2017-11-30 14:34:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "እናንተ ወጣቶች የሁላችንም የወደ ፊት ተስፋ ናችሁ" ማለታቸው ተገለጸ።


ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ሰላም እና ፍቅር” በሚል ምሪ ቃል 21ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት በምያንማር በማደረግ ላይ መሆናቸውን ቀደም ሲል ባዘጋጀናቸው የተለያዩ ዝግጅቶች መጥቀሳችን ያትወቃል። በኅዳር 20/2010 ዓ.ም. በያንጎን ከተማ በሚገኘው ካቴድራል ፊት ለፊት በሚገኘው ስፍራ መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል። 

ይህንን መስዋዕተ ቅዳሴ በምያማር የሚኖሩ በቁጥር አነስተኝ የሆኑ የካቶሊክ ምዕመናን በጉጉት እና በትዕግስት ሲጠባበቁት የኖሩት ወሳኝ ጊዜ እንደ ነበረም ተገልጹዋል። በጣም ብዙ የሚባሉ ከተለያዩ ሥፍራዎች የተውጣጡ ምዕመናን በመስዋዕተ  ቅዳሴው ላይ የተሳተፉ ሲሆን በተለይም  ከምያንማር የገጠራማ ሥፍራዎች ሳይቀር የበርካታ ቀናት የእግር ጉዞ አደርገው ይህንን ታላቅ የሆነ ክስተት ለመከታተል የመጡም በርካታ ምዕመናን በመስዋዕተ ቅዳሴው ተሳትፈዋል።

ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት "በርካታ በምያንማር የሚኖሩ ዜጎች በግጭቶች ምክንያት የተፈጠሩ ቁስሎችን ተሸክመው እንደ ሚገኙ” አስታውሰው “ከእነዚህን ሰቆቃዎችና አስከፊ ትዝታዎች” መፈወስ የሚችሉበትን መንገዶች በመጠቆም ይህንን አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታም በተዘዋዋሪ መንገድ ገልጸውታል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በእለቱ የተነበቡት ምንባባት

  1.  ሮሜ ሰዎች 10፡9-18
  2. መዝሙር 18
  3. የማቴዎስ ወንጌል  4፡18-22

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እሕቶቼ እንደምን ዋላችሁ!

 

ይህንን ውብ በሆነ ሀገራችሁ እያደረኩት የምገኘውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት እያጠናቀኩ በምገኝበት በአሁኑ ወቅት በእነዚህ ቀናት ለተቀበለናቸው በርካታ ፀጋዎች እግዚኣብሔርን አብራችሁኝ እንድታመሰግኑ እጋብዛችኃለሁ። እናንተን የምያንማር ወጣቶችና በዚህ ካቴድራል ፊት ለፊት የተሰበሰቡትን ሰዎች ሁሉ በምመለከትበት በአሁኑ ወቅት ዛሬ ከተነበበልን የመጀመሪያው ምንባብ  (ወደ ሮሜ ሰዎች 109-18) ላይ የተወሰደውን እና በውስጤ የተሰማኝን አንድ አረፍተ ነገር ለመጥቀስ እፈልጋሉ። ይህም ሐሳብ የተወሰደው ከትንቢተ ኢሳያስ መጽሐፍ ሲሆን ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ደግሞ ይህንን ሐሳብ በሮም ለሚገኙ ወጣት የክርስቲያን ማኅበረሰብ በጻፈው መልእክቱ በድጋሚ ሲያስተጋባ እንሰማለን፣ እስቲ ይህንን ቃል በድጋሚ እንስማውየምሥራችን የሚያመጡ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው!” (ሮሜ 1015) የሚለው ነው።

የተከበራችሁ የምያንማር ወጣቶች፡ ይህንን የወጣትነት ድምጽአችሁን እና በዚህ ድምጻችሁ ያቀረባቸሁትን ዝማሬ በሰማሁበት ወቅት እነዚያን የሐዋሪያው ጳውሎስን ቃላት በእናተ ላይ መተግበር እፈልጋለሁ። አዎ! "እናንተ የምስራች ድምጽ ናችሁ እናንተ የምታምሩ እና የምታበረታቱ እይታዎች ናችሁ፣ ምክንያቱም መልካም ዜናውን ስላመጣችሁልን፣ የወጣትነታችሁን መልካም ዜና ስላመጣችሁልን፣ እምነታችሁን እና ጉጉታችሁን ስላመጣችሁልን ነው። በእርግጥም እናንተ የምስራች ቃል ናችሁ፣ ምክንያቱም እናንተ ቤተክርስቲያን ዘላለማዊ የሆነ ደስታ እና ተስፋ በሚሰጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላትን እምነት የሚገልጽ ተጨባጭ የሆነ ምልክቶች ስለሆናችሁ ነው።

ምን አልባት ከመካከላችን አንድ አድን ሰዎች በዙሪያችን የሚገኙ ብዙ ሰዎች በስቃይ ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት እንዴት ነው የምስራችሁን ቃል መናገር የምንችለው? ብለው ሊጠይቁ ይችሉ ይሆናል። ብዙ የፍትሕ መጓደል፣  ድህነትና መከራ በእኛ እና በዓለም ዙሪያ ባጠላበት በአሁኑ ወቅት የምስራችሁ ቃል የት ነው ያለው? ነገር ግን እናንተ ከዚህ ሥፍራ ለቃችሁ ወደ መጣችሁበት በምትመለሱበት ወቅት የግል የሆነ መልእክቴን ይዛችሁ እንድትመለሱ እፈለጋለሁ። በምያንማር የሚኖሩ ወጣቶች በአምላክ ምሕረት እና በምስራቹ ቃል፣ ስምና ፊት ባለው በኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምያምኑ ሰዎች እንዲያውቁ እፈልጋለሁ። እንደ የምስራቹ ቃል መልእክተኞች በመሆን የምስራችሁን ቃል ለቤተክርስቲያኗ፣ ለሀገራችሁ እና እንዲሁም ለመላው ዓለም  ለማዳረስ ዝግጁዎች ናችሁ። በስቃይ ላይ ለሚገኙ፣ የእናንተን ጸሎት እና አጋርነታችሁንም ለሚሹ ወንድም እና እህቶቻችሁ የምስራችሁን ቃል ለማዳረስ ዝግጁዋች ናቸሁ፣ በተጨማሪም የሰው ልጆች መሰረታዊ መብቶች ይከበሩ ዘንድ፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ እየሱስ ክርስቶስ ብቻ የሚያመጣልንንሰላም እና ፍቅርእንዲበረክት በመፈለግ ጉጉት ታሳያላችሁ።

ነገር ግን በማከልም ተግዳሮቶችን በፊት ለፊታችሁ ለማኖር እፈልጋልሁ። የመጀመሪያውን ምንባብ በጥንቃቄ አዳምጣችኃል ወይ? በዚያ ምንባብ ውስጥ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስካልሰሙስ?” የሚለውን ቃል ሦስት ጊዜ ሲደጋግም ሰምተናል። ይህ ቀላል የሆነ ቃል ቢመስልም ቅሉ ነገር ግን በእግዚኣብሔር እቅድ ውስጥ ያለንን ስፍራ እንድናስብ ይጠይቀናል። በእርግጥ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሦስት ጥያቄዎችን ያቀርብልናል፣ እነዚህንም ጥያቄዎች ለእያንዳንዳችሁ በግል ማቅረብ እፈልጋለሁ።ስለ እርሱስ ሳይሰሙ እንዴት ያምኑበታል?” የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ ማቅረብ እፈልጋልሁኝ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞሰባኪ ሳይኖር እንዴት መስማት ይችላሉ? የሚለው ሲሆን ሦስተኛው እና የመጨረሻው ጥያቄ ደግሞካልተላኩስ እንዴት መስበክ ይችላሉ?” (ሮሜ. 1014-15)የሚሉት ናቸው

ሁላችሁም በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ በጥልቀት እንድታስቡ እፈልጋልሁ። ነገር ግን መጨነቅ የለባችሁም! አንደ አንድ ተወዳጅ አባት (ምን አልባትም አያታችሁ ነኝ ብል ይሻላል መሰለኝ፣ )ከእነዚህ ጥያቄዎች ጋር ብቻ ግብ ግብ እንድትፈጥሩ አልፈልግም። እስቲ ደግሞ በእውነተኛ የሕይወት ጉዞዋችሁ ልመሩዋችሁ የሚችሉ ጥቂት ሀሳቦችን ላቅርብላችሁ እና ጌታ እናንተን የሚጠይቃችሁን ነገሮች እንድታውቁም ይረዳችኃል።

ቅዱስ ሐዋሪያ ጳውሎስስለ እርሱስ ሳይሰሙ እንዴት ያምኑበታል? በማለት ጥያቄን ያቀርብልናል። በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በብዙ ድምፆች የተሞላ ነው፣ የእግዚኣብሔር ድምጽ ተውጦ እንዲቀር የሚያደርጉ ብዙ የውድመት ድምጾችም ይሰማሉ። ሌሎች ሰዎች ሰምተው በእርሱ ማመን እንዲችሉ የሚያበቃቸውን ሀቀኛ የሆኑ ሰዎችን ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። ማዳመጥ የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጋሉ! በእርግጠኛነትም የሚፈልጉት ይህንኑ ነው። ነገር ግን ሐቀኛ እንድንሆን የሚያደርገን ጌታ ብቻ በመሆኑ የተነሳ ከእርሱ ጋር በጸሎት መነጋገር ልመዱ። በጸጥታ በልባችን ውስጥ የሚናገረውን የእርሱን ድምጽ መስማት ተማሩ።

በሰማይ ቤት ከሚገኙ ጓደኞቻችን ከሆኑ ከቅዱሳንም ጋር በጸሎት መነጋገር ልመዱ። ይህንንም ዛሬ ዓመታዊ በዓሉ እንደተከበረለት እንደ ቅዱስ እንድሪያስ አድርጉ። ቅዱስ እንድሪያ አንድ ተራ ዓሳ አጥማጅ የነበረ ሰው ቢሆንም የኢየሱስን ፍቅር የመሰከረ ታላቅ ሰማዕት ነው። ነገር ግን ሰማዕተ ከመሆኑ በፊት ስእተቶችን የሰራ ቢሆንም ታጋሽ መሆን ነበረበት፣ በትዕግስትም የኢየሱስ እውነተኛ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ቀስ በቀስ ተማረ። ስለዚህም ከራሳችሁ ስህተቶች መማርን አትፍሩ! ቅዱሳን ወደ ኢየሱስ እና ነብሳችሁንም በእርሱ እጆች ውስጥ ማኖር እንድትችሉ ይምሩዋችሁ ያስተምሩዋችሁም። ኢየሱስ በምሕረት የተሞላ መሆኑን ታውቃላችሁ። ስለዚህም በልባችሁ ውስጥ ያለውን ፍራሃት፣ ጭንቀት እንዲሁም ሕልማችሁን እና ተፋችሁንም ቢሆን ሁሉንም ነገሮች ለእርሱ አካፍሉት። ልክ የአትክልት ስፍራችሁን ወይም የእርሻ ማሳችሁን እንደ ምትንከባከቡት ልባችሁንም ኮትኩቱት። ይህም ጊዜን እና ትዕግስትን ይጠይቃል። ነገር ግን ልክ አንድ ገበሬ ሰብሉ እስኪያድግለት እንደ ሚጠብቅ ሁሉ እናንተም ከታገሳችሁ ጌታ ፍሬ እንድታፈሩ እና ይህንንም ያፈራችሁትን ፍሬ ከሌሎች ጋር እንድትካፈሉ ይረዳችኃል።

የሐዋሪያው ጳውሎስ ሁለተኛው ጥያቄ የነበረውሰባኪ ሳይኖር እንዴት መስማት ይችላሉ?” የሚለው ነበር። ይህ ነው እንግዲህ ለየት ባለ ሁኔት ለእናንተ ለወጣቶች የተሰጠው ኃላፊነትይህም ሚስዮናዊ ደቀ መዝሙር እንድትሆኑ የኢየሱስ መልካም ዜና አብሳሪዎች እንድትሆኑ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አሁን በእናንተ ጊዜ ለሚገኙ ሰዎች እና ለጓደኞቻችሁ ሳይቀር እንድታበስሩ ነው። ሰዎችን እንዲያስቡ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ አይፍሩ! ቅዱስ ወንጌል ሁል ጊዜም ቢሆን እያደገ የሚሄደው ከትንሽ ነገር ተነስቶ በመሆኑ የተነሳ  አንዳንድ ጊዜ ጥቂቶች የሆናችሁ መስሎ በሚሰማችሁ ጊዜ እና በጣም ወደ ዋላ የቀራችሁ መስሎዋችሁም በሚሰማችሁ ወቅቶች ሁሉ አትጨነቁ። ስለዚህም ራሳችሁን ተደማጭ አድርጉ። እንድትጭኹም እፈልጋለሁ! ነገር ግን በድምጻችሁ ሊሆን አይገባም። በፍጹም! ነገር ግን ጩኸታችሁን በሕይወታችሁና በልባችሁ በምታሰሙበት ወቅቶች ሁሉ ብርታት ለሚፈልጉ ሰዎች የተስፋ ምልክቶች ትሆናላችሁ፣ ለበሽተኞ ምርኩዝ፣ ለባዕድ ሀገር ሰው ፈገግታን እንዲሁም በብቸኝነት ለተጠቁ ሰዎች ደግሞ መልካም ትብብርን በማሳየት ሊሆን ይገባል።

የቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ የመጨረሻው ጥያቄካልተላኩስ እንዴት መስበክ ይችላሉ?” የሚለው ነው። ይህ መስዋዕተ ቅዳሴ ካበቃ ቡኃላ ሁላችንም የተቀበልናቸው ስጦታዎች ከእኛ ጋር በመውሰድ ይህንንም ስጦታ ለሌሎች ለማጋራት እንላካለን። ይህም ኢየሱስ የምልከን ወዴት እንደሆነ ሰለማናውቅ ሁሌም ቢሆን የሚረብሸን ሁሌም የሚያስጨንቅ ነገር ነው። ነገር ግን እርሱ ከኛ ጋር ጎን ለጎን ሳይራመድ ብቻችንን በምንም ዓይነት መንገድ አይልከንም። ሁልጊዜ ከፊት ለፊታችን በመራመድ ወደ አዲስ እና ድንቅ ወደ ሆነው የመንግሥተ ሰማያት ክፍሎች ይመራናል።

ዛሬ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ (ማቴዎስ 4 18-22) ጌታ ቅዱስ እንድሪያስን እና ወንድሙን ስምዖን ጴጥሮስን እንዴት ነበረ የላከው? “ተከተሉኝ!”(ማቴዎስ 419) ነበረ ያላቸው። መላክ ማለት እንግዲህ ይህ ነው! ኢየሱስን መከተል እና አመለካከታችንን በራሳችን ውሳኔ ብቻ መቀየር የለብንም ማለትም ጭምረ ነው። ጌታ ከእናንተ አንዳንዶቹን እንደ ካህናት አድርጎ ይልካል፣ በዚህ መንገድ "ሰዎችን አጥማጆች" እንዲሆኑ ይጋብዛል። ሌሎቻችሁንም ደግሞ ሕይወታቸውን ገዳማዊያን ወይም የተቀደሰ ሕይወት የሚኖሩ ወንዶች እና ሴቶች አድርጎ ይልካቸዋል። ሌሎቻችሁን ደግሞ በጋብቻ ሕይወት ወስጥ በመሰማራት ተወዳጅ የሆናችሁ አባቶች እና እናቶች እንድትሆኑ አድርጎ ይልካችኃል። ጥሪያችሁ ምንም ዓይነት ይሁን ምን ጠንካሮች፣ ደጋጎች እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ደስተኞች እንድትሆን አደራ እላችኃለሁ።

ዛሬ እዚህ በተሰበሰብንበት፣በያለ አዳም ኃጢያት የተጸነሰች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያሥም በተሰየመው እጅግ ውብ በሆነ ካቴድራል አጠገብ እንገኛለን። ማሪያም መልአኩ ገብረኤል ባበሰራት ጊዜአዎን አንዳልከኝ ይሁንልኝብላ በመለሰችበት ወቅት ልክ አሁን እንደ እናንተ በእድሜ ወጣት ነበረች። ነገር ግን የሰማችሁንመልካም ዜናበእምነት የመቀበል ወኔ ነበራት፣ ይህንን በሕይወቷ እና በጥሪዋ ተማኝ በመሆን ራሷን በመስጠት፣ በእግዚኣብሔር ፍቅር ጥበቃ ሥር ውስጥ ራሷን በሙሉ በማስገዛት በተግባር አሳየች። እንደ ማሪያም ሁላችሁም መልካሞች ሁኑ፣ ኢየሱስን እና የእርሱን ፍቅር ለሌሎች ለማዳረስ ብርታት ይኑራችሁ።

የተከበራችሁ ወጣቶች ከልብ ከመነጨ ፍቅር እያመሰገንኩዋችሁ እናንተን ሁላችሁንም እና ቤተሰቦቻችሁንም ሁሉ በእርሷ የእናትነት አማልጅነት ሥር ትሆኑ ዘንድ በአደራ ለእርሷ አስረክባችኃለሁ።

እባካችሁን ለእኔም መጸለይ እንዳትረሱ

እግዚኣብሔር ምያማርን ይባርክ!

 








All the contents on this site are copyrighted ©.