2017-08-02 15:47:00

ቨነዝወላ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ልታዘግም እንደምትችል የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ


በቨነዝወላ እ.ኤ.አ. ከባለፈው ሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀጣጠለው ጸረ መንግሥት አቋም ያለው ሕዝባዊ አመጽ አሁንም እልባት አለ ማግኘቱና እንስከ አሁን ድረስ 121 ሰዎች መዳረጋቸው ብሎም እሁድ በመንግሥት ፍላጎት መሠረት ሕዝባዊ ምርጫ በተካሄደበት ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. 14 ሰዎች ለሞት ሕይወታቸው ማጣታቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ርእሰ ብሔር ማዱሮ ውሳኔ መሠረት ብዙ የተቃዋሚ የፖለቲካ ሰልፍ መሪዎች ክእነርሱም ውስጥ ለፖልዶ ሎፐዝና አንቶኒዮ ለደዝማ የሚገኙባቸው ብዙ የተቃዋሚ የፖለቲካ ሰልፍ አባላት ለእስር ዳርገዋል። ለእስር የተዳረጉት የአንቶኒዮ ለደዝማ ልጅ ቫነሳ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ አባታቸው ለደዝማ ሌሊት ከተኙበት በጸጥታ ኃይል አባላት መወሰዳቸውና ለእስር የዳረጋቸው ምክንያትም ሆነ የት እንደተወሰዱም እንዳልታወቅ ገልጠው፡ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በቨነዝወላ ተከስቶ ያለው ህዝባዊ ዓመጽ ተገቢ መፍትሔ እንዲያገኝና የአገሪቱ መንግሥት እየተከተለው ያለው የአምባ ገነናዊ ሥርዓት በሁሉም ዘርፉ እንዲቃወም ጥሪ በማቅረብ ያለው ሁኔታ በእንዲህ ከቀጠለ ቨነዝወላ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ልታዘግም እንደምትችል ነው ብለዋል።

ማንኛውም የፖለቲካ አካል የመንግሥት ተቋማት አበይት የፖለቲካ አካላት የማዱሮ መንግሥት ሲቃወም ቢገኝ አለ ምንም ምሕረት በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ለእስር እንዲዳረግ ርእሰ ብሔሩ ለጸጥታ ኃይል አባላት ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን፡ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ በሥልጣን ላይ ያለው የማዱሮ መንግሥትና ተቃውሚ ሕዝብ መካከል ያለው ውጥረት በእንዲህ ከቀጠለ አገሪቱ ለከፋ ችግርና የውስጥ ጦርነት እንደምትጋለጥ ከተለያዩ የላቲን አመሪካ ፖልቲካ ተንተኛኞች እየተሰጠ ያለው አስተያየት እውነት መሆኑ ቨነሳ ለደዝማ ይጠቁማሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በቨነዝወላ ላይ የኤኮኖሚ ማዕቅድ የደነገገ ሲሆን የማዱሮ መንግሥት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እየተገለለ መሆኑ ሲገለጥ። የዚህ ዓይነቱ ሂደት ላለው ውጥረት መፍትሔ ለማፈላለግ ለሚደረገው ጥረት ሊያጨናግፍ እንደሚችል የላቲን አመሪካ ሊቅ የኢጣሊያው ሶለ 24 ኦረ ለተሰየመው ዕለታዊ ጋዜጣ ልኡክ ጋዜጠኛ ሮበርቶ ዳ ሪን መናገራቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አሊና ቱፋኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.