2017-11-27 14:51:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በማያንማር እና በባንላዲሽ የሚያደሩትን 21 ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ጀመሩ።


ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በዛሬው እለት ትኩረት ሰጥተን ወደ እናንት የምናደርሰው ዘገባ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በማያንማር (የቀደሞ ስሟ በርማ)እና በባንላዲሽ ከኃድር 17 እስከ ኅዳር 23/2010 ዓ.ም. ድረስ የሰላም ልዑክ በሚል መሪ ቃል የሚያደሩትን 21 ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት የተመለከቱ ዘገባዎችን በሰፊው ወደ እናንተ እናቀርባለን።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በማያንማር እና በባንግላዲሽ ከኅዳር 17 እስከ ኅዳር 23/2010 የሚያደርጉትን ጉብኝት በትላንትናው እለት ማታ ጀምረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህንን 21ኛ ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት እንደ ተለመደው ማንኛውንም ዓይነት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ከሮም ከተማ በሚወጡበት እና ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እምብርት ላይ በሚገኘው እና በአውሮፓ በማሪያም ስም ከተሰየሙት አብያተ ክርስቲያን መካከል በትልቅነቱ በሚታወቀው፣ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ግንባታው እንደ ተጠናቀቀ በሚነገርለት በሳንታ ማሪያ ማጆሬ በተክርስቲያን ተገኝተው ይህ ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው የሰመረ ይሆን ዘንድ፣ በሚጎበኝዋቸው ሀገራት ውስጥም ሳይቀር ሰላም እና ፍቅር ይስፈን ዘንድ ጉዞዋቸውን ለማሪያም በደራ በመስጠት የእንደ ሚጀምሩ፣ በተመሳሳይ መልኩም ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅትም ሳይቀር በዚሁ ቤተክርስቲያን በመገኘት ለእግዚኣብሔር ምስጋናን ያቀርባሉ፣ በዚህም መስረት በትላንትናው እለት አመሻሹ ላይ በዚሁ በሳንታ ማሪይ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ጸልት አድርሰዋል።

ቅዱስነታቸው ባሳንታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ጸሎት ካደርሱ ቡኃላ በትላንትናው እለት በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5:40 ላይ በሮም ከተማ ከሚገኘው እና በ15ኛው ክፍለ ዘመን በኖረው የጌታን የመጨረሻ እራት እና ሞናሊዛን በመሳሰሉ ድንቅ በሆኑ ስዕሎቹ በሚታወቀው ብሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ስም ከተሰየመው ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማርፊያ በመነሳት ጉዞዋቸውን ጀምረው 8584 ኪሎ መትሮችን በአየር ላይ አቋርተው የ10፡20 ደቂቃ ጉዞ ካደረጉ ቡኃላ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 4 ሰዓት ላይ በማያንማር ዋና ከተማ ያንጎን በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአየር ማርፊያ በሰላም አርፈዋል።

ቅዱስነታቸው በማያንማር ለሚያደርጉት ጉዞ የመረጡት አርማ በልብ ቅርጽ የተሰራ እና በላዩ ላይ ሰላም እና ፍቅር የሚል ጹሑፍ የታተመበት ሲሆን በዚሁ የልብ ቅርጽ ውስጥ ደግሞ በግራ በኩል የማያንማር ሪፖብሊክ የሀገሪቷ ካርታ በቀኝ በደኩል ደግሞ የሰላም ምልክት የሆነውን  ነጭ እርግብ በእጃቸው ላይ በማይዝ ቅዱስነታቸው የተነሱት ፎቶ ታትሞ ይገኝበታል። ይህም አርማ በሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች መካከል ያለውን ልዩነት፣ ይህም ማለት አብዛኛው የማይንማር ማሕበረሰብ የቡዳ እምነት ተከታይ ነው፣ ቅዱስነታቸው የሚወክሉት ደግሞ የክርስቲያን ማሕበረሰቡን ነው፣ በሁሉቱ ማሕበረሰቦች ዘንድ ልብ ለልብ የሚያገናኝ  በፍቅር እና በሰላም የታጀበ ግንኙነት ይኖር ዘንድ ምኞቱን የሚገልጽ እና ይህንንም ምኞት በይፋ የሚያበስር  አርማ ነው።

በቫቲካን እና በማያንማር መካከል ስላለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና ትብብር

ቫቲካን እና ማያንማር ሪፖብልክ ኦፊሰሊያዊ የሆነ ግንኙነት የጀመሩት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 4/2017 ዓ.ም. (ከሰባት ወራት በፊ ማለት ነው)በዚሁ ዓመት እንደ ተጀመረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የቅድስት መንበርን በመወከል ከሀገሪቷ ጋር አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያደረገች የምትገኘው በአሁኑ ወቅት የታይላንድ፣ የካንቦዲያ እና የላዎስ የቅድስት መነበር አባሳደር በሆኑት በአቡነ ፖል ቻንግ ኢ ናም ለማያንማር የቫቲካን ልዩ ልዑክ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአሁኑ ወቅት በማያንማር በቁጥር አናሳ በሆኑ ሮሂንጋያ የሙስሊም ማኅበረሰብ ላይ በአገሪቱ የሚገኙ በአንድ አንድ አካራሪ የቡዳ እምነት ተከታዮች አማካይነት እየተፈጸ የሚገኘውን አሰቃቂ ጥቃት በማውገዝ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለሆኑት እና በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ለሆኑት ሳን ሱ ኪ በቁጥር አናሳ በሆኑት የሮሂንጋያ የሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ጣቅት በማውገዝ ሰላም እና እርቅ እንዲፈጠር በተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የማያንማር ፕሬዚዳንት የሆኑትን ሳን ሱ ኪ ን በቫቲካን ጋብዘው በሁለቱ ሀገራት የወደ ፊት ግንኙነት እና በእነዚህ በቁጥር አናሳ የሆኑት የሮሂንጋያ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ላይ እየተቃጣ የሚገኘው ጥቃት ባስቸኳይ ይቆም ዘንድ እና ብሔራዊ እርቅ ይደረግ ዘንድ ይህንንም በተመለከተ በግል ተገናኝተው መወያየታቸው የሚታወስ ሲሆን በአንድ አንድ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን እና ፕሬዚዳንት ሳን ሱ ኪም ቅዱስነታቸውን በኅዳር ወር ውስጥ ማያንማርን እንዲጎበኙ ጥሪ እንዳደረጉላቸው ያታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በማይንማር የሚያደርጉት በ21ኛ ሐዋሪያዊ ግብኝታቸው በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተደረገ የመጀመሪያ ታሪካዊ ጉዞ ነው። በዚሁ ግቡኝታቸው ለቅዱስነታቸው ትላቁ ፈታና የሚሆንባቸው ነገር ቢኖር በአሁኑ ወቅት ከ600,000 ሺ በላይ ሰዎችን ለስደት እና ለመከራ የዳረገው በቁጥር አናሳ በሆኑት የሮሂንጋያ የሙስሊም ማሕበረሰቦች ላይ የተቃጣው ጥቃት ነው። ቅዱስነታቸው ይህንን ጥቃት በተደጋጋሚ አውግዘዋል። ነገር ግን አሁን አወዛጋቢ የሚሆነው ጉዳይ “ሮሂንጋያ” የሚለው የእነዚህ በቁጥር አናሳ የሆኑ የሙስሊም ማሕበረሰብ መጠሪያ መጠቀም እንደ ሌለባቸው የማያንማር ባለስልጣናት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን አሳስበዋል። በሀገሪቷ የሚገኙ ብቸኛው ካርዲናልም ቅዱስነታቸው ይህንን የመጠሪያ ስም ባይጠቀሙ ይሻላ የሚል የበኩላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል። ምክንያቱም “ሮሂናጋያ” የሚለው መጠሪያ የአንድ የማያንማር ጎሳ መጠሪያ ነው። ነገር ግን አብዛኛውን በማያንማር የሚኖሩ የቡዳ እምነት ተከታዮች እነዚህ በቁጥር አናሳ የሆኑ በማያንማር የሚኖሩ  የሙስሊም እምነት ተከታዮች በስደት ከባንግላዲሺ ወደ ማያንማር የገቡ በመሆናቸው የተነሳ ይህ “ሮሂንጋያ” የሚለው የማያንማር አንድ ጎሳ መጠሪያ ስም በመሆኑ፣ ለእነርሱ ይህ የመጠሪያ ስም አይገባቸውም በማለት እየሞገቱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ቅዱስነታቸው ይህንን የመጠሪያ ስም ከተጠቀሙ በብዙኃኑ የቡዳ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣ ይቀሰቅሳል የሚል ስጋት ፈጥሩዋል። ነገር ግን ቀደም ባሉት ጊዜያት ቅዱስነታቸው “በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን የሮሂንጋያ ማሕበረሰብ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እና ስደት ይብቃ!” ማለታቸውም ይታወስል።

የማያንማር (የቀድሞ ስሟ በርማ) አጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ በአጭሩ

ማያንማር እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ 54.4 ሚልዮን ሕዝብ ብዛት እንዳላት የተገለጸ ሲሆን በዋና ከተማዋ ያንጎን 4,800, 000 ሺ ሰዎች ይኖራሉ። ዋና ከተማው “ያንጎን” የሚለው መጠሪያ ያገኘው እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1755 ዓ.ም. በወቅቱ በሀገሪቷ ሲካሄድ የነበረ የእርስ በእርስ ጦርነትን ማብቂያን አስመልክቶ የተሰጣት ስያሜ ሲሆን ይህም በሀገሪቷ ቋንቋ  “የግጭቶች ማብቂያ” የሚል ትርጓሜ አለው። ያንጉን የሀገሪቷ ዋና ከተማ ከመሆኑዋ ባሻገር ከፍተኛ የሆነ የእንዱስትሪ እና መዋለ ነዋይ የሚንቀሳቀስባት ቦታ እንደ ሆነች ይታወቃል።

አብላጫው የሀገሪቷ ሕዝብ የቡዳ እምነት ተከታይ ሲሆን ኢኮኖሚያቸው መሰረቱን ያደርገው በከፍተኛ ሁኔታ እየተመረተ በሚገኙ የሩዝ፣ የጣውላ እና የመዕድናት ምርት ላይ እንደ ሆነም ለመገንዘብ ችለናል።

በማያንማር ዋና ከተማ በያንጎን የሚገኘው የካቶሊክ ሀገረ ስብከት በይፋ የተመሰረተው እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በጥቅምት 8/1991 ዓ.ም. ሲሆን በዚሁ ርዕሰ ሰባካ (Metropolis) ውስጥ ከሚኖሩ 12,191,500 ሕዝብ ወስጥ 62,490 የካቶሊክ ምዕመናን 42 ቁምስናዎች፣ 8 ትላልቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ 89 የሀገረ ስብከት ካህናት፣ 23 ደናግላን 47 የዘርዐ ክህነት ተማሪዎች 72 የተለያዩ ማኅበራት፣ 382 የሴቶች ገዳም አባላት፣ 23 የትምሕርት መስጫ ተቋማት፣ 18 የእርዳታ መስጫ መዕከላት ይገኝእሉ። በዚህ በያዝነው ዓመት ብቻ 1,207 ምዕመናን መጠመቃቸው ታውቁዋል። የሀገረ ስብከቱን በበላይነት የሚመሩትም የ69 አመቱ ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል ቻርለስ ማኡንግ ቦ ናቸው።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.