2017-07-29 16:29:00

አል አዝሓር መንበረ ጥበብ እየሩሳኤም ዙሪያ እንዲመክር የጠራው ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጉባኤ


በግብጽ ርእሰ ከተማ ካይሮ የሚገኘው የሱኒው ታዋቂውና አቢይ አል አዝሓር የምስልምና ሃይማኖት የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ እ.ኤ.አ. እስከ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ኢየሩሳሌም ርእስ ዙሪያ በመነጻጸር የሚመክር በወቅቱ በቅድስት መሬት የተከስተውን ውጥረት እንደ መንደርደሪያ በማድረግ ስለ ከተማይቱ መጻኢ ጉዳይ የሚወያና በዚሁ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አላቸው የሚባሉት መንግሥታት ልኡካንና ተቋማንት ያሳተፈ ዓውደ ጉባኤ እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረቡ ከአል አዝሐር መንበረ ጥበብ የተሰራጨው ዜና የጠቀሱ የግብጽ የመገናኛ ብዙኃን ይጠቁማሉ።

እየተከሰተ ያለው አመጽ  በግድ የለሽነት አለ መመልከት

የግብጽ የመገናኛ ብዙሃን የአል አዝሓር መንበረ ጥበብ ያሰራጨው መግለጫ ጠቀስ ባስተላለፉት ዜና በቅርቡ ኢየሩሳሌም በሚገኘው መስጊድ ፊት ባለው አደባባይ የተቀሰቀሰው ግጭት በማመላከት የእስራኤል መንግሥት የወሰደው የጸጥታና የደህነት ውሳኔ የስልጣኔና የሰብአዊ መረተ ደንብ ላይ ያልጸና ነው ሲል የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይኸንን ጉዳይ ችላ እንዳይል ጥሪ ማቅረቡንም የገለጡት የግብጽ የመገናኛ ብዙኃን አያይዘው፥

ዓለም አቀፍ የሰላም ጉባኤ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ራንቸስኮ በግብጽ አካሂደዉት በነበረው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት በሳቸው አነሳሽነት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በአል አዝሐር መንበረ ጥበብ ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ያለው የሰላም ጉባኤ መካሄዱንም ዘክረው መንበረ ጥበቡ በሰላምና በተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ጉባኤ ሂደት አቢይ አስተዋጽኦ የሚሰጥ መሆኑም የሚነገረለትና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ለሰላም የሚደረጉትት ውይይቶች ጭምር የሚያነቃቃና ተስታፊ ጭምር መሆኑ ይነገራል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.  ፍራንቸስኮ ሰላም በዓለም ዙሪያ ይሰፍን ዘንድ የሚያደርጉት ጥረትና ስለ ሰላም የሚያቀርቡት የማይታክት ጥሪ ይኽ እሳቸው የሚቀርቡት ከፍተኛ አዎንታዊ የሆነው ተግባር የተለያዩ ተቃዋሚ አንጃዎች፡ በተለያዩ መንግሥታት መካከል በጠረጴዛ ዙሪያ ቀርበው እንዲወያዩ ከማድረጉም ባሻገር የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ሰላም ፍትሕ ፍቅርና ወንድማማችነት በተሰኙት እሴቶች ላይ ግንዛቤው እንዲዳብር በማድረግ ተጨባጭ ሰላም በማረጋገጡ ሂደት አቢይ አስተዋጽኦ ያለው እንደ ሆነም በዓለም አቀፍ የሰላም መድረክ የሚታይ በህሉም የሚመሰከር እውነት ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.