዚአብሔር ስም የመለወጥ የተስፋ እና የማጽናኛ ቃል የሚያደርሱ ናቸው። ልክ አቧራ እንደሚያስነሳው ነፋስ፡ ነቢዩም ያንን የእግዚአብሔርን ቃል የዘነጋው የሐሰት መረጋጋት ላይ ያለውን ህሊና በማወክ ሁነቶችን በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን አማካኝነት በማስተዋል ሕዝብን በዚያ በጨለማው ታሪክ ውስጥ የማለዳ ምልክት የሆነውን የፀሐይ ጀንበር እንዲያይ ያደርጋል።

ዛሬም ቢሆን የርዮተ ዓለም እና የነሲብነትን ፈተናዎችን ለማሸነፍ ከጌታ ጋር በመገናኘት ለጥሪያችን የሚጠቀምባቸው ሥፍራዎች መሣሪያዎች እና ሁነቶችን ለይተን እናስተውል ዘንድ ትንቢቶች ያስፈልጉናል። እያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ማንበብ እና የተልእኮ ቀጣይነቱን የሚያረጋግጥ የት እና ለምን እግዚአብሔር እንደሚጠራው መረዳት የሚያስችለው ብቃት ማሳደግ ያስፈልገዋል።

መኖር

በመጨረሻም ኢየሱስ ያንን የብዙዎችን ተስፈኞች የሚያደርገው ሌሎችን ደግሞ ልባቸው እንዲያደነዱ ሊያደርግ የሚችለውን  የአሁኑ ጊዜ አዲስነቱን ያውጃል። ጊዜው በእርሱ ተፈጽሟል እና እርሱም እሰረኞችን ነፃ ሊያወጣ ለታወሩት ማየትን የሚሰጥ እና ለእያንዳንዱ ፍጥረት የእግዚአብሔር መሐሪውን ፍቅር የሚያበስረው ኢሳያስ ያወጀው መሲሕ ነው።  “እነሆ ይህ አሁን ሲነበብ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” (ሉቃ. 4,20) ሲል ኢየሱስ እራሱ እንዳረጋገጠው ነው።

ያ ከእግዚአብሔር እና ከወንድሞቻችን ጋር እንድንገናኝ ክፍት የሚያደርገን ወንጌላዊ ሃሴት የእኛ ቀስታማነትን እና ስንፍና የሚጠባበቅ አይደለም። የተገባ ምቹ የሆነውን ጊዜና ሰዓት እጠባበቃለሁ በሚል ሰበብ በመስኮት ላይ ብቅ ብለን የምንቀር ከሆን ገና ውስጣችንን አልነካውም ማለት ነው፡ ይኽ ደግሞ አንድ ጥሪ የሚኖረው ሥጋት ሁሉ፡ ዛሬ በኃላፊነት ለመቀበልም ሳንችል እንቀራለን። ዛሬ የክርስቲያን ጥሪ ለህልው ጊዜ ነው! እያንዳንዳችን በዚህች አሁነኛዋ ሰዓት የጌታ መስካሪያን እንድንሆን በሚሥጢረ ተክሊል አማካኝነት ለዓለማዊ ምእመንነት፡ በሚሥጢረ ክህነት፡ ለቅስና አገልግሎት ወይንም ደግሞ ለምንኵስና የመናንያን ሕይወት ጥሪ ተጠርተናል።

በእርግጥ ይኽ “ዛሬ” በኢየሱስ የተበሰረው እግዚአብሔር ሰብኣዊነታችንን ለማዳን እና የተልእኮው ተሳታፊያን ሊያደርገን ወደ እኛ መውረዱን ይቀጥላል። ከእርሱ ጋር እንድንኖር እና እርሱን በመከተል በተለየ ቅርበት ከበሰተ ኋላ በመጓዝ በእርሱ ቀጥተኛው ያገልግሎት ተልእኮ ለማሳተፍ ይጠራል። ሙል በሙሉ እራሳችንን ለመንግሥቱ ለመሰዋት እንደጠራን ካስተዋልን መፍራት የለብንም። በሙላት እና በፍጹም ለእግዚአብሔር እና ወንድሞችን ለማገልግለ እራስን መስጠት መልካም እና አቢይ ጸጋም ነው።

ጌታ ዛሬም እንዲከተሉት ይጠራል። ለጥሪው እነሆኝ እንዳልከው ይሁንልኝ የሚለው ለጋስ መልስ ለመስጠት ፍጽማን እንድሆን መጠበቅ የለብንም፡ ውስንነታችን ኃጢአተኛነታችን ሊያስፈራን አይገባም። ባንጻሩ የጌታን ድምጽ ልብን ከፍቶ መቀበል ነው። በቤተ ክርስቲያን እና በዓለም ግላዊ ተልእኳችን ማዳመጥ፤ ማስተዋል በመጨረሻም እግዚአብሔር በሚሰጠን ዛሬነት ተልእኮውን መኖር።

ያች ሥጋ የለበሰው የእግዚአብሔር ቃል በማዳመጥ እና በመኖር በልቧ ያቀበቸው ዳረኛዋ ልጅ እግር ሴት ቅድስተ ማርያም በጉዞአችን ትሸኘን።

አገረ ቫቲካን እ.ኤ.አ. ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም.

የስክበተ ገና  ሳምንታት የመጀመሪያ እሁድ








All the contents on this site are copyrighted ©.