2017-12-04 14:58:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በስብከታቸው "ስብከት ገና ከክርስቶስ ጋር የምንገናኝበት ወቅት ሊሆን የገባል" ማለታቸው ተገለጸ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከኅዳር 17-23/2010 ዓ.ም. ድረስ በምያንማር እና በባንግላዲሽ ያደረጉትን 21ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን በሰላም እና በተሳካ መልኩ አከናውነው ባለፈው ቅዳሜ ማታ አመሻሹ ላይ ወደ ቫቲካን ተመልሰዋል። ቅዱስነታቸው እንደ ተለመደው በትላንትናው እለት  ማለትም በኅዳር 24/2010 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች  በእለቱ በላቲን ስራዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በትላንትናው እለት በይፋ የተጀመረውን የስብከተ ገና ሳምንት አስመልክተው ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት ስብከት ገና ከክርስቶስ ጋር የምንገናኝበት ወቅት ሊሆን የገባል ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

ክቡራ እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በላቲን የርስዓተ አምልኮ አቆጣጠር መሰረት የተጀመረውን የስብከተ ገና ሳምን አስምለክተው ያደርጉትን ስብከት እንደ ሚከተለው ተርጉመናዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ወደ ገና በዓል የሚደረገውን የስብከተ ገና የደህንነት ጉዞዋችንን ዛሬ ጀምረናል። የስብከተ ጋና ሳምንታት እኛን ለመገናኘት የሚመጣውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመቀበል የምንዘጋጅበት እንዲሁም እግዚኣብሔርን ለመገናኘት ያለንን ፍላጎት የምናረጋግጥበት የወደ ፊቱን ጊዜ በመመልከት ለክርስቶስ ዳግም መምጣት ራሳችንን ለማዘጋጀት እንድንችል የተሰጠን ጊዜ ነው። እርሱ በገና በዓል አማካይነት በድጋሚ ወደ እኛ ይመጣል፣ በዚህም እርሱ በትህትና የሰውን ባሕሪ ተላብሶ የመጣበትን ታሪካዊ ወቅት እናስታውሳለን፣ ነገር ግን እኛ እርሱን በውስጣችን ለመቀበል ዝግጁዎች በምንሆንባቸው ወቅቶች ሁሉ ወደ እኛ ይመጣል፣ እናም በመጨረሻው ዘመን "በሕያዋን እና በሙታን ላይ ለመፍረድ" እንደገና ይመጣል። ለዚህም ዘወትር ነቅተን መጠበቅ እና ጌታ ለመገናኘት በተስፋ መጠባበቅ አለብን። የዛሬው  ሥርዓተ አምልኮ ከዚሁ ሐስብ ጋር በተጎዳኜ መልኩ ነቅተን እንድንጠባበቅ የሚያሳስቡንን መሪ ሃሳቦችን ያስተዋውቀናል።

በማርቆስ ወንጌል 1333-37 ላይ ኢየሱስ እርሱ የሚመጣበት ቀን እና ሰዓት ስለማይታወቅ ነቅታችሁ ጠብቁ ብሎ ያሳስበናል። እንዲህም ይላልስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤{. . .} ትጉ፣ ጸልዩም ተግታችሁ ጠብቁ፤ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁበማለት ያሳስበናል።

በዓለም ውስጥ ያሉትን በጣም የሚረብሹ ድምጾችን በመስማት እነዚህ ድምጾች በሚፈጥሩት ስሜት የማይረበሽ፣  ነገር ግን በምልአት እና በማስተዋል በመኖር በተለይም ደግሞ ለሌሎች ሰዎች ቅድሚያ ለመስጠት የሚጨነቅ ሰው እርሱ ነቅቶ የሚኖር ሰው ነው። ይህ ባሕሪ ደግሞ ለባልንጀሮቻችን እንባ እና ፍላጎቶቻቸውም ሳይቀር ትኩረት እንድንሰጥ በማድረግ መንፈሳዊ እና ሰብዓዊ ብቃትን እና ጥራትን እድናዳብር ያደርገናል። አስተዋይ የሆነ አንድ ሰው ወደ ዓለም በመሄድ በቸልተኝነት እና በጭካኔ መንፈስ የሚፈጸሙትን ተግባሮች ለመቃወም በመሞከር፣ እንዲሁም ባሉት መልካም እና ውብ የሆኑ ሀብቶች መደሰት እና ይህንንም ደስታ በመጥበቅ የሚኖር ሰው ነው። የግለሰቦችን፣ የህብረተሰቡን ችግር እና ድህነትን በመለየት፣ በየቀኑ በሚያገኘው ጥቃቅን ነገሮች ውስጥ፣ ጌታ በሰጠን ቦታ ውስጥ ሳይቀር ተደብቆ ለሚገኙት ሀብቶች ሁሉ እውቅና የመስጠት እና ማስተዋል ያስፈልጋል።

ነቅቶ እንዲጠበቅ የደረሰውን ጥሪ የተቀበለ ሰው እርሱ ንቁ ሰው ነው፣ ይህም ማለት ተስፋ በቆረጠ ስሜት የተኛ እና በእነዚህም ስሜቶች የተመሰረተ ሰው አይደለም ማለት ነው። በተመሳሳይ  መልኩም በዓለማችን ውስጥ የሚግኙ ብቸኝነትንም ሊያስከትሉ በሚችሉ በርካታ ከንቱ ከሆኑ ነገሮች ራሱን በማግለል እና ከንቱ የሆኑ ነገሮችንም በመቃወም፣ አንድአንዴም በእነዚ ነገሮች ውስጥ ተዘፍቀው የሚኖሩትን ቤተሰቦቹን ይሁን ሌሎች ግለሰቦችን ከዚህ ማጥ ውስጥ  ለማውጣት ጊዜውን የሚሰዋ ሰው እርሱ ነቅቶ የሚጠብቅ ሰው ነው። ይህም ዛሬ ነቢዩ ኢሳያስ የተረከልን አሳዛኝ የሆነ የእስራኤል ሕዝቦች ተሞክሮ ነው፣ የእራኤል ሕዝብ እግዚኣብሔር ችላ ያላቸው ስለመሰላቸውእግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን?” (ኢሳያስ 6317) ብለው እግዚኣብሔርን እንደ ጠየቁት ዓይነት ነው። ነገር ግን ይህ የተከሰተው እነርሱ ለእግዚኣብሔር ታማኞች ባለመሆናቸው የተነሳ ነው። እኛም ብንሆን አንደንድ ጊዜ ለጌታ ጥሪ ታማኞች የማንሆንባቸው ጊዜያት አሉ፣ ነገር ግን እርሱ ሁል ጊዜ የሚያሳየን የእምነትን፣ መልካም የሆነን የፍቅር መንገድን ሲሆን ነገር ግን እኛ ደስታችንን የምንፈልገው ከእነዚህ ነገሮች ተቃራኒ በሆኑ መንገድ ነው።

መጠንቀቅ እና ነቅቶ መጠበቅ የሚሉት ማሳስቢያዎችከጌታ መንገድ በወጣት ከእርሱ ርቀን እንዳንሄድ እኛን ለማሳሰብ የተሰጡን ማሳሰቢያዎች ሲሆኑ በኃጢአቶቻችን እና እመንት በማጉደላችን የተነሳ እንዳንጠፋ ያደርጉናል። ነቅቶ መጠበቅ እግዚኣብሔር ሕልውናችንን ሰንጥቆ እንዲገባ መንገድ የሚያመቻች ሲሆን መጥፎ የሚባሉ ነገሮችን ከሕይወታችን አስወግደን በምትኩም በእርሱ መልካምነት እና ርኅራኄ እንድንሞላ ያደርገናል።

እግዚአብሔርን በትዕግስት በመጠበቅ እና የንቁዎች ሁሉ አብነት የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ልጅዋን ኢየሱስ እንድንገናኝ እና ለእርሱ ያለንን ፍቅር እንድንገልጽለት ትረዳን ዘንድ አማላጅነቷን እንማጸናለን አሜን!

ከመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት ቡኃላ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን ስብከት ካጠናቀቁ ቡኃላ እና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነው እና ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን መልዐኩ ገብርኤል ማሪያምን ያበሰረበት የምስራች ጸሎትን ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ ቡኃላ ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በምያንማር እና በባንግላዲሽ ያደረጉትን 21ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት በሰላም አጠናቀው መመለሳቸውን ገልጸው ይህ ሐዋሪያዊ ጎዞዋቸው እንዲሳካ በጸሎትም ሆነ በተለያዩ መልኮች የተባበሩትን ሰዎች ሁሉ በከፍተኛ ሁኔታ አመስግነዋል።

በተለይም ደግሞ በእነዚህ ማለትም በምያንማር እና በባግላዲሽ የሚኖሩ በቁጥር አነስተኛ የሆኑትን የካቶሊክ ምዕማናን በመጎብኘቴ እና በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ምንም እንኳን በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም ነገር ግን እየሰጡት የሚገኘው ምስክርነት ከፍተኛ ቦታ ሊሰጠው የሚገባው መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

በተለይም ደግሞ የተለያዩ ጫናዎችን እና መከራዎችን ተቋቁመው በብርታት እና በታላቅ ደስታ ወንጌላዊ ምስክርነትን በታላቅ ግድል እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸው ለዚህም ክቡር ለሆነ ተግባራቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በሁንዱራስ በአሁን ወቅት የሚታየውን ፖሌቲካዊ ቀውስ በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው ማንኛውንም ልዩነቶቻቸውን በሰላም እና በውይይት ይፈቱ ዘንድ ጥሪ አቅርበው በዚህም አስቸጋሪ ወቅት እግዚኣብሔር ከአሁንዱራስ ሕዝቦች ጋር ይሆን ዘንድ ምኞታቸው እና ጸሎታቸውም እንደ ሆነ ከገልጹ ቡኃላ ቡራኬን ሰጥተው ለእለቱ የነበረው ዝግጅት ተጠናቁዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.