2017-07-29 09:13:00

ዝክረ አንደኛው ዓመት 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


“የሚምሩ ብፁዓን ናቸው ምሕረትን ያገኛሉና” (ማቴ. 5,7) በሚል ወንጌላዊ ቃል ተመርቶ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 26 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በፖላንድ ክራኮቪያ ከተማ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዝክረ አንደኛው ዓመት ምክንያት በማድረግ በዚያ ተገኝተው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን በሁሉም አቢያተ ክርስቲያን የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በሚከታተሉት አቢያተ ጽሕፈት አማካኝነት እየታሰበ ነው፡

“ኢየሱስ የእኛ ደጋፊ ነው፡ ዘወትርም ደጋፊያችን ነው። በምንወድቅበት ጊዜ ኢየሱስ ከወደቅንበት ያነሳናል፡ ምንም’ኳ ደካሞች ብንሆንም አርሱ ያፈቅረናል። ከእርሱ ጋር ዓለም ለመለወጥ ትችላላችሁ” የሚል ሃሳብ ላይ አማክለው በዚያ በክራኮቪያ በሚገኘው በምህረት አደባባይ ተገኝተው ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መዝጊያ ዕለት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በለገሱት ስብከት ወጣቶቹን የተማሩ መሓሪያ እንዲሆኑ ማሳሰባቸው ይታወሳል።

ያ የክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በዚያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባወጁት ልዩ የምሕረት ዓመት ወቅት የተካሄደ በመሆኑም በምሕረት ላይ ያማከለ ለመሆኑም የተከተለው ዋናው ወንጌላዊ መርሆ ይመሰክራል። እ.ኤ.አ. ሓምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በዚያች በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከተማ ክራኮቪያ የተካሄደ ሲሆን። ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እ.ኤ.አ. በ 1985 ዓ.ም. ያስጀመሩት እራሳቸው ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መሆናቸው ይዘከራል።

ያ በክራኮቪያው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በሩወን በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባለው መንበረ ታቦት ፊት አባ ዣከስ ሃመል በግብረ ሽበራ መገደል የተሸኘና በዚያኑ እለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ክራኮቪያ እንደደረሱም ወጣቶች በሙሉ በሞቀ ውሉዳዊ ፍቅር አቀባበል በማድረግ በመጀመሪያው ቀን ባካሄዱት ግኑኝነትም መሐሪ ልብ በሚል ሃሳብ ላይ ያማከለ ንግግር በማስደመጥ የእምንት ስማዕታትን በማሰብ መጠለያ ለሌለው ማደሪያ ላጣው መጠለያና ማደሪያው የኢየሱስ መሐሪው ልብ ነው። የእርሱ ልብ የሁሉም ቤት ነው፡ ለተሰደደው ለተናቀው ለጠፋው ሁሉ መጠለያው መሐሪው የኢየሱስ ልብ ነው። መሐሪ ልብ ተካፍሎ መኖርን ያውቃል። ያለው ነገር ሁሉ ከሌላው ጋር የሚካፈል ነው ለሚሰደደው ለሚፈናቀለው የሚያስተናግድ ነው። “ምሕረት ሲባል እድል ነው። ተስፋ ነው ኃላፊነትም ጭምር ነው ነው እማኔ ነው ሌላውን ለማስተናገድ በርን ክፍት ማድረግ ማለት ነው። የሌላውን ሁነት ተካፋይ መሆን ማለት ነው” የሚል ጥልቅ የምሕረት ትርጉም ዙሪያ ያሰመሩበት ሃሳብ ይታወሳል።

በእጅጉ የሁሉንም ልብ የመሰጠው ቅዱስነታቸው የናዚው ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት የብዙዎችን ሕይወት ለሞት የዳረገበትን የአውሽዊዝና የቢርከናው የእልቂት ሰፈር ያካሄዱት ጉብኝት እንደነበርና በዚያ አንድም ቃል ሳያሰሙ በጽሞና ቆመው የሕሊና ጸሎት ሲያዳርሱ የኖሩት ጽሞና በዚያ የእልቂት ሰፈር የተፈጸመው አሰቃቂው ቅትለት ጥልቅ ስቃዩን የሚያስተውልና ከዚያ ከእልቂት ሰፈር የተረፉ ጋር ተገናኝተው በመተቃቀፍ ሰላምታን በመለዋወጥ አብረው የሕሊና ጸሎት በማድረስ በጽሞና በሰው ዘር ላይ የተፈጸመው አሰቃቂው መለከያ የሌሌው እልቂት በሁሉም ልብ ውስጥ እንዲስተነተን አድርገውዋል።

ሌላው ኣዛው ታጉረው የነበሩት ውስጥ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት የነበረውን በመተካት እንዲገደሉ  የጠየቁት ሰማዕት ቅዱስ ማሲሚሊያኖ ኮልበ ታጉረውበት የነበረውን ክፍል ጎብኝተው፡ ከፖላንድ የአይሁድ እምነት አቢይ መምህር በቢርከናው ከዛም በፖላንድ  ከሚያገለግሉት ከ 25 የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት ካህናት በፖላንድ የነበረውን አምባ ገነናዊ ሥርዓት እምቢ በማለት ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ከነበሩት የአገሪቱ ዜጎች ጋር በመገናኘት የከፈሉት መሥዋዕትነት ማድነቃቸውንም ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ክራኮቪያ በሚገኘው ሰቂለ ሕሊናዊቷ የመሐሪው ኢየሱስ መንፈሳዊነት እክብሮትና ስግደት ያስፋፋች የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጠባቂያን ቅዱሳት ውስጥ አንዱ የሆነቸው የቅድስት ፋውስቲና ኮዋልስካ ቅዱስ አድም ያረፈበት በምሕረት ቤተ መቅደስ የፈጸሙት መንፈሳዊ ንግደት እና እዛው ለተገኙት ከኢጣሊያ የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አዘጋጅ አባላት ጋር ተገናኝተው ወጣቶቹ ባቀረቡላቸው ጥያቄዎች ላይ ተንተርሰው አስተምህሮ ሰጥተው፥ ወጣት ትውልድ አገናኝ የሰላም ድልድይ ገንቢ ይሁን በማለት በአጽንኦት ጥሪ ማቅረባቸውና፥

“ወጣት ሆይ የሚለያየውን የግንብ አጥሪ ወይንም ደግሞ አገናኙን የሰላም ድልድይ የምትገነባ ነህ። አንዱን ምረጥ፡ የግንብ አጥር ይለያያል ጥላቻን ያከራል ድልድይ ግን ያገናኛል ያቀራርባል። ለአንድ ሰው ሰላም በማለት እጁቹን ስትጨብጥ ድልድይ ይሰላም እየገነባህ ነው። እጆችህን ከመጨበጥ ይልቅ ለቡጢ ስትጠቀምበት ሌላውንም ስታንቋሽሽና ስታማ ለያይ አጥር ትገነባለህ። ድልድይ መገንባት የሕይወታችሁ እቅድ አድርጉት። ሰብአዊ ድልድይ ገንቡ”

በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ አስታውሶ ቅዱስነታቸው በዚያ በክራኮቪያ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የቀጣቶች ቀን ወቅትም እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም. ከጥር 22 ቀን እስከ ጥር 27 ቀን የሚካሄደው 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በአገረ ፓናማ እንደሚሆንና መርሕ ቃሉም “እነሆ እኔ የጌታ ባርያ ነኝ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” (ሉቃ. 1.38) የሚል በማርያም አፍ የተነገረው በልበ ማሪያም የተጸለየው ወንጌላዊ ቃል እንደሚሆንም ማበሰራቸው ዘክሮ ያመልክታል።  
All the contents on this site are copyrighted ©.