2017-11-24 15:26:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ወደ ባንግላድሽ የዕርቅ የምሕረት እና የሰላም ምልክት


እ.ኤ.አ. ከሕዳር 30 እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በእስያ ክፍለ ዓለም በምትገኘው አገረ ባንግላደሽ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚዘከር ሲሆን። ቅዱስነታቸ ይኸንን በቅርቡ የሚያከናውኑት ክፍለ ዓለማዊ ጉዞ ምክንያት በማድረግ በባንግላደሽ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን ልኡካነ ወንጌል እ.ኤ.አ. ሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የድምጸ ምስል መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኰ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው በዚያች አገር ካለው ከጠቅላላው ህዝብ ብዛት ውስጥ 0.4% የሚሸፍነው ካቶሊክ ምእመንን፥ እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አገልጋይ ወደ እናንተ ዕርቅ ምሕረትና ሰላምን ላበስር እመጣለሁ፡ በእምነት እና የሁሉም ሰብአዊ ክብር እንዲከበር ሁሉም ልቡን በመክፈት እርስ በእርሱ በመቀባበልና በመፈቃቀር በተለይ በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ማስተናገድ በሚለው ወንጌላዊ ምስክርነት በምኖሩት ተልእኮአችሁ ለመጽናት ወደ እናንተ እመጣለሁ በማለት ቅዱስነታቸው በዚያ ባስተላለፉት የድምጸ ምስል መልእክት ገልጠው፥

የጋራ መረዳዳት እና የርእር በእርስ መከባበር ለማነቃቃት

ቅዱስነታቸው አያይዘውም የመላ የባንግላደሽ ሕዝብን በማሰብ፥ ከእናንተ ከባንግላደሽ ሕዝብ ጋር ለመገናኘት ምኞቴ ነው። በተለይ ደግሞ በአገሪቱ ከሚገኙት እርስ በእራስችንም እንደ አንድ ሰብአዊ ቤተሰብ ለመደጋገፍ  የጋራ መግባባትና የእርስ በእርስ መከባበር እንዲያነቃቁ ከተጠሩት ከሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት መሪርዎች እና መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር ለመገናኘት ምኞቴ ነው፡ እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኰ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት የድምጸ ምስል መልእክታቸውን፥ በባንግላደሽ ለማከናውነው ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዋጣለት እንዲሆን ቅድመ ዝግጅቱን በማካሄድ ላይ የሚገኙትን ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ፡ ከእናንተ ጋር እንድገናኝም የተስፋ እና ለሁሉም የማበረታታቻ ምልክት ሆኜ እንድገኝ ከእናንተ ጋር ስለ ምቆይባቸው ቀናት ሁሉ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ እኔም ስለ እናንተ ብለው በእናንተ እና በቤተሰቦቻችሁ ላይም መለኮታዊው የደስታ እና የሰላም ቡራኬ እማጸናለሁ!  በሰላም ያገናኘን በማለት ማጠቃለላቸው አስታወቁ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ወደ ባንግላደሽ ለሐዋርያዊ ጉብኝት ከመጓዛቸው በፊት እ.ኤ.አ. ክ አህዳር 27 ቀን እስከ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአገረ ምያንማር ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያከናወኑም ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኰ በማስታወስ ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.