2017-09-23 09:22:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኢጣሊያ የጸረ የወንጀል ቡድኖች (ማፊያ) ድርገት አባላትን ተቀብለው አነገሩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢጣሊያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ጣምራው የጸረ ወንጀል ቡድኖች (ማፊያ) ድርገት አባላት በድርገቱ ሊቀ መንበር ሮዛ ቢንዲ ተሸኝተው አገረ ቫቲካን የገቡትን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት ንግግር በቀጥታ በኢጣኢያ በጸረ የወንጀል ቡድኖች ትግል ሕይወታቸውን የሰዉ ዜጎች የመንግሥት አካላት የሕግና ፍትሕ ጉዳይ አባላትን እንደ የሕግ ዳኛ ሮሳሪዮ ሊቫቲኖ፡ ዳኞች ጆቫኒ ፋልኮነና ፓውሎ ቦርሰሊኖ በማስታወስ በቀጥታ በግለሰብ ደረጃም ሆነ እንደ ተቋም እያጠቃ ያለው የግብረ ገብ ቀውስ ላይ በማነጣጠር የሰው ልጅ ከእራስ ወዳድነት ካስመሳይነት ላድር ባይነት ሙስናና ማጭበርበር ከተሰኙት ተግባሮችና ከህግ በላይ ሆኖ መኖር ከሚለው ፈተና እንዲጠበቅ አደራ እንዳሉ ጂሶቲ አመለከቱ።

አቅጣጫውን  የሳተ ለግልና ለአንዱ ወገን ጥቅም ያደላ ግልጽ ያልሆኑ ስምምኖቶችን የሚከተል ፖለቲካ ሕሊናን የሚያጨልም ተግባር ልሙድና እንደ ተራ ነገር ብሎ የሚያስብ እውነትንና ሐሰትን የሚያደባልቅ የተሰጠው ኃላፊነት ለእራስ ጥቅም በማጠፍ ዜጎችን የሚክድ ነው፡ ከዚህ በተቃራኒ እውነተኛ ፖሊቲካ ይላሉ ቅዱስ አባታችን፥ የሕዝብና የአገር ጥቅም በመዝረፍ የዚጎችን ተስፋና ክብር የሚያጨልሙትን የወንጀል ቡኖችን መዋጋት ተቀዳሚ አላማው የሚያደርግ ነው፡ በመሆኑም በሁሉም መንገድ ያንን የጋራውን ጥቅም የሚያንቋሽሽና የሚረግጥ ሙስና እና ምግባረ ብልሽት መቃወም ግዴታ ነው።

ብዙውን ጊዜ ሙስናና ምግባረ ብልሽት እንደ ልሙድ ቅቡልና ከሰው ልጅ ጋር አብሮ የተፈጠረ ባህርይ ተድርጎ ሲነገር እንሰማለን ይባስ ብሎም የብልጣ ብልጥ መፍትሄ ተደርጎ ይነገራል። የግል ጥቅም ለማካበትና ብሎም የግል ግቦችን ለማሳስካት የሚያስችል አቋራጭ መንገድ እንደሆነ ተድርጎ ሲፈጸም ይታያል። ሙስና ልክ እንደ ተላላፊ በሽታና ጥገኛ የሚያደርግ መርዛማ ሥር እየሰደደ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያውክ አገርንና ሕዝብ የሚያራቁት  ሕጋዊ መዋዕለ ንዋይ የሚያሸሽ ስርቆትና ዝርፍያ እንደ ባህል የሚያሰርጽ ጸያፍ ሊኮነን የሚገባው ተግባር ነው እንዳሉ ጂሶቲ አስታወቁ።

ማፍያነት (ወንጀለኛነት) በአካባቢያችን  አማራጭ ሥርዓት ሆኖ ይታያል። ሙስናንና ምግባረ ብልሽት መዋጋት አማራጭ ሳይሆን ቁርጥ ፈቃድ የሚጠይቅ ተቀዳሚ ዓላማ መሆን አለበት መቃወም ብቻ ሳይሆን ይኸንን ጸያፍ ተግባር በግልም ሆኖ በማህበርም በመንግሥት ደረጃና በፖለቲካው ዓለም ጭምር በመዋጋትና እኩልነትና ፍትህ የሰፈነበት ኅብረተሰብ መገንባት ያስፈልጋል። ማኅበራዊ ፍትሕ ጤናማ ኅብረተሰብ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት መሠረት ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አክለው፥ ዛሬ ስለ የወንጀል ቡድኖችና ስለ ማፊያ ስንናገር ያንን አቢይ ችግር እያመጣ ያለው የወንጀል ቡድኖች በሕገ ወጥ መንገድ በጦር መሣሪያ ንግድ አደንዛዥ እጸዋትን በማዘዋወር በመሳሰሉት ጸረ ሰብአዊ ተግባር አማካኝነት የሚይከማቹት የገንዘብ ሃብት ሕጋዊነት ለማልበስ የሚገለገሉበት እየጠቀመ ያለው የገንዘብ ሃብት አሥራ ላይ ማዋል ብቻ የሚለው ከዴሞክራስያዊ ስርዓትና ደንብ በላይ ሆኖ  እየተስፋፋ ያለው የኤክኖሚ ስልት ዋና ርእሰ በማድረግ መወያየት እጅግ አስፈላጊ ነው፡ ስለዚህ ከማፊያነት ተግባር እውነተኛ ነጻነት መቀዳጀት ያስፍለጋል እንዳሉ የገለጡተ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፥ ሕግንና ስርዓት የማክበር ባህል ማስፋፋት ዜጎችን ለሕጋዊነት ማነጽ አገር በሁሉም ዜጋ የምትገነባ የሁሉም ኃላፊነት የመወጣት ተግባር የምትሻ ናት። ሁሉም ጥሮ እና ግሮ መኖር የሚችልባት ሁሉም እንደ ችሎታውና ብቃቱ የሚሳተፍባት ሁሉም ዜጋ አሳታፊ አገር መገንባት ወሳኝ ነው፡ ይኽ ደግሞ አንዱ የዚህ የጸረ ማፊያ ድርገት ኃላፊነት ነው።

የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ለማስከበር የሚደረገው ጥረት መቼም ቢሆን ችላ ሊባል አይገባውም በማለት ያስደመጡት ንግግር ማጠቃለላቸው ሮበርታ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.