2017-09-28 12:00:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይፍዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ክርስቲያናዊ ተስፋ ርእስ ዙሪያ የጀመሩትን ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል፡ በዚህ ከውጭና ከውስጥ የጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስየተስፋ ጠላቶች ንኡስ ርእስ ዙሪያ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሆርውን ከመጀመራቸው በፊት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ለተሰበሰበውን ምእመን እየተዘዋወሩ ሰላምታን አቅርበው አስተምህሮው ወደ ሚለግሱበት መንበረ ር.ሊ.ጳጳሳት ደርሰው፥

ወድ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደምን አደራችሁ በማለት እንደ ወትሮው ልሙድ ሰላምታቸውን ካቀረቡ በኋላ

ዛሬ ከእናንተው ጋር አብሬ ስለ የተስፋ ጠላቶች ዙሪያ ለማስተንተን እፈልጋለሁ። በዚህ ምድር ለማንኛውም መግባረ መልካም ተጻራሪና ጠላት እንዳለው ሁሉ ተስፋም ጠላቶች አሉት።

ይኽንን በምልበት ሰዓት የፓንዶራ ሳጥን በመባል የሚጠራውን የሁሉም ክፋቶች ማደሪያ ተብሎ ይገለጥ የነበርው ግሪካዊ አፈታሪክ እንዳስታውስ አድርጎኛል፡ ግሪካዊው ገጣሚ ኤሲዶ ተግባሮችና ቀናቶች በተሰኘው ድረሰቱ እንደሚገልጥልን ዘውስ ሳጥኑን ለፓንዶራ ሲያስረክብ፡ የሳጥኑን መክደኛ አደራ እንዳትከፍቺ ብሎ ነበር ያስጠነቀቃት፡ ሳጥኑ ሲከፍቱት የተለያዩ መቅሰፍቶች ይከሰቱ ነበርና፡ ነገር ግን በመጨረሻ ሳጥኑ ተከፍቶ ሁሉ አለ የሚባል በውስጡ ታጉረው የነበሩት መቅሰፍቶች ወጥተው ተሟጠው ካለቁ በኋላ አንድ የተስፋ ጭላንጭ ብቅ ማለት ይጀምራል። ያንን ፓንዶራ አቅባው የነበረው መልካም ምግባር ይኸንን ያስተዋለቸው የመጨረሻዋ ሰው እርሷም ነበረችና ይኸንን ያስተዋሉ ግሪካውያን ኤልፒስ በማለት ይጠሩዋታል፡ ትርጉሙም ተስፋ ማለት ነበር፡ ይኽ አፈታሪክ የሰው ልጆች ተስፋ እንዲያደርጉ በጣም አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ይገልጥልናንል።

በልማዳዊው አባባል ሕይወት እስካለ ድረስ ተስፋ አለ ይባላል። የተሳሳተ አባባልም ነው፡ ምናልባት እውነታው መሆን ያለበት ልማዳዊ አባባሉን በተቃራኒ ማስቀመጥ ነው፡ ማለትም ሕይወትን የሚያቆመው ተስፋ ነው፡ ሕይወትን የሚያቆም የሚያቅብ ተስፋው ነው። ሰው ተስፋን ባይኰተኩት በዚህ መልካም ምግባር ባይደገፍ በእውነት ከዋሻው ዘመን ባልወጣ፡ በዓለም ታሪክ ውስጥ ጨርሶ ዱካው ሳያተው ባለፈም ነበር። ከዚህ እጅግ የመጠቀ በሰዎች ልብ ውስጥ ህልው የሆነው የመለኮት ህላዌ መግለጫ ሌላ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም።

አንድ ቻርለስ ፐጉይ የተባለው ፈረንሳዊ ገጣሚ በተስፋ ዙሪያ የድረሳቸው ብዙ የሚያስደንቁ የግጥም ገጾች ትቶልን አልፏል። የሁለተኛው የበጎነት ሚስጥር ታዛ (በረንዳ) በሚል ርእስ ሥር ያደረሰው ግጥም ማየቱ ይበቃል። በዚህ በደረሰው የግጥም መጽሓፉ ውስጥም፥ እግዚአብሔር ሰዎች ባላቸው እምነትም ሆነ በሚፈጽሙት ሰብአዊነት (ግብረ ሠናይ) ሳይሆን ባላቸው ተስፋ ነው እጹብ በሆነ መደነቅ በጥልቅ በስሜት የሚነካው ሲል ያመላክትልናል።

“እነዚያ ድኾች ልጆች” ይላል ፐጉይ በግጥሙ፥ “እነዚያ ድኾች ልጆች ሁኔታዎች እንዴት እንደሚሄዱ ይመለከታሉ፡ ነገር ግን ነገ የተሻለ ይሆናል ብለው ያምናሉ” ሲል ጽፍፏል። ኣዎ አርሶ አደረሩ ድኻ ሠራተኛው የተሻለ ወደፊት የሚፈልጉ ስደተኞች ሁሉ ምንም’ኳ በሚያጋጥማቸው ችግር ምክንያት ምሬት ያለባቸው ቢሆም ቅሉ እንደ ሁሉም ድኻ፥ ልጆቼ ከዚህ እኔ ካለሁበት ሕይወት የተሻለ ቅንና የተረጋጋ ሕይወት እንደሚኖራቸው በማመን ተስፋ ተነቃቅተው ከዚህ ዓለም ያልፋሉ።

ተስፋ ቤቱንና ንብረቱን አንዳንዱም ቤተሰብን ዘመዶች እራሳችውን ከሚወዱዋቸው ሰዎች ተነጥለው የሕይወት ልክነት ያለው ሕይወት ለእራሱና ለሚያፈቅራቸ ሁሉ በማሰብ ለተሻለ የሕይወት ፍለጋ የሚያነቃቃ ግፊት ነው። ይኽ የተስፋው ግፊትም በዚያ በሚያስተናግደው ሰው ልብ ውስጥ ለማገናኘት ለመወያየት እራስን አስተዋውቆ ሌላውን ለማወቅ ባጠቃላይ ለመተዋወቅ የሚያነቃቃውም ነው። በስደተኛውና ባስተናገጁ ልብ ውስጥ ያለ ግፊትም ነው፡ የዚያ የተለያዩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የግብረ ሠናይ ማኅበራትን የሚያቅፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ “የጎዞ ተካፋይ” በሚል መርሕ ቃል የስደተኛውን ሕይወት በስደተኛው ውስጥ ሆኖ በመኖር ያንን የስድተኛውን ትመክሮ በመኖር አብሮ መጓዝ ስደትኛውን ለማሰናገድ ያነቃቃል። ስለዚህ በሕይወት ጉዞ ተካፋይ መሆን ሊያስፈራን አይገባም። ተስፋን ለማጋራት አንፈራም፡ የሚለውን እማኔ የሚያረጋግጥ ነው።

ተስፋ ለከርሰ ጠገብ ለሆኑ ሰዎች የሚመለከት ክቡር እሴት ውይንም መልካም ምግባር አይደለም። ለዚህም ነው ከጥንተ ታሪክ ጀምሮ ተስፋን ሰንቀው ይጓዙና ይኖሩ የነበሩት ድኾች መሆናቸው የሚነገረው፡ እግዚአብሔር ወደ ዓለም ይገባ ዘንድ እነዚህ ተስፋን ሰንቀው የሚጓዙት ድኾች መረጠ፡ ዮሴፍና ማርያም የቤተልሔም እረኞች እስፈለጉት። ጌታችን በተወለደባት ሌሊትም አንድ ያንቀላፋ የተኛ የዛለ ገዛ እራሱን ከሁነቶች ጋር አላምዶ በይገባኛል ርእሰ መተማመን ተተብትቦ ይኖር የነበረ አንድ ዓለም ነበር፡ ባንጻሩ ግን እዩልኝ ስሙልኝ ሳይሉ የመልካም ምግባር አብዮት ያሰናዱና ለዚህ አዲስ አብዮት መንገዱን ያቀኑ የነበሩ የተናቁና ድኾች ነበሩ። ምንም ነገር ያልነበራቸው፡ አንዳንዱ ደግሞ በመትረፍ በድኽነት ጣራ ስር ሆኖ ዕለታዊ ኑሮውን ይመራ የነበረውም ነው። ሆኖም እነዚህ ድኾች ዓለም መለወጥ የሚል እጅግ ድንቅ የሆነ መልካም ሃብት ውጭ ሌላ ሃብቴ የሚሉት ነገር ምንም ያልነበራቸው ሰዎች ናቸው።

አንዳንዴ በሕይወት ሁሉን ነገር እግኝቶ መኖር አደጋ ነው፡ መጠባበቅና ትዕግስት የተሰኙት እሴቶች ያልተላለፈለትና በዚሁ ጉዳይ ያልታነጸ ጥሮና ግሮ ማግኘት ያልተለማመደ፡ ሁሉን ነገር አለ ምንም ላብ ሊኖረው የቻለ፡ እንደ ሰው መከወን የሚገባው እርምጃዎችን ለመፈጸም ያልቻለ፡ ገና በ 20 ዓመት ዕድሜዎች ውስጥ ዓለም እንዴት እንደሚሄድ የሚያውቅ፡ ምንም ነገር ላለ መመኘት ፍርድ የተዳረገ በልቡ ውስጥ ጸደይ የጠለቀበት ወጣት አስቡ።

ባዶ የሆነች ነፍስ ለተስፋ እጅግ የከፋ እንቅፋት ነች። ከዚህ ዓይነቱ ፈተና ማንም ነጻ ነኝ ለማለት የሚችል አንድም’ኳ የለም፡ ይኽ ፈተናም ተስፋን የመቃወም ፈተና በዚያ ክርስቲያን ነን ብለን በምንጓዝበት ክርስትያናዊ ሕይወት ሊያጋጥም ይችላል። ጥንታውያን መነከኮሳት የአንድ ሕይወት ቁርጠኝነት የሚያዝል ዋነኛ ጠላት ያንን ታታሪነትን ከሕይወት የሚያገል እርሱም የሐሰት ጌታ እርሱም ዲያብሎስ ነው በማለት ይገልጡት ነበር። ይኽ ፈተና ይደርሳል ብለን በማንስብበት ሰዓት ይከሰታል። ዕለታዊ ሕይወታችን አሰልቺና ጥሮና ግሮ መኖርን ዕለታዊ ድካምን ሁሉ ዋጋ ቢስ ነው እንድንል ያደርገናል። የቤተ ክርስቲያን አበውም ይኸንን ውስጣዊ ሕይወትን ባዶ ቀፎ እስኪሆን ድረስ የሚሸረሽር ስንፍና ወይንም ለገምተኛ ተግባር በማልትም ይገልጡታል።

ይኽ  በሚከሰትበት ጊዜ ክርስቲያኖች መታገል እንጂ በሕይወታችን ውስጥ ስንፍና ለማዳ ማድረግ አይገባንም። እግዚአብሔር የፈጠረን ለሐሴትና ጥሮ ግሮ ለመኖርም እንጂ በአስተካዥ ሃሳብ ውስጥ እንድንንከባለል አይደለም። ለዚህም ነው ማንኛውም ከዚያ ከእግዚአብሔር ሊመጣ ፈጽሞ ከማይችለው ውስጠ ኃይላችንን ከሚያዝል የሐሴት አልቦነት ፈተናንን በመቃወም ልባችንን ከዚህ ፈተና አቅቦ መኖር እጅግ አስፈላጊ የሚሆነው።

በዚያ ውስጣዊ ኃይላችንን ከሚያረግፍ ስንርቅና በተለይ ደግሞ እጅግ ከባድ የሆነውን ጭንቀታምነትን በመቃወም ለመገሰጽ በምናደርገው ትግል ወደ ኢየሱስ መቅረብና ከእርሱ ጋር መሆን አለብን። ያንን በወንጌል ምልከታውን የምናገኝለት የሁሉም ለክርስትያናዊ መንፈሳዊነት ባህሎች የማእዝን ድንጋ የሆነውን፥ “የእግዚአብሔር ልጅ ጌታዮ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፡ ሐጢአተኛ ነኝና ማረኝ” የሚለውን ያልተወሳሰበውን ጸሎት እንድገም።

በተስፋ መቁረጥ ውጊያ ውስጥ ብቻችን አይደለንም። ለብቻችን አይደለንም። ኢየሱስ ዓለምን ካሸነፈ መልካምን ሁሉ የሚቃወሙትን በሙሉ በእኛ ውስጥ ሆኖም ያሸንፋል። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ያንን በሕይወት ለመኖር የሚያስፈልገንን መልካም ምግባር ማንም ከልባችን ሊነጥቀን አይችልም። ተስፋን ሊሰርቅብን የሚችል ማንም የለም በማለት የለገሱትን የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው አስተምህሮውን ለመቀበል ለተገኙትን ሁሉ ደግመው ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበት ማሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.