2017-10-19 09:28:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ፍራንቸስካውያን ለ800 ዓመት በቅድስት መሬት የሰላም ምስክሮች


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በቅድስት መሬት የፍራንቸስካውያን ወንድሞች ማኅበር ህላዌ 800ኛ ዓመቱ ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት፥ “ለመላው ሕዝበ እግዚአብሔር ልኡካን ናችሁ። በተጋ ጸሎትና አስተንትኖ በድኽነትና በትህትና ለሮማ ጳጳስ ታዥን በመሆን በቅድስት መሬት ከተለያዩ ባህሎችና ጎሳዎችና ሃይማኖቶች የተወጣጡትን ወንድሞች በሚገኙበት ክልል ሰላም ወንድማማችነትና መከባበርን መስካሪያን ናችሁ” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ይኽ በቅድስት መሬት ስምንት መቶኛውን ዓመቱን እያስቆጠረ ያለው የፍራንቸስካውያን ህላዌ ከዚያ እ.ኤ.አ. ግንቦት 14 ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስ በተከበረበት ዕለት 1217 ዓ.ም. በአሲዚ ተካሂዶ ከነበረው የፍራንቸስካውያን ወንድሞች ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ ጋር ጥብቅ ትሥሥር ያለው እርሱም ከዚያ ጠቅላይ ጉባኤ ማኅበሩ ለወንጌላዊ ልኡክነት አገልግሎትና ለኵላዊነት አድማስ ክፍት እንዲሆን ከተወሰነበት ታሪክ ጋር የተቆራኘ መሆኑ ቅዱስነታችን ባስተላለፉት መልእክት ዘክረው እ.ኤ.አ. በ 1217 ዓ.ም. ጸደይ ወቅት ላይ የፍራንቸስካውያን ማኅበር ወንድሞች በወንድም ኤሊያ ዘኮርቶና ተመርተው አክሪ በመግባት ያንን ወንድማማችነትና ሰላምን የመመስከር ታሪክ አንድ በማለት መጀመሩንም አስታውሰው፥ ይኽ የፍራቸስካውያን ህላዌ በቅድስት መሬት በተለያየ ወቅት ለሚሄዱት መንፈሳውያን ነጋዲያን ከቅድስት መሬት ጋር የማስተዋወቅ በማሰተናገድ በቅድስት መሬት ቅዱሳት ሥፍራ በማስጎብኘትና መንፍሳዊ መርሓ ግብሮችን በማቅረብ የሚይፈጽሙት አገልግሎት የሚያጎለብት መሆኑም ጠቅሰው። ለሥነ ቅዱሳት ቅርስ የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ ምርምርና ጥናት የሚካሄድባቸው መናብርተ ጥበብ በማቋቋም ለክልሉ ማኅበረ ክርስቲያንና ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በተለያየ ዘርፍ በማገልገል በተለይ ደግሞ በከተሞች ዳር ለሚኖርት ለድኾችና ለተረሱት የኅብረተሰብ አባላትን ቅርብ በመሆን የተለያዩ አገልግሎት በማቅረብ የምስራቅ ሥርዓት ለሚከተሉት አቢያተ ክርስቲያን ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በመደገፍ ለቅድስት መንበር የትብብርና የድጋፍ ምጽዋት በማሰባሰብ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት ሕያው ሆኖ እንዲቀጥል በሚደረገው ጥረት ሁሉ የላቀ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው ቅዱስ ፍራንቸስኮ፥ ወንድሞቼ ወደ ተለያየ የዓለም ክልል ለተልእኮ ወንጌል ሲላኩ የቃላት ሹክቻ እርስ በእርስ ከመጋጨት ተቆጥበው ሌሎችን ካለ መፍረድ ትሁታን ሰላማውያን ቅንነት የተሞሉ በድኽነት የሚኖሩ ይሁን ሲል የሰጠው ምክር አስታውሰው ትህትና ሰላምና ፍቅር መለያችሁ ይሁን እንዳሉ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.