2017-11-29 16:04:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከምያንማ ርእሰ ብሔር እና ከመንግሥት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒ. አውን ሳን ሱ ጋር ተገናኙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በምያንማር እያካሄዱት ያለው ዓለም አቀፋዊ ሐዋrያዊ ዑደት በመቀጠል hዳር 18 ቀ 2010 ዓ.ም. ከያንጎን  በአይሮፕላን ተጉዘው በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከአንድ ሰዓት በረራ በኋላ ልክ 9 ሰዓት ላይ በአዲሲቷ የምያንማ ርእሰ ከተማ ንያ ፕዪ ታው ደርሰው የአገሪቱ መንግሥት ባቀረበላቸው ይፋዊ የእንኳን ደህና መጡ ሥነ ስርዓት ተሳትፈዋል።

ቅዱስነታቸው በቀጥታ ለአገሪቱ መንግሥት እና ሕዝብ ክብር ወደ የርእሰ ብሔር ሕንፃ በመሄድ እዛው ከርእሰ ብሔር ህቲን ክያው ጋር ከተገናኙ በኋላ ቀጥለውም ከመንግሥት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ኡውንግ ሳን ሱ ክዪ ጋር መገናኘታቸው ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

በዚህ ክሌአዊ ግንኙነትም ቅዱስ አባታችን በቤተ መንግሥት እንደ ደረሱም ርእሰ ብሔር ህቲን ክያው በጋራ ወታደራዊ የሙዚቃ ጓድ ለብራችው ያቀረበው ወታደራዊ ብሔራዊ መዝሙር ተደምጦ ይፋዊ ፎቶ ከተነሱም በኋላ ወደ ቤተ መንግሥት ገብተው ቅዱስነታቸው በክብር መዝገብ ፍሪማቸውን አኑረዋል።

የምያንማር እና የአገረ ቫቲካን ሰንደቅ ዓላማዎች ወደ ተኖረበት አቢይ ክፍል ውስጥ ገብተው ይፋዊ የሁለቱ አገሮች ግኑኝነት የሚወሳ ዳግም ፎቶ ከተነሱ በኋላ፡ ቅዱስ አባታችን እና ርእሰ ብሔር ህቲን ክያው ክሌአዊ የግል ግኑኝነት ማከናወናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅዱስ አባታች በመቀጠል ከመንግሥት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒ. አውንግ ሳን ሱ ክዪ ጋር ግላዊ ግኑኝነት እንዳካሂዱም ጠቅሶ፥ ኡንግ ሳን ሱ ክዪ፥ ይኽ ግንኙነት በመግሥታዊ ሥልጣንና በሰላም የመረጋገጥ ሂደት ላይ ያለንን እማኔ የሚያረጋግጥ ነው  እንዳሉ ሲያመልክት፡ በራክሂነ ክልል ያለውን ወቅታዊው ቀውስ ተጠቀሰ ሃሳብም ያስደመጡ ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ሰላም እንዲረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ሁሉ ሊበረታታ ይገባዋል ሲሉ፡ ሳን ሱ ክዪ በበኩላቸውም፥ በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ የቶክስ አቁም ስምምነት መሠረት ያደረገ የነበረው መንግሥት የጀመረው የሰላም የውይይት ሂደት እንዲቀጥል የወቅቱ መንግሥት ፍላጎት እና አላማም ነው እንዳሉ ይጠቁማ።

የሰላሙ ጉዞ ዘወትር ቁልቁለት አይደለም ሆኖም ግን ቅንና የበለጸገች መጠጊያ ኵራት እና ሃሴት የሆነቸውን የሕዝብ የሆነች አገር ለማስጨበጥ ያለውን ፍላጎቱ እውን ለማረግ ብቸኛው መንገድ እርሱ ነው፡ የመጪው ትውልድ መጻኢ ዋስትና እንዲኖረው ሰላም የመሻቱ ሂደት ተቀባይነት ባለው የልማት እና የእድገት እቅድ አማካኝነት መበረታታት ይኖርበታል እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.