2017-08-07 13:05:00

በዚህ የአካል እና የመንፈስ እረፍት በምናደርግበት የበጋ ወቅት ይህንን እድል ያላገኙ ሰዎችን ማሰብ ይገባል።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 30/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ኢየሱስ፣ ጴጥሮስንና ያዕቆብን እንዲሁም ዮሐንስን ወደ ታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዞአቸው በወጣበት ወቅት የኢየሱስ መልክ በቅጽበት የተቀየረበት እለት በተከብረበት እለት ባደረጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት በዚህ የአካል እና የመንፈስ እረፍት በምናደርግበት የበጋ ወቅት (በአሁኑ ወቅት በመላው አውሮፓ በጋና ጸሐያማ በመሆኑ የተነሳ ሰዎች ከቤተሰቦቻችው ጋር የሚገኛኑበት የእረፍት ወቅት ነው) ይህንን እድል ያላገኙ በብቸኝነት የሚኖሩ፣ ጠያቂ የሌላቸው፣ የታመሙ፣ ድኸ የሆኑ በጦርነት እና በብጥብጥ ብሎም በፍትህ መጓደል ምክንያት እየተሰቃዩ የሚገኙ በዓለም ዙሪያ የኒገኙትን ወንድም እና እህቶቻችንን ማሰብ ይገባናል ብለዋል።

“የእየሱስ መልክ የተቀየረበት አጋጣሚ ለእኛ የተስፋ መልእክት ያስተላልፍልናል፣ ወንድሞቻችንን ማገልግል እንችል ዘንድ በቅድሚያ እየሱስን እንድንገኛ ጥሪ ያቀርብልናል” በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በዛሬው እለት ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው በታቦር ተራራ የተፈጠረው በዓይነቱ ልዩ የሆነ ክስተት እውነተኛነቱ በሐዋሪያው ጴጥሮስ፣ በያዕቆብ እና በዩሐንስ የተመሰከረ ትይን እንደ ሆነም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ይህ በሦስቱ ደቀ መዝሙር የተመሰከረው ክስተት “ወደ ሰማያው ቤታችን የምናደርገው ጉዞ የተሳካወይም ደግሞ ውጤታማ ይሆን ዘንድ  ከዓለማዊ ነገሮች መላቀቅ እንደ ሚያስፈልግ እንድናስብ ያደርገናል” ያሉት ቅዱስነታቸው የእግዛኢብሄርን ቃል በተሟላ መልኩ ለመቀበል ያስችልነ ዘንድ ጥልቅ የሆነ ጸሎት የምናደርገብት ውቅቶችን እንድንፈልግ ያደርገናል ብለዋል።

“በወንጌል ቃላት ላይ አስተንትኖ የምናደርግበት፣ መጽሐፍ ቅዱስነት የምናነብበት፣ መልካም የሆኑ ነገሮችን የምንመኝበት፣ የምንደምቅበት እና ደስታ የምናገኝበትን ሰላም የሰፈነበት ሁኔታ ፈልገን እንድናገኝ ጥሪ ያደርግልናል” በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ አካላዊ እና የመንፈስ እረፍት የምናደርገበት የበጋው የእረፍት ወቅት “እየሱስን ለማግኘት ጥብቅ ፍለጋ የምናደርግበት ወቅት” ሊሆን ይገባል ብለዋል።

“በዚህ አካልዊ እና የመንፈስ እረፍት በምናደርገበት በአሁኑ የበጋ ወቅት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የሚያርፉበት፣ ብዙ ቤተሰቦች እረፍት በሚያደርጉበት በአሁኑ ወቅት እለታዊ ከሆኑ ጭንቅቶቻችን መላቀቅ ይኖርብናል” ያሉት ቅዱስነታቸው በእለታዊ ጭንቀቶች ምክንያት የደከመውን አካላችንንና እና መንፈሳችንን ለማደስ መንፈሳዊ ሕይወታችንን በጥልቅ መመርመር ይኖርብናል ብለዋል።

ይህንን የእረፍት ጊዜያችን የተረጋጋ ይሆን ዘንድ፣ ይህንን የእረፍት ጊዜ በእድሜ ምክንያት በተፈለገው መልኩ መጠቀም ያልቻሉትን አረጋዊያን፣ በጤና እክል ወይም ደግሞ በሥራ ምክንያት፣ በገንዘብ እጥረትና በመሳሰሉት ምክንያቶች በተገቢው ሁኔታ የእረፍት ጊዜ ማድረግ ባለመቻለቸው የተነሳ ያዘኑና የብቸኝነት ስሜት የሚሰማቸውን ሰዎች ታጽናና ዘንድ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በአደራ ልንሰጥ ይገባል ካሉ ቡኃላ “የእግዛኢኣብሔር መልአክ ማሪያምን አበሰራት እርሷም በመንፈስ ቅዱስ ጸነሰች” የሚለውን ጸሎት ከምእመናን ጋር በመቀባበል ደግመውና ቡራከን ሰጥተው የእለቱን አስተንትኖዋቸውን አጠናቀዋል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.