2017-07-31 16:02:00

ዜና ዕረፍት


ክቡር አባ ሃብተጊዮርጊስ ዮሓንስ ባደረባቸው ሕምም ምክንያታ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በገዳመ ምኔት ደብረ ፍልሰታ ዘሲታውያን ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው ከማኅበረ ሲታውያን የተላለፈልን ዜና ይጠቁማል።

ኣባ ሃብተጊዮርጊስ በኤርትራ ሰራዮ ክፍለ ሃገር አዲዜኑ እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 1933 ዓ.ም ተወልደው፡ አስመራ በሚገኘው በሲታውያን ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ተማሪ ሆነው ኣዛው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና ለከፍተኛ ትምህርት በኢጣሊያ ሮማ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ገዳመ ምኔት ዘሲታውያን ተልከው ጥቅምት 1 ቀን 1954 ዓ.ም. የመጀመሪያ መሐላ ፈጽመው ከአምስት ዓመት በኋላ መስከረም 15 ቀን 1959 ዓ.ም. ዓቢይ መሐላ መፈጸማቸው የገለጠው የሲታውያን ዜና ምንጭ አክሎ የፍልስፍናና ቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሌሎች ሦስት የማኅበሩ አባላት ጋር ከብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ገብረ ኢየሱስ ማዕርገ ክህነት ተቀብልው እ.ኤ.አ. ጥር 13 ቀን 1963 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ተመልሰው የሲታውያን ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ምክትል አለቃ በመሆን እስከ 1966 ዓ.ም. ካገለገሉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተልከው መንዲዳ በሚገኘው የሲታውያን ገዳም ለአንድ ዓመት የገዳሙ አለቃ ሆነው አገልግለዋል። እ.ኤ.አ. በ 1967 ዓ.ም. ወደ ሮም ተመልሰው የምንኩስና ሕይወት በኢትይጵያ በሚል ርእስ ሥር በደረሱት መጽሓፍ ከጳጳሳዊ ተርሲያኑም የስነ መንፈሳዊ ተቋም ሊቅነት አስመስክረው ከዛም ለአንድ አመት በአየርላንድ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያም ወደ ኤርትራ እየተላኩ በተለያዩ ገዳመ ሲታውያን ያገለገሉ መሆናቸው ዜናው ይጠቁማል።   
All the contents on this site are copyrighted ©.