2017-09-15 10:16:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ,

ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በኮሎምቢያ ሓዋርያዊ ጉዞ አጠናቅቄያለሁ። በፍጹም ልቤ ጌታን ስለዚህ ታላቅ ስጦታው አመሰግናለሁ፡ ደግሜ የረፓብሊካዊት ኮሎምቢያ ርእሰ ብሔር ላደረጉልኝ አቀባበል ላሳዩት ታልቅ መልካምነት እና አክብሮት፡ ለአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ሌሎችም የአገሪቱ የመንግሥት አካላት በጠቅላላ ሁሉም ያካሄድኩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለተዋጣለት ክዋኔ በተለያየ መልኩ አስተዋጽኦ ላደረጉት ሁሉ እወቅና በመስጠት ደግሜ  ምስጋናዮን ማደስ እፈልጋለሁ፡ በተለይ ደግሞ እጅግ በፍቅርና በታላቅ ደስታ ተቀብሎ ላስተናገደኝ ለኮሎምቢያ ሕዝብ ልዩ ምስጋና አቀርባለሁ።

ይኽ በኮሎምቢያ ባካሄዱኩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከእኔ በፊት እ.ኤ.አ. 1968 ዓ.ም.  ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ እና ቀጥሎም እ.ኤ.አ. በ1986 ዓ.ም. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በአገሪቱ ላካሄዱት ጉብኝት ቀጣይነቱ ያስተዋለና ቀጣይነቱ ደግሞ በዚያ የሕዝበ እግዚአብሔር ጉዞ በታሪክ ውስጥ በሚመራው በመንፍስ ቅዱስ በጽናት የተነቃቃ መሆኑ በጥልቀት በዚህ ባካሄድኩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማስተዋል ችያለሁ።

የዚያ በኮሎምብያ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት መርህ ቃል Demos el primer paso”,  የመጀመሪያው እርምጃ ከእኛ ይጀምር የሚል ያንን በኮሎምቢያ ከዚያ የግማሽ ዘመን የዘራው ስቃይና የጠላትነት መንፈስ ለመፈወሱ እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን ብዙ ጉዳት ካስከተለው ተነክራ ከነበረችበት ውስጣዊ ግጭት ተላቃ እየተከተለቸው ያለው የእርቅ ሂደት የሚመለከት ነው። ነገር ግን በእግዚአብሔር እርዳታ የእርቁ መንገድ እየተከናወነ ይገኛል። ያካሄድኩት ሐዋርያዊ ጉብኝትም የሕዝቡ ጥረት ለመባረክና በእምነት እና በስፋ ለማጽናት ለዚያ ለመላይቱ ቤተ ክርስቲያን የሆነውን አገልግሎቴን ትልቅ ድጋፍ የሆነውን የሕዝቡ ምስክርነትንም ለመቀበል አስችሎኛል።

ኮሎምቢያ  ልክ እንደ አብዛኛው የላቲን አሜሪካ ሀገሮች ሁሉ ጥልቅ ክርስቲያናዊ መሰረት ያላት አገር ነች። ይህ እውነታ ያ ያለባት ቁስል ከባድ የሚያደርገው ቢሆንም በተመሳሳይ መልኵም የሰላምን ዋስትና የሚያጸና፡ ለዳግመ ግንባታው ሂደት ጽኑ መሰረት እና ለዚያ ለማይረታውና ለማይበገረው ተስፋዋም ሕይወት ነው። ነገር ግን ያ የክፋት መንፈስ  የእግዚአብሔርን ሥራ ለማጥፋትና ለማጨናገፍ ሰዎች መከፋፈል ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ቅሉ ያ ማለቂያ የሌለው  የክርስቶስ ፍቅር እና ምሕረት ከኃጢአትና ከሞት ይልቅ ጠንካራ ነው።

ይህ ጉዞ በዚያ ብሔር ልብ ውስጥ ላለው ለተጥለቀለቀው የሕይወትና የሰላም ፍላጎት ሁሉ፡ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን በረከት ለማድረስ የተካሄደ ነበር:፡የሕይወትና የሰላም ፍላጎቱን በዚያ የበጎታ አደባባዮችን ባጥለቀለቀው በብዙ ሺሕ የሚገመተው ሕዝብ ብዙ ሺሕ ሕጻንት እና ወጣቶች፡ በአገሪቱ በተገናኘኹዋቸው ሰዎች ፊት ሁሉ ቀርቤ ያረጋገጥኩት እውነት ነው፡  የአገሪቱ ተፈጥሮም የሚያውጀው እውነት ነው። በበጎታ ከእገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት እና ከመላ የላቲን አመሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት አስፈጻሚው ኮሚቴ ጋር ለመገንኘት ችያለሁ።  ቀርቤ እንዳያቸውን አቅፌ ለመሳም ሰላም ለማለትም በመቻሌና በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው በዚያ ሰላማችንና ተስፋችን ለሆንው ክርስቶስ ቅዱሳት ምስጢራቱ ለሆነቸው ቤተ ክርስቲያን በሚሰጡት አገልግሎት ላበረታታቸውም እድል በማግኘቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡

ቪላቪሰንሲዮ የፈጸሙት ጉብኝት ለዚያ በኮሎምቢያ ላካሄድኩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዋና ምክንያት የሆነው እርቅ ለተሰየመው መርሐ ግብር  የተኖረባት ከተማ ስትሆን። በዚያች ከተማ ጧት ላይ ቅዱስ ቁርባን ተከብሯል ለእምነት ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ኼሱስ ኤሚልዮ ኻራሚሎ ሞንስላቨና ለሰማዕት ካህን ፐድሮ ማሪያ ራሚረስ ብፅዕናም ታውጀዋል። ከሰዓት በኋላም  የንስሐና የዕርቅ ሊጡርጊያ በዚያ በቦካያ ተካሂዶ በነበረው ግጭት አለ እጅና እግር የቀረው የጥቃት ሰለባ የሆነው ልክ እንደ የእገሪቱ ህዝብ በጦርነት የተጎዳው ታሪካዊ የክርስቶስ መስቀል ዘቦካያ በተኖረበት ጉባኤ ተፈጽሟል።

የሁለቱ ሰማዕታት የብፅዕናው አዋጅ በሚገባ እና ምናልባትም ሰላም ሊገመት በማይቻለው ስለ ፍቅር እውነትና ፍትህ በሚሰጠው በደም ምስክርነት ላይ የጸና መሆኑ የሚያረጋገጥም ቅዱስ ፍጻሜ ነው፡ ሁለቱ ሰማዕታት በእምነታቸው ምክንያት ተገድለዋል። የብፁዓኑ የሕይወት ታሪካቸውን ማዳመጥ ዓይኖቻችን በእንባ እንዲሞላ አድርገዋል። እምባውን የስቃይና የደስታ ትእምርት ነው የነበረው። የእግዚአብሔርን ቅዱስ ታማኝ ሕዝብ በብፁዓኑ ቅዱስ ትሩፋት ፊት በዚያ ብዙዎች ለዓመጽ ሰለባ የሆኑትን በስቃይና በደስታም በማሰብ ጥልቅና ብርቱ የሆነውን መለያውን እንዲያስተውልና ያንን መለያውን ለማዳመጥ አስችሎታል። “እግዚአብሔር ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ ከትውልድ እስከ ትውልድ ምሕረቱን ያደርጋል (ሉቃስ ምዕ. 1,50 ተመል)።

ምሕረት እና እውነት ይተቃቀፋሉ፥ ጽድቅ እና ሰላም ይሳሳማሉ" (መዝ. 85:11). ይህ መዝሙር ያንን ባለፈው ዓርብ (እ.ኤ.አ. መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም.) ይኽ ትንቢትም በኮሎምቢያ የተረጋገጠ የንስሐ ሊጡርጊያውን በውስጡ የተመሰከረና፡ ለዚያ ለተጎዳው ሕዝብ ትንቢትና የተሰጠም የእግዚአብሔር ጸጋ ነው፡ ምክንያቱም እንዲነሱና እና በአዲስ ሕይወት ይጓዙም ዘንድ ነው። እነዚያ የእግዚአብሔር ጸጋ የተሞሉ ትንቢታዊ ቃላቶች እነዚያ ጉዳት ከደረሰባቸው ጀምሮ እነዚያ በነበረው ዓመጽና ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን ሁሉ ወክለው በክርስቶስ ጸጋ ተደግፈው በእራስ ውስጥ ከመዘጋት ወጥተው ለምህረትና ለእርቅ ከሌላው ጋር ለመገናኘት ፈቅደው ምስክርነት በሰጡት ሥጋ ለብሶ የተረጋገጠ እውነት ነው።

በመደሊን ውስጥ የነበረው አመለካከትና የክርስትናው ኑሮ እንደ ደቀ መዝሙር የመሆን ፍላጎት፡ የሚገልጥ ጥሪ እና ተልዕኮ ነው፡ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስት ለመከተል በሚፈጽሙት ተግባርና ጉዞ ሙሉ በሙሉ በዓለም ውስጥ ጨው፡ ብርሃንና እና እርሾ ይሆናሉ፡ ይኽ ደግሞ እውነት መሆኑ በእገሪቱ የሚታየው የተትረፈረፈው ፍሬ ይመሰክረዋል። ከፍሬዎችም ውስጥ በሆጋር የሚገኘው ህጻናት እና ወጣቶች በሕይወት ውስጥ ጉዳት የደረሰባቸው ሁሉ ተፈቅረው ተጠበቀው እና ተጓዳኝ አግኝተው የሚኖርበት አንድ አዲስ ቤተሰብ የሚያገኙበት ማእከል ለመግለጥ ይቻላል፡ በኮሎምቢያ የሚታየው ቀርቤ ለመባረክና በደስታ ለማበረታታት እድል እግኝቼ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኘውኹዋቸው የክህነትና የውፉይ ሕይወት ጥሪ የሚኖሩ አገልጋዮች ጥሪ ከተትረፈረፉት ዘለላ ፍሪዎች ውስጥ የሚጠቀስ እንደሆነም ቀርቤ ያየሁት በአገሪቱ የሚታየው የተቀደሰና የፉይ ሕይወት መበራከት ለመጥቀስ ይቻላል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን የጎበኝዋትን ያችን የካርታገና ከተማ በማስታወስ ከተማይቱ፥ የቅዱስ ፒየትሮ ክላቭ በባርነት ሥርዓት ይሰቃዩ ለነበሩት ሁሉ ነጻነትን ለማወጅ ሐዋርያዊ ትኩረቱ የሰውን ሰብአዊ እና መሰረታዊ መብቶቹን በማስተዋወቅና በማነቃቃት አገልግሎት በመስጠት የተራመደበት ከተማ ነች በማለት ገልጠው፡ ቅዱስ ፒየትሮ ክላቨ እና ቅድስት ማሪያ በርናርዳ ቢዩልተር ለድሆች ለተገለሉ ሁሉ ሕይወታቸው ሰጥትዋል፡ እንዲህ ባለ ጉዞም ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም መሰረት ያደረገ ሳይሆን ትላንትናም ዛሬም ሰዎችን ከነበርውና ካለው የባርነት ቀንበር ነጻ የሚያወጣውን እውነተኛው ሕይወት የሆነው ወንጌላዊ አብዮት የመሰከሩባት ከተማ ነች፡  አገልግሎታቸውም የቆሰለውን እና የተጣለውን የወንድማችንን ሥጋ ጎንበስ ብሎ ጉልበትን አጥፎ ከዚያ ስለ እኛ ሲል እራሱን ካዋረደው ከክርስቶስ ጋር ሆኖ ለመንካት የመጀመሪያው እርምጃ ከእኛ መሆን እንዳለበት ያስገነዝበናል። ለክርስቶስ ምስጋና ይድረሰው እርሱ ምሕረትና ሰላም በመሆኑ በእርሱ አማካኝነት ተስፋ ህያው ነው።

ደግሜ አሁንም ኮሎምቢያ እና ተወዳጁ ሕዝባንም ጭምር ለዚያች ቀርቤ በጎታ በሚገኘው ካቴድራል ደርሼ አማላጅነቷን ለመጸለይ እድል ላጋጠመኝ ለእመቤታችን ቅድስተ ማርያም ዘቺንከይኩይራ ጥበቃ አወክፋለሁ።. በማርያም እርዳታ እያንዳንዱ ኮሎምቢያዊ በፍቅር በፍትሕ እና በሰላም ጎዳና በየቀኑ ወደ ወንድም እና ወደ  እህት የመጀመሪያው እርምጃ እንዲያደርግ ማርያም ትደግፈው በማለት የለገሱት የዕለቱ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፡ በጉባኤው ለተገኙት ሁሉ ሰላምታቸውን አቅርበው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.