2017-11-28 09:23:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምያንማር ደረሱ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ህዳር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ምያንማር ርእሰ ከተማ ያንጎን በሚገኘው የአይሮፕላን ማረፊያ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት ልክ 04 ሰዓት ላይ ደርሰው በምያንማር እና በመቀጠልም ወደ ባንግላደሽ የሚያደርጉት 21ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በይፋ ጀምረዋል።

ቅዱስ አባታችን በአየር ማረፊያው እንደደረሱም ወደ አይሮፕላኑ ውስጥ በመግባት በታይላንድ ካምቦጃ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በላኦስ ደግሞ ሐዋርያዊ ወኪል በሆኑት በብፁዕ ኣቡነ ፓውል ቻንግ ኢን ናም እና የቅድስት መንበር እና የምያንማር የክሌአዊ ግኑኝነት ሥነ ስርዓት ተጠሪ አማካኝነት ታጅበው ከአይሮፕላኑ እንደወረዱ እዛው ይጠባበቁዋቸው በነበሩት በምያንማር ረፓብሊካዊት ርእሰ ብሔር ህቲን ክያዋ ልዩ ሚኒስትር በምያንማር አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት እና ወደ መቶ በሚገመቱ ሕፃናትና ባህላዊ ልብስ ለባስያን የምያንማ ብሔር ብሔሮችን በወከሉት እና በመንግሥት ሰልፈኛው ክቡር ዘብ አቀባበል እንደተደረገላችው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው በቀጥታ ያንጎን ወደ ሚገኘው ወደ ሊቀ ጳጳሳዊ ሕንፃ ደርሰው በግል መሥዋዕተ ቅድሴ አሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው ወደ ምያንማር ባደርጉት የአይሮፕላን ጉዞ የበረራ ድንበሮቻቸውን ላቋረጡባቸው አህጉራት፥ ለኢጣሊያ ረፓሊክ ርእሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ፡ ለርእሰ ብሔሩ እና ለኢጣሊያ ሕዝብ ጸሎታቸውን በማረጋገጥ ሕዝብ የጋራ ጥቅም መሻት ላይ በጸና ተስፈኛ መጻኢ ላይ እንዳያተኵር በዚህ ወደ ምያንማር እና ወደ ባንግላደሽ የማደርገው በሁለቱ አህጉራት ለሚገኙት አናሳ የካቶሊክ ምእመናን በእምነት ለማጽናት እና ለማበረታታት ያለመው በሰላም ነጋዲ ጎዞዮ ለእርስዎ ክቡር የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ሰላታዮን አስተላልፋለሁ የሚል የተሌግራም መእክት እንዳስተላለፉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ህኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ተመሳሳይ የተሌግራም መልእክት የአየር በረራ ድንበሮቻቸውን ላቋረጡባቸው ለክሮአዚያ ለቦስኒያና ኤርዘጎቪና ለሞንተ ነግሮ፡ ለሰርቢያ፡ ለቡልጋርያ፡ ለቱርክ፡ ለጆሪጂያ፡ ለአዘርባጃን ለቱርክመንስታን ለአፍጋኒስታን ለፓኪስታንና ለሕንድ መራሔ መንግሥታት ማስተላለፋቸው ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.