2017-12-02 11:29:00

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከኅዳር 21-23/2010 ዓ.ም. በባንግላድሽ ያደረጉት 21ኛው ሐዋሪያው ግብኝት ተቅላላ ይዘት።


የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከኅዳር 21-23/2010 ..  የባንግላድሽ 21ኛው ሐዋሪያው ግብኝት

መርሃ ግብር

Viaggio Apostolico del Santo Padre in Myanmar e Bangladesh
            (26 novembre - 2 dicembre 2017)

የዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

ቅዱስነታቸው በባንግላዲሽ ለምያደርጉት ጉብኝት የመረጡት መሪ ቃል ይህ ከላይ የምትመለከቱት “ሰላም እና ሕብረት” የሚሉት ቃላት ነው።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከኅዳር 21-23/2010 ዓ.ም.  የባንግላድሽ 21ኛው ሐዋሪያው ግብኝት መርሃ ግብር

በኅዳር 21/2010 ዓ.ም በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በሀገሪቱ ከሚገኙ ባለስልጣናት እና የሲቪል ማሕበራት ጋር ተገናኝተው ንግግር አድርገዋል።

በኅዳር 22/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 04፡00 ላይ መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል በዚሁ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የሚስጢረ ክህነት ቅባ ቅዱስ ለ16 አዳዲስ ካህናት ሰጥተዋል

በኅዳር 22/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር 10፡15 ላይ በሀገሪቷ ከሚገኙ ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው ንግግር አድርገዋል።

በኅዳር 22/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር 11፡00 ላይ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋምት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በኅዳር 23/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 04፡45 ላይ ባንግላዲሽ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፣ ደናግላን ፣ ገዳማዊያን/ገዳማዊያት እና የዘርዐ ክህነት ተማሪዎች ጋር ተገናኝተዋል።

በኅዳር 23/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር 09፡20 የባንግላዲሽ ውና ከተማ በዳካ ከሚገኙ የወጣቱ ማሕብረሰብ አባላት ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በመቀጠል  የባንግልዳሽን አጠቃላይ ሁኔታ እንደ ሚከተለው እናስቃኛችኃለን።

ባንግላዲሽ በኢስያ አህጉር የትገኝ ሀገር ስትሆን በ2016 ዓ.ም. በተድረገው አጠቃላይ የሕዝብ ቆጠራ 166 ሚሎዮን የሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ናት። ከጠቃላይ የሕዝብ ብዛቷ ውስጥ 350,000 የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ይህም በመቶኛ ሲሰላ 0.24 % ነው። በብዛኛው የባንግላዲሽ ሕዝብ የሙስሊም እምነት ተከታትይ ሲሆን፣ የቡዳ እና የሌሎች ባሕላዊ እመንት ተከታዮችን መኖሪያ ናት።

የባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ ይባላል። ዳካ በሀገሪቷ ከሚገኙ ከተሞች ሁሉ በስፋቱ ትልቅ የሆነና 15,669,000 ሕዝብ ታጭቆ የሚኖርባት ከተማ ስትሆን ይህም  በዓለም ደረጃ በጣም ብዙ ሕዝብ ታጭቆ ከሚኖርባቸው በርካታ ከተሞች አንዷ ያደርጋታል። ዳካ የባንግላዲሽ የፖሌቲካ፣ የባሕል፣ የኢኮኖሚ በተጫማሪም የኢዱስትሪ ማዕከል የሆነች ከተማ ስትሆን ይህቺ ከተማ የተቆረቀረችሁም ከክርስቶስ ልደት ቡኃላ 1000 ዓ.ም. ነው።

እንደ አውሮፓዊያን የቀነ አቆጣጠር  በ1765 ዓ.ም. በእንግሊዚ የቀኝ ግዛት ሥር ገብታ የነበረ ሲሆን አሁንም እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1946 የፓኪስታን ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች። በመቀጠልም ከፍተኛ የሆነ ደም አፋሳሽ ጦርነት ከተደረገ ቡኃላ 1971 ዓ.ም. ከፓኪስታን ቅኝ ግዛት ነጻ በመውጣት የባንግልዲሽ ዋና ከተማ ሆና እስከ ዛሬው እለት ድረስ እያገለገለች ትገኛለች። በዳካ በጣም ብዙ የሚባሉ ቀልብን የሚስቡ የቱሪስት መስዕቦች የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም በሀገሪቷ በጣም ትልቅ የሆነ የቴክኖሎጂ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ትምህርቶች የምሰጡበት ትልቅ በምንግሥት የሚተዳደር ዩንቬርሲቲ ይገኛል። 2014 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ተገንቦቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ኖተር ዳም በመባል የሚታወቅ የካቶሊክ ዩኒቬርሲቲም የሚገኝባት ከተማ ናት ዳካ።

የዳካ ሀገረ ስብከት እንደ አ.አ በመስከረም 1 /1886 ዓ.ም. እንደ ተቋቋመ የተገለጸ ሲሆን በ1950 ዓ.ም. ደግሞ የሀገሪቷ ሊቀ ጳጳሳት መቀመጫ በመሆን እስከ ዛሬ ድረስ እያገለገለች ትገኛለች። የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ የብራዚል ተወላጅ የሆኑት ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል ፓትሪክ ዲ ሮዛሪዮ ሲሆኑ   በአጠቃላይ በዳካ ሀገረ ስብከት ክልል ውስጥ ከሚገኙ 23,673,082 ነዋሪዎች ውስጥ 76,072 ብቻ የካቶሊክ እመንት ተከታዮች ናቸው።  ይህም በመቶኛ ሲሰላ የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት በዳካ 3.1% ነው ።  (ይህ ስሌት የጠቃላላው በባንግላዲሽ የሚኖሩ ካቶሊኮች ብዛት ሳይሆን በዋና ከተማዋ በዳካር የሚገኙት የካቶሊክ ምዕመናንን የሚመለከት ብቻ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን)

በዚሁ የዳካ ሀገረ ስብከት 19 ቁምሳና፣ 16 ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ 44 የሀገረ ስብከቱ ካህናት፣ 63 ደናግላን፣ 16 የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች፣ 135 የተለያዩ የወንዶች መንፈሳዊ ማኅበራት፣ 314 የተለያዩ የደናግላን መንፈሳዊ ማሕበራት፣ 78 የትምህርት መስጫ ተቋማት፣ 35 የእርዳታ መስጫ ማዕከላት የሚገኙበት ሀገረ ስብከት ሲሆን በዚህ አመት ማገባደጃ ላይ ብቻ 878 ሰዎች ምስጢረ ጥምቀትን ተቀብለዋል።

ቅዱስነታቸው በባንግላዲሽ

ቅዱስነታቸው በዳካ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ በደረሱበት ወቅት የባንግላዲሽ ሪፖብልክ ርዕሰ ብሔር በሆኑት አብዱል አህመድ እና በተለያዩ የመንግሥት ባለስልጣናት እና 10 በሚሆኑ የባንግላዲሽ ጳጳሳት፣ 25 ምዕመናን እና 40 ሕጻናት ተገኝተው ደማቅ አቀባብል የተደርገላቸው ሲሆን በሁለት ሕጻናት የአበባ ስጦታዎች እንደ ተደረገላቸው ከስፍራዉ የደረሰው ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም በዳካ በሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። ይህ የሰማዕታት ሀውልት ከዳካ ከተማ 35 ኪሎ ርቀት ላይ የተገነባ ሲሆን ባንግላዲሽን ከፓኪስታን ቅኝ ግዛት ሥር ነጻ ለማውጣት ታስቦ በተደረገው ጦርነት ነብሳቸውን ለሰው ሰዎች መታሰቢያነት የተሠራ ነው። ይህም ሀውልት 1971 ዓ.ም. ሀገሪቷ ከፓኪስታን አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆኑዋን ለማብሰር ታስቦ የተገነባ ነው።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም በዚያው ስፍራ የሚገኘውን በሔራዊ ሙዚየም ጎብኝተው በክብር መዝገብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

ቅዱስነታቸው በባንግላዲሽ ብሔርዊ ሙዚየም ቆይታን ካደረጉ ቡኃል ወደ ሀገሪቷ ብሔርዊ ቤተ መንግሥት  አቅንተዋል። በዚያም  በሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር አብዱል አህመድ በድጋሚ ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በብሔርዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ለተሰበሰቡ የሀገሪቷ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት ልዑካን እና የሲቪል ማኅብራት ተወካዮች በተገኙበት የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል።

 

ክቡር ርእሰ ብሔር

የተከበራችሁ ባለ ሥልጣናት

የተከበራቸው ውድ ወንድሞቼ ጳጳሳት

ክቡራትና ክቡራን በዳካ የውጭ አገሮች መንግሥታት ልዑካን

ከምያንማር ራክሂነ ግዛት የተሰደዱት በባንግላደሽ ጊዚያዊ መጠለያ ላገኙት ተፈናቃዮችን በማሰብ እነዚህ ወንድሞችንና እህቶች ተፈናቃዮች ያለባቸው ችግር ብሎም እየኖሩት ያለው አሳሳቢው ሁኔታ ለሁሉም ገሃድ ነው፡ በመሆኑም በዚህ አጋጣሚ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተገቢ ድጋፍና ትብብር እንዳይለያቸው  እማጸናለሁ።

በባንግላደሽ ሃይማኖታዊ ስምምነት መግባባት ሰላም እና ሰብአዊነት የሰፈነባት አገር መሆንዋ የገለጡትን ሓሳብ ቅዱስ አባታችን መለስ ብለው በማስተዋል እነዚያ ተፈናቃዮች ይኸንን መልካምነት በተካነች አገርና ሕዝብ ታላቅ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ቢሆንም ጊዚያዊ መጠለያ እና የመጀመሪያ መሠረታዊ እርዳታ ለማግኘ ችሏል። በሁሉም የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሚታይ ቅዱስ ተግባር ነው።

የሁኔታው አሳሳቢነት ለሕይወት አስፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ምግብ መድሃኒት መጠለያ የመሳሰሉት አቅርቦት እጥረት አጥጋቢ ባለ መሆኑ ወንድሞቻችንን እህቶቻችን ሕፃናት አዛውንቶች እና በጠቅላላ ስደተኞች ለከፋ አደጋ እንዲጋለጡ አያደረገ ነው። ሁኔታው እንዲሆ ሆኖ እያለ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይኸ መፈናቀል እያስከአለው ያለው አቢይ ሰብአዊ ችግር እግምት ውስጥ በማስገባት የተስተካከለ ምላሽ በመስጠቱ ረግድ እጅግ የዘገይ ይመስላል። የተከሰተው ችግር ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ታልሞ እየተደረገ ያለው ጥረት አስፈላጊ ነው ሆንም ግን ይኽ ጥረት ለብቻው በቂ አይደለም፡ ቅድሚያ እነዚህ ስደተኞች ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን እያስተናገደች ላለቸው አገረ ለስደተኛው የተሟላ ድጋፍ ለማቅረት የሚያስችላት በቂ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ ትችል ዘንድ አጠቃላይ ድጋፍ ልታጋኝ ይገባል።

ቅዱስ አባታችን በዚህ ባስደመጡት ንግግር ባንግላደሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያካሄዱት ..ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ቀጥለውም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎ ሁለተኛ መሆናቸው ዘክረው የባንግላደሽ ርእሰ ብሔር ይህችን የተባረከች አገር እንጎበኝ ዘንድ ስላቀረቡልኝ ይፋዊ ጥሪ ከልብ አመሰግናለሁ፡ ባንግላደሽ ኅብረ ቋንቋ እና ኅብረ ባህል ግምት የሰጠ አንድነት እውን ለማድረግ እያካሄደቸው ያለው ዘርፈ ብዙ ጥረት የሚደነቅ ነው፡ ማንም አገር ይሁን ሰው በተነጥሎ ዝግ በሆነ ኑሮ ህልው ሊሆን አይችልም። በተነጥሎነት እድገት ሊጨብጥም አይችልም። የብቸኛው ሰብአዊ ቤተሰብ አባል እንደ መሆናችን መጠን እያንዳንዳችን እርስ በርሳችን ተፈላላግያን እና አያንዳንንዳችን የሌላው ጥገኞች ነን፡ በማለት ባንግላደሽን ከፓኪስታን ተለይታ ነጻነቷን እንደ በተቀዳጀችበት ማግስት የመጀመሪያው ርእሰ ብሔር ሸክ ሙጂቡር ራህማን ስለ አገራቸው ሲናገሩ፥ ወቅታዊት ኅብረአዊት ሁሉንም የምታቅፍ እያንዳንዱ ሰው እና እያንዳንዱ ማኅበረተሰብ በነጻነት በሰላም በአንድነት ለጋራ ጥቅም መረጋገጥ የሚገባውን አስተዋጽኦ የሚያበረክትባት በተለይ ደግሞ ለድኾች እጅግ በድኽነት ለተጠቁት ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን ስለ እነርሱ አሳቢነት እና ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት የሕግ ሉኣላዊነት የተረጋገጠባት አገረ ባንግላድሽ መገንባት የሁላችን ኃላፊነት ነው በማለት የተናገሩት በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ የተዘገበው ባንግላደሽ እንደ አላማ የምትመራበት መርሆ በማስታወስ፥ እውነተኛ እና ቅን ውይይት  ብዛህነት የሚከበርባት የባህል የሃይማኖት የቋንቋ ልዩነት የታረቀባት የሁሉም የሃሳብ ልዩነት የሚስተናገድባት አገር ውህንደት ይኖራታል። ምክንያቱም ውይይት መጻኢን ይመለከታል አንድነትን ይገነባል እያንዳንዱ ለጋራ ጥቅም ትጉ እንዲሆን ያደርጋል እንዳሉ ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን በራምና ከተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች እና ከተለያዩ የአቢያተ ክርስቲያን መንፈሳዊ መራህያን ጋር በጋራ ለሰላም በሚል ርእየት ላይ ያተኮረ ለሰላም ግንባታ የጋራ ጥረት ለማበረታት የተካሄደው የጋራው የጸሎት መርሐ ግብር ዘክረው ይኽ ደግሞ ለሰላም ግንባታ አስተማማኝ መሠረት የሆኑትን እሴቶች የሚያጎላ የጋራ መከባበር እንዲኖር የሚያነቃቃ ነው፡ በሌላው ረገድ መንፈሳውያን እሴቶች ለአንድ ሰላማዊ እና ቅን ሕብረተሰብ መሠረት መሆኑ የሚመሰክር ነው።

በዚህ አልፎ አልፎ ሃይማኖት በተሳሳተ እጅግ እንቅፋት ለሆነ ምግባር መሣሪያ እየተደረገ የመከፋፈል የግጭት የጥፋት  ምክንያት እንደሆነ ተደርጎ ሲተገበር ይታያል።  ስለዚህ ሃይማኖት የእርቅ እና የአንድነት ለሰላም ለተከባብሮ መኖር መሆኑ እንዲገለጥ የእያንዳንዱ አማኝ ምስክርነት ከምን ግዜም በበለጠ ዛሬ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ያስገነዘቡት ቅዱስ አባታችን፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ ባለፈው ዓመት በዳካ ተጥሎ የነበረው ዘግናኙ ግብረ ሽበራ አስታውሰው፡ በዚያኑ ወቅት በባንግላደሽ ለሚገኙት ለሁሉ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች እና ለአገሪቱ መንግሥት አስተላልፈዉት በነበረው መልእክት፥ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስም ጸረ ማንኛውም አምሳያ ላይ ለሚሰነዘረው ጥቃት እና አመጽ መሣሪያ ሊሆን አይችልም በማለት ያሰመሩበትን ሃሳብ አስታውሰው፥ ዓይነ ልቦናቸውን ወደ እነዚያ በቁጥር አናሳ ወደ ሆነው የባንግላደሽ ካቶሊካውያን ምእመናንን ላይ በማነጣጠር በቁጥር አናሳ ቢሆኑም በግብረ ሠናይ አገልግሎት አማካኝነት ለአገር ግንባታ አቢይ አስተዋጽኦ የሚያበረክት የኅብረተሰብ ክፍል ነው።

ቤተ ክርስቲያን በባንግላደሽ ሁሉንም የተለያዩ ኃይማኖቶችን የሚያስተናግድ ያለው የነጻነት ግንዛቤ በማድድነቅ የዚህ ነጻነት ውጤት ተጠቃሚም መላ አገሪቱ ነች፡ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በምትገኝባቸው ክልሎች ባላት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የግንኙነት ባህል የምታስፋፋ፡ ሁሉንም በዚህ ባህል የምታንጽ እያንዳንዱ በማኅበራዊ ሕይወት የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በኃላፊነት መንፈስ እንዲያድግ ታስተምራለች። በባንግላደሽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ባላት የሕንጸት ዘርፍ በተለይ ደግሞ ትምህርት ቤቶች አማካኝንት ያንን የሁሉን ሃይማኖቶች የጋራ ግንኙነት በማነቃቃት የሚሰጠው አወንታዊ ውጤት በማመላከት አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ባስተማሪነትም ሆነ በተማሪነት ሁሉንም በማሳተፍ ሰላማዊ አብሮነትን ትመሰክራለች ብለው ደግመው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፡ በአገሪቱ ያለው በቁጥር አናሳ የሆነው ካቶሊክ ምእመን በአገሪቱ ያለው ነጻነት በመኖር ለጋራ ጥቅም በሚያበረክተው አስተዋጽኦ እንዲበራታ አደራ በማለት ሁሉንም አመስግነው ንግግራቸው እንዳጠቃለሉ አኵይሊኖ ባጠናቀሩት ዘገባ ተቁሟል።

 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳረጉ

በኅዳር 22/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 4,00 ላይ መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል። በዚሁ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የሚስጢረ ክህነት ቅባ ቅዱስ ለ16 ለአዳዲስ ካህናት ሰጥተዋል። 0.24% የካቶሊክ ምዕመናን በሚኖሩባት ባንግላድሺ በአንድ ጊዜ 16 ካህናት መገኘታቸው በዚያ ለሚኖሩ የካቶሊክ ምዕመናን አበራታች እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው መናገራቸው ተጠቁሙዋል።

በኅዳር 22/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር 11፡00 ላይ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋምት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። በዚህም ንግግራቸው ቅዱስነታቸው ትኩረት የሰጡት ጉዳይ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች በተገኘው ውጋጣሚ በሙሉ ግጭቶችን እና አሸባሪነትን መቃወም እና ማውገዝ እንደ ሚጠበቅባቸው በጽኖት ገለጸዋል። በተጨማሪም በልዩነት ውስጥ ኅብረትን እንዲፈጥሩ በማሳሰብ ዘላቂ ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለውም በልዩነቶች ማመን ሲቻል ብቻ በመሆኑ የተነሳ ልዩነት ውበት እንጂ የግጭቶች መንስሄ እንዳይሆን አጥብቆ መስራት እንደ ሚገባም ገልጸዋል።

በኅዳር 22/2010 ዓ.ም. በሀገሪቷ የሰዓት አቆጣጠር 10፡15 ላይ በሀገሪቷ ከሚገኙ ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው ንግግር አድርገዋል። የዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው እናቀርባለን።

የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች አመጽን የሚቃወም ድምጻቸውን በአንድነት ቢያስተባብሩ እና የግጭት እና የአመጽ ባህል በግንኙነት ባህሊ እዲተካ ቢጥሩ የዚያ የሚከተሉት ሃይማኖት መሠረታዊ ትምህርት እንደሚተገብሩ የተረጋገጠ ነው፡ ማንም ሃይማኖት ለዓመጽ ምክንያት ሊሆን አይችልም ያሉት ቅዱስ አባታችን ለብፁዓን ጳጳሳቱ፥

አቡናት በቁምስናዎች በካቶሊክ ማኅበረሰብ ህልውና እንዲሆኑ እና ለምመናን ለሁሉም ቅርብ መሆናቸው እንዲመሰክሩ አደራ። የባንግላደሽ ሕዝብ ለቤተሰብ ያለው ፍቅር በሁሉም የሚመሰከር እውነት ነው፡ በአገሪቱ የሚገኘው ካቶሊክ ምእመን ይኸንን ፍቅር የሚኖር እና በግብረ ሠናይ መስክ በሚሰጠው አገልግሎት በተለይ ደግሞ ለተናቁት በድኽነት ለተጠቁት የሚመሰገን ነው ሆኖም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው የግብረ ሠናይ አገልግሎት ግብረ ኖልዎ እስትንፋስ ያደረገ መሆን አለበት እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አያይዘው፡ ቅዱስ አባታች በዚህ ብፁዕ ካርዲናል ፓትሪክ በሁሉም በባንግላደሽ በሚገኙት ብፁዓን ጳጳሳት ስም ላስደመጡት ንግግር  እና በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በጥልቀት የሚያስርዳ መሆኑም ገልጠው ምስጋናን አቅርበው፡ በመካከላቸው በመገኘታቸው ምክንያት ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው እና የቤተ ክርስቲያን ኵላዊነት እና ልኡክነት የሚያጎላ ግኑኝነት ነው እንዳሉ ይጠቁማሉ።

ቤተ ክርስቲያን በሁሉም ሥፍራ የሱታፌ ትምሕርት መሆን አለባት ይኽ ደግሞ በብፁዓን ጳጳሳት መካከል ጉባአያውነት እንዲኖር የሚደግፍ መሆኑ ያብራሩት ቅዱስ አባታችም፥ ጉባእያውነት በብፁዓን ጳጳሳት መካከል ሲኖር የዚያ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ጉባእያውነት ይንጸባረቃል። የሕዝብ ዕለታዊ ኑሮ የሚንጸባረቅባት ቤተ ክርስቲያን መኖር ያስፈልጋል። ለካህናት ለምእመናን ቅርብ መሆን። መቼም ቢሆን ተገሎ ከመኖር ፈተና መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በምእመናን መካከል ለሚሠራው መንፈስ ቅዱስ ክፍት መሆን የክርስቲያን ሕንጸት የካህናት ሕንጸት የሚያነቃቁ ስለ ሁሉም መንፈሳዊ ጥማት ማሰብ ይጠበቅብናል እንዳሉ ሎሞናኮ አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት መርሕ ቃል፥ ነቢይነት የድኾች ድምጽ መሆን የተናቁት የተገለሉትን ያማከለ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መኖር ይኽ ደግሞ ያንን በምኅረት ቅዱስ ዓመት የተኖረውን ክርስቲያናዊ መንፈስ የሚያሳስብ ነው፡ የምህረት ባህል ያስፋፉ ዘንድ አደራ ብለው፡ ለሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው፡ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ በማለት የለገሱት ምዕዳን ማጠቃለላቸው ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኰ አስታውቋል።  

ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ከምያንማር በአሰቃቂ ሁኔታ ከተሰደዱ እና በቁጥር አናስ ከሆኑ የሙስሊም ማኅብረሰቦች ጋር በባንግላዲሽ የተገናኙ ሲሆን “ለስደት በዳረጉዋችሁ ሰዎች ስም ሆኜ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ማለታቸው ተገልጹዋል። የሰው ልጆች ሁሉ በእግዚኣብሔር መልክ እና አማስያ በመፈጠራቸው የተነሳ ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ ሊኖሩ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አበክረው ገልጸዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.