2017-08-24 09:40:00

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ፔትሮ ፓሮሊን በራሻ የሚያደርጉትን የአራት ቀን ጉብኝት ጀመሩ።


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከነሐሴ 15-18/2009 ዓ.ም ለአራት ቀናት ያህል የሚቆይ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ራሻ እንደ ሚሄዱ መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ለዚሁ ጉዞ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት እንደ ተቻለው ይህንን የአራት ቀን ጉብኝት በትላንትናው እለት መጀመራቸው ታውቁዋል።

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ባለፈው ሰኞ እለት ከሞስኮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ሀላፊ ከሆኑትና የሞስኮ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክን በመወከል ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር የሚደረገውን ግንኙነት በበላይነት እንዲመሩ ሃልፊነት ከተሰጣቸው ሊቀ ጳጳስ ሂላሪኦን ጋር ለሁለት ሰዓታት ያህል አድርገውት የነበረው ውይይት በጣም ገንቢ እንደ ነበረም ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን መግለጻቸውም ታውቁዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በቀጣይነት ከራሻ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሴርጌ ላቭሮቪ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን በግንኙነታቸው ወቅት ዓለማቀፋዊ ስለሆኑ ጉዳዮች እና በቫቲካን እና በራሻ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ከቪዛ-ነዛ የሆነ ዝውውር ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተም መወያየታቸውም ተገልጹዋል።

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊንና የራሻው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በግል ካደረጉት ውይይት ቡኃላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደ ገለጹት የቫቲካን እና የራሻ ፌዴሬሽን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ ሰዎች ያለምን የቪዛ መስፈርት በሁለቱ ሀገራት ውስጥ መዘዋወር የሚያስቻላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን ገልጸዋል።

ከፊርማው ስነ-ስራዓት ቡኃላ ካርዲና ጴትሮ ፓሮሊን እንደ ገለጹት ይህ አሁን የተፈረመው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲጠናከር ካለው ፍላጎት የመነጨ መሆኑን ገልጸው ይህም ሁለቱ ሀገራት በተናጥል እና በጋራ ዓለማቀፋዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሰሩ መንገድ ይከፍታል ብለዋል።

በራሻ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን ሕይወት እና ተግባር በተመለከተ ከራሻ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሴርጌ ላቭሮቭ ጋር መወያየታቸውን የገለጹት ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን በተለይም ደግሞ የራሻ ዜግነት የሌላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በራሻ ለመቆየት ወይም ለመሥራት የሚያስችላቸው የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት እንደ ሚቸገሩና በተጨማሪም ለካቶሊክ እምነት ተከታይ ምዕመናን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን ለመገንባት የሚያስችል ፈቃድ ማግኘት በአሁኑ ወቅት በቫቲካን እና በራሻ ፌዴሬሽን መካከል የሚታዩ ችግሮች መሆናቸውንም የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጨምረው ገልጸዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሴርጌ ላቭሮቭ በበኩላቸው እንደ ገለጹት በመካከለኛው ምስራቅ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በተለየ መልኩ መፍትሔ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀው በተመሳሳይ መልኩም በሊቢያ እና በኢራቅ በሚገኙ የተለያዩ የጎሳ እና የሃይማኖት ቡድኖች መካከል ሚዛናዊ የሆነ ተመሳሳይ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ የበኩላችንን ጥረት ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ በሩሲያ እና በቅድስት መንበር መካከል ልዩነት እንዳለ እንደ ሚገነዘቡ የጠቀሱ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ሆኖም ግን በሁለቱም ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ እና በአንድ አንድ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ሁለቱም ሀገራት የሚጋሩት ጉዳይ መሆኑንም ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በቬንዙዌላ የሚታየውን ፖሌቲካዊ ቀውስ በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን በአሁን ወቅት ይህንን ጭግር ለመፍታት ቫቲካን እያደርገች የምትገኘውን ጥረት የራሻ ፌዴሬሽን እንደ ሚያግዝ እምነታቸው መሆኑን ገልጸው በተለያዩ የፖሌቲካ አንጃዎች መካከል ያለው ልዩነት በውይይት እንዲፈታ ለማድረግ የሚደረገውን ውይይት የራሻ እገዛ እንዲታከልበትም የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት  ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጨምረ ገልጸዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ሐላፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በዛሬው እለት ከራሻ ፌዴረሽን ፕሬዚዳንት ከሆኑ ቨላዲሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም የደረሰን ማስረጃ ያስረዳል








All the contents on this site are copyrighted ©.