2017-09-20 17:02:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ክርስቲያናዊ ተስፋ፥ በተስፋ መታነጽ

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ

እንደምን አደራችሁ

የዛሬው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሯችን መርህ ርእስ በተስፋ መታነጽ የሚል ነው። ስለዚህ በማቀርበው አስተምህሮ በቀጥታ ተውላጠ ስም በመጠቀም አንተ እያልኩኝ አቀርባለሁ።

እግዚአብሔር በዚያ አንተን በጠራበት ጥሪ፥ ተስፋ ይኑርህ

ለጨለማው ዳፍንት እጅህን አትስጥ፡ የመጀመሪያው ልትቆጣጠረው የሚገባህ ጠላት ባንተ ውስጥ እንጂ ካንተ ውጭ አይደለም። ስለዚህ ለአሉታዊ አስተሳሰቦች ሁሉ ቦታ አትስጥ። በጽናት የመጀመሪያው እግዚአብሔር የሠራው ተአምር ያ በእጅቻን ላይ ያኖረው አስደናቂው አዲሱ ጸጋ ፍጥረተ ዓለም ነው። እምነት እና ተስፋም አብረው ይጓዛሉ። እጅግ የላቁና እጅግ አስደሳች ከሆኑት እውነቶች በመነሳት እመን። በዚያ እያንዳንዱን ከምድራዊ ሕይወት ፍጻሜ በኋላ የሚጠብቀውን በክርስቶስ አቅፍ ውስጥ በማኖር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ መልካምነት አቅጣጫ በሚመራው በፈጣሪው እግዚአብሔር ላይ ታመን። አልፎ አልፎ የእምነት ምስጢረ ውበቱን የምታይ አንተ ብቻ እንደሆንክ ቢሰማህም’ኳ በዙሪያህ የሥላቄ ቃላት ቢከቡህ ለእነዚያ ገዛ እራሳቸው ለሌሎች ክፍት ለሚያደርጉ፡ አገናኝ ድልድይ ለሚገነቡ ላመኑና መልካም ከማድረግ ለማይቆጠቡ ምስጋና ይሁን ዓለም ወደፊት ይላል አትጨነቅ።

በዚህ በምድረ ዓለም የምትመራው ወይንም የምታደርገው ትግል ጥቅም አልቦ ነው ብለህ አታስብ። በሕይወት ፍጻሜ የሚጠብቀኝ ጥፋት ነው ብለህ እትመን፡ በእኛ ውስጥ የፍጹም ዘር (በኑባሬ) አለ፡ እግዚአብሔር በውስጣችን (በልባችን) ተስፋን ካስቀመጠ በቀጣይነት ተስፋ ቆርጦ አያታልልም፡ እግዚአብሔር በልባችን ተስፋን ካስቀመጠ በቀጣይነት ተስፋውን በመሻር እድትደክም አያደርግም። ሁሉም በዘለዓለማዊ ፀደይ ውስጥ እንዲያብብ ነው የተወለደው።

በማንኛው ሥፍራ ገንቢ ሰው፡ ቆመህ ያለኸው ተቀምጠኽ ያለኸው ተነሥና ተጓዝ! መሰላቸትና መጨነቅ መስለል ቢያመጣብህም ይኽንን መንፈስ በመልካም ሥራ (ተግባር) ገስጽ! ባዶነት ቢሰማህም ቅስምህም ቢሰበር ያንን ባዶነት መንፈስ ቅዱስ ይሞላው ዘንድ ጠይቅ (መንፈስ ቅዱስን ጸልይ)።

በሰዎች መካከል ሰላም ሠሪ ሁን፡ የጥላቻ እና የመከፋፈል ቃል የሚነዙትን ድምጻቸውን አትስማ። ምንም’ኳ የሰው ዘር እርስ በእርሱ የተለያየ አንዱ ካንዱ ልዩ ሆኖ ቢፈጠርም ቅሉ ለአብሮ መኖር የተጠራ ነው። ንጽጽር ባለበት ሁሉ ትእግስት ይኑርህ። አንድ ቀን እያንዳንዱ ሰው የእውነት ፍላጭ ወይንም ቁራሽ የተኖረበት (የተቀመጠበት) መሆኑ ትረዳለህና።

ሰዎችን አፍቅር፡ አንድ በአንድ አፍቅር። እያንዳንዱ ሰው ቀጥተኛም ይሁን የተወሳሰበ ችግር ያለበትም ይሁን እያንዳንዱ የሚያወሳው የራሱ ታሪክ አለው፡ እያንዳንዱ የሚወለደው ሕፃን ሕይወት ከሞት እንደሚበልጥ ቃል ለተገባው ሕይወት ማረጋገጫ ነው። ማንኛውም የሚፈልቀው ፍቅር ደስታን የሚያቃትት የመለወጥ ኃይል ነው።

ኢየሱስ በጨለማ ውስጥ የሚፈነጥቅ ብርሃን ሰጥቶናል። ይኸንን ብርኃን ጠብቅ ተከላከል፡ ይኽ ብቸኛው እና ልዩ የሆነው እምነት ተጥሎ የተሰጠህ ብርሃን አቢይ ሃብት (ጸጋ) ነው።

እስካሁን ድረስ ያልታየው የበለጠውን ዓለም ተመኝ (ዓልም) በእርግጥ ምምጣቱ እይቀሬ ነው፡ ተስፋ ሙሉ በሙሉ የፍጥረት ሁሉ ህላዌነት ድምዳሜ የሆነው እግዚአብሔር ሁሉና በሁሉም እስከ ሚለው ድረስ ቀጣይ (የሚዘረጋ) ነው። የምናባዊነቱ ብቃት ያላቸው ሰዎች ለሰው ዘር የሥነ ምርምር እና የዕደ ጥበብ ግኝቶችን ለግሰዋል። ማንም ያላደረገው ውቅያኖሶችን (ኣውክያኖስን) እና መሬትን አቋርጠው በባርነት ሥርዓት ላይ ድል የነሱ ተስፋ በመዝራት የበለጠ የኑሮ ሁኔታ ያመቻቹ በዚህች ምድር መሻሻልን ያመጡ ናቸው።

ለዚህ ዓለም እና ለእያንዳንዱ ሰው ህይወት ተጠያቂነት ይኑርህ። ማንኛውም ያንን ሰብአዊ ክብር የሚያጎድፍ ጸረ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል የሆነው ኢፍትሐዊነት ክፍት ቍስል ነው። ሕይወት ባንተ ህልውነት አይደመደምም ወይንም አይቆምም፡ ምክንያቱም በዚህች ዓለም ሌሎች ትውልዶች ይተካሉ ሌሎች ብዙ ነገሮችም ይከሰታሉና።

እግዚአብሔርን የብርታትን ጸጋ እንዲሰጥህ ለምነው። ኢየሱስ ስለ እኛ ብሎ ያንን እምነታችንን ለመቃወም ምንም ነገር ለማድረግ የማይቻለውን ጠላታችን በሆነው አታላዩ ፍርሃት ላይ ድል ነስተዋልና። በአንዳንድ የሕይወት ችግሮች ፊት ስትገኝ አንተ ስለ እራስህ ብቻ እንደማትኖር አስታውስ። ምክንያቱም በሚሥጢረ ጥምቀት ሕይወትህ በዚያ የቅድስት ሥላሴ ሚሥጢር ውስጥ ገብታለች። የዚያ የቅድስት ሥላሴ ሕይወት ተካፋይ ሆናለች፡ የኢየሱስ ወገን ነህ። አንድ ቀን በሥጋት ላይ ብትወድቅም ወይንም የክፋቱ መንፈስ ለመጋፈጡ እጅግ ከባድና የማይቻል ነው ብለህ ስታስብ ኢየሱስ በአንተ ውስጥ እንደሚኖር ብቻ አስብ። እርሱ በአንተ ውስጥ በርኅራኄው የሰው ልጅ ጠላት እርሱም ኃጢኣት ጥላቻን ጥፋትን ዓመጽን ሁሉ በእግሩ ሥር እድርጎታል።  

ዘወትር የእውነት ብርታት ይኑርህ፡ ነገር ግን ከማንም በላይ የበለጥክ እና ለማንም የበላይ እንዳልሆንክ አስታውስ። በዚህች ምድር በእውነት ላይ ጸንተህ የምታምን አንተ ብቻ ሆነህ ቢሰማህና ብቸኛው አማኝ ሆነህ ብትቀርም መቼም ቢሆን ከሌሎች ሰዎች እራስህን እታርግል። ልክ የባህታዊው ጽሞና’ኳ ብትኖርም የፍጥረት ሁሉ ስቃይ በልብህ አኑር። ክርስትያን ነህና በጸሎት ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ስጥ።

መልካም ዓላማ አዳብር። ሰው ሰገር ለሆነው ለላቀው ዓላማ ኑር። አንድ ቀን እነዚህ መልካም ዓላማዎች ከባድ መስዋዕትነት የሚያስጠይቅህ ሆነው ቢገኙም በልብህ ይዘኻችው መኖርን አታቋርጥ፡ በልብህ ያዛቸው፡ ታማኝነት ሁሉን ነገር ያስገኛል።

ከተሳሳትክ ከወደቅበት መሳሳት ብድግ ብለህ ተነሣ፡ ደካማህ ነህና፡ ስህተት ከመፈጸም በላቀ ደረጃ ሰው የሚያስብለን ሌላ የበለጠ ምንም ነገር የለም፡ ሆኖም ለአንተ እነዚያ ስህተቶች ከርቸሌ መሆን አይገባቸውም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ልጅ ለጤነኞች ሳይሆን ለህሙማን ነው የመጣው። ስለዚህ ላንተም ጭምር ነው የመጣው። ስህተት መፈጸም ሊያስፈራህ አይገባም። ብትሳሳት አትፍራ ብድግ ብለህ መነሣትን እወቅ!። እግዚኣብሔር ወዳጅህ ነው።

ምሬት ቢጫንህ ቅር ብትሰኝም በጽናት አሁንም ስለ መልካም የሚተጉ ሰዎች እንዳሉ ታመን። በእነዚህ ሰዎች ውስጥ የዝያ የበለጠውና የተሻለው ዓለም ዘር አለና። አስደናቂያን ከሆኑ ነገሮች ሁሉ ተማር። መደነቅን አጎልብት።

ኑር አፍቅር እመን፡ በእግዚአብሔር ጸጋ መቼም ቢሆን ተስፋ አትቍረጥ።

በማለት ቅዱስ አባታችን የለገሱት የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው ለአስተምህሮው የተገኙት ሁሉ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ወደ መጡበት ሸኝተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.