2017-08-14 14:20:00

"እምነት የሕይወት ጉዞዋችንን የሚደግፍ ነገር ነው እንጂ የማምለጫ መንገድ ወይም የመሸሸጊያ ዋሻ አይደለም"


ዘወትር እሁድ እለት ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አማካይነት በእለቱ በሚነበበው የቅዱስ ወንጌል ቃል ላይ ተመርኩዘው የሚሰጡትን  አስተንትኖ ለመከታተል እንደ ሚሰበሰቡ ይታወቃል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የዚህ መርዕ ግብር አንዱ አካል በሆነው በትላንትናው እለት ማለትም በነሐሴ 7/2009 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ያደረግት አስተንትኖ መሰረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከማቴዎስ ወንጌል 14:22-33 በተወሰደው እና ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ መሄዱን በሚገልጽው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ያተኮረ እንደ ነበረም ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “እምነት የሕይወት ጉዞዋችንን የሚደግፍ ነገር ነው እንጂ የማምለጫ መንገድ ወይም የመሸሸጊያ ዋሻ አይደለም” ማለታቸው ታውቁዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጵሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ (ከማቴዎስ ወንጌል 14:22-33) በተነበበው ቃል ላይ ኢየሱስ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልይ ካመሸ ቡኃላ  በገሊላ ባሕር ላይ እየተራመደ ደቀ መዛሙርቱ  ወደ አሉበት በጀልባ መሄዱን ይገልጻል። በዚያ ጊዜ ጀልባዋ ባሕሩን ዘልቃ እየተጓዘች ሳለች ነፋስ ተነሥቶ በማዕበል ትንገላታ ጀመር። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ በባሕሩ  ላይ እየተራመደ ሲመጣ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ እነርሱም፣ምትሀት ነው!” በማለት በፍርሃት ጮኹ! ኢየሱስም ወዲያውኑ፣ “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ አትፍሩ” አላቸው። ጴጥሮስም፣ ከጀልባው ወርዶ በውሃው እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ። ነገር ግን የነፋሱን ኃይል ባየ ጊዜ ፈራ፤ መስጠምም ሲጀምር፣ጌታ ሆይ፤ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። ኢየሱስም ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና ከመስመጥ አዳነው።

ይህ የወንጌል ክፍል ትርጉም ያለው ተምሳሌት የተካተተበትና በግለሰብ ደረጃ ይሁን እንደ ቤተክርስቲያን ማኅበረሰበ ስለእምነታችን እንድናሰላስል የሚያደርገን ነው። ይህ የኅብረተሰብ ክፍል ወይም ይህ የቤተክርስቲያን ማኅበረሰብ እምነት አለው ወይ? በእያንዳንዳችን እና በማህበረሰባችን ውስጥ ያለው እምነት እንዴት ነው? በዛሬው ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው ጀልባ የእያንዳንዳችንን እና የቤተክርስቲያን ሕይወት ያመለክታል፣ ብርቱ የነበረው አውሎ ንፋስ ደግሞ ተግዳሮቶቻችንን እና ፈተናዎቻችን ያመለክታል። ጴጥሮስም ኢየሱስን ጌታ ሆይ፤ በውሃው ላይ እየተራመድሁ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝያለው እና ከዚያም በመቀጠልጌታ ሆይ አድነኝ!” በማለት የተናገራቸው ቃላት እኛ ጌታ ቅርባችን ይሆን ዘንድ ከምንመኘው ምኞት ጋር ይመሳሰላል፣ እንዲሁም በራሳችን እና በማኅበረሰባችን ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙንን ውስጣዊ እና ውጫዊ ፍርሃት እና ጭንቀቶች ያስታውሰናል።

ኢየሱስ ለጴጥሮስ የተናግራቸው እርግጠኛ የሆኑ ንግግሮች ብቻ በቂ አልነበሩም፣ ነገር ግን ለእርሱ በወቅቱ አስፈላጊ የነበረ ጉዳይ ቢኖር ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ይዞ ያዳነው ክስት ነው። ይህም በእኛ ሕይወት ውስጥ ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። መተማመኛ ለማግኘት እና እርግጠኛ ለመሆን ያስችለን ዘንድ የእግዚኣብሔርን ቃል የሙጥኝ ብለን የማንይዝ ከሆነ እኛም መስመጥ እንጀምራለን ማለት ነው። የዛሬው ወንጌል በጌታ እና በቃሉ ማመን ሁሉም ነገር ቀላልና መረጋጋት ወይም ጸጥታ ባለበት መንገድ መራመድ ማለት እንዳልሆን ያስታውሰናል፣ እንዲሁም የሕይወትን ማዕበል ሁሉ ለማስወገድ የሚችሉ ነገሮች እንዳልሆኑም ያስታውሰናል።

እመነት ኢየሱስ ከእኛ ጋር እንደ ሆነ እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል፣ ሕልውናችንን እንዳናጣ ያደርገናል፣ በችግርች ውስጥ በምንሆንባቸው ጊዜያት ሁሉ በመከራዎቻችን ብዛት የተነሳ እንዳንሰምጥ እጁን ዘርግቶ እንደ ሚረዳን ማረጋገጫ በመስጠት ጨለማ በሚባልበት ስፍራውስ ውስጥ እንኳን ቢሆን መንገድ ያሳየናል።  ባጠቃላይ እምነት በሕይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙን ችግሮቻችንን የምንሸሸግበት ቦታ ሳይሆን ነገር ግን ይህንን መከራ እና ችግሮቻችንን እንድንወጣ በማድረግ ትርጉም ያለው ሕይወት እንድንኖር ያደርገናል።

አንድ ጀልባ ረጅም የሆነ ባሕርን በምያቋርጥበት ወቅት ጉዞ ላይ እያለ ጠንካራ የሆነ አውሎ ነፋስ ይገጥመዋል ይህም ክስተት ለአደጋ ያጋልጠዋል።  ይህ ክስተት በሁሉም ዘመናት ውስጥ የቤተክርስቲያን እውነታ የሚያሳይ ድንቅ የሆነ ምስል ነው። ቤተክርስቲያንን እስከ ዛሬ ቀን ድረስ ያዳናት በውስጡዋ የሚገኙ ሰዎች ብርታት ወይም ጥራት አይደለም፣ ቤተክርስቲያን አስቸጋሪ የሆነ ማዕበልን መወጣት የቻለችሁ ግን በክርስቶስ እና በቃሉ በተሰጣት ማረጋገጫ ነው፣ ይህም ማረጋገጫ በኢየሱስ እና በቃሉ ማመን ነው።

በዚህ ዓይነቱ ጀልባ ላይ በምንሳፈርበት ወቅት እርግጠኞች እንሆናለን፣ በተለይም ደግሞ በመከራዎቻችን እና በድክመቶቻችን ወቅቶች ሁሉ ልክ ደቀ መዛሙርቱ በስተመጨረሻበእርግጥ አነተ የእግዚኣብሔር ልጅ ነህ”! ብለው ለኢየሱስ እንደ ሰገዱለት ሁሉ እኛም ደግሞ ለኢየሱስ መንበርከክ እና መስገድ ይገባናል። ኢየሱስን በእርግጥ አነተ የእግዚኣብሔር ልጅ ነህ”! ማለት እንዴት ደስ የሚያሰኝ ቃል ነው? እስቲ ሁላችንም በጋራበእርግጥ አነተ የእግዚኣብሔር ልጅ ነህ”! እንበለው።

እመቤታችን ቅስት ደንግል ማሪያም በሕይወት ውስጥ የሚገጥሙንን ውጣው ውረዶችን በመቋቋ፣ በእመንት ጸንተን እንድንኖርና ምቀኝነትን ሆነ ስሜታዊነትን፣ የእራሳችንን ፍልስፍናዎች፣ ልምዶች እና መፈክሮች አስወግደን ቤተክርስቲያን ጀልባ ላይ ሆነን መጓዝ እንችል ዘንድ በአማልጅነቷ ትርዳን።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.