2017-07-29 11:27:00

"በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸመ የሚገኘው ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውር አስፈሪና "አጸያፊ ክስተት" ነው!


“በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ እየተከሰተ የሚገኝ አስፈሪና "አጸያፊ ክስተት" ነው፣ በአሁኑ ጊዜ በምድራችን ላይ ከፍተኛ ገንዘብ የማግኛ ዘዴ እየሆነ የመጣ በጣም "አስፈሪ ወንጀል" ነው፣ ይህንን ለማስቆም ያሉትን ሁሉ አማራጮች አሟጦ መጠቀም ይገባል”።

የዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ይህ ቀደም ሲል ያነበባችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባገኙት አጋጣሚዎች ሁሉ ለመግሥታት እና ጉዳዩ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ለሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት የሰው ልጆች ሕገ-ወጥ ዝውውር ይገታ ዘንድ፣ ይህ አስከፊ እና አሳዛኝ የሆነ ተግባር ይቆም ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪ እንደ ሚያቀርቡ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ደግሞ በመጭው እሁድ ሐምሌ 23/2009 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስተባባሪነት በዓለማቀፍ ደረጃ የሚከበረውና ሕገወጥ የሰው ልጆች ዝውውርን በይፋ በመቃወም የሚከበረውን እለት አስመልክተው ባስተላለፉት ምልእክት እንደ ገለጹት “ይህ ሰቆቃ የተሞላበት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሊገታ ይገባል” ብለዋል።

ባለፈው አመት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሕዳር 7/2016 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ጋር ይህንን የሰው ልጆች ሕገ-ወጥ ዝውውር በማውገዝ በተካሄደው ጉባሄ ላይ ቅዱስነታቸው “በዚህች በምንኖርበት ዓለማችን ከሚታዩት ስቃዮች ሁሉ ለከፍተኛ ስቃይ የተጋለጡት የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰላባ የሆኑ ሰዎች ናቸው፣ ይህም የሰው ልጆች በእግዚኣብሔር የተሰጣቸውን ሰብዓዊ መብት የሚገፍ ዘመናዊ የባርነት ስርዓት ነው፣ በጣም ብዙ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን የዚሁ መከራ ገፈት ቀማሾች ናቸው፣ በአጠቃላይ ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውር በሰባዊነት ላይ የተቃጣ ወንጀል ነው” ብለው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንኑ መልእክታቸውን በድጋሚ በማስትጋባት በመጭው እሁድ እለት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስተባባሪነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውርን በመቃወም ለሚከበረው ቀን ይህን ቀደም ሲል ያስተላለፉትን ምልእክታቸውን በድጋሚ አስተጋብተዋል።

የዚህን  አሰቃቂ ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውር አሳሳቢነት በተመለከተ ብዙ ጥናቶች መደረጋቸውና የዚህን አሰቃቂ ክስተት መስፋፋት በጥልቀት ማጥናት እና እንዲሁም ይህንን ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውር በተመለከተ ማኅበረሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራት በስፋት ሊሠሩ ይገባል ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ብዙኃኑ ሕዝብ በዚህ ጉዳይ ላይ በጥልቀት በመወያየትና ሐሳብ በመለዋወጥ፣ የመንግሥት አካላትን፣ሕግ አውጭዎችን እና ሕግ አስከባሪዎችን፣ እንዲሁም የማሕበራዊ ተቋማትን ባካተተ መልኩ   የተቀናጀ ተግባር በማከናውን ይህ ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውር እንዲቀረፍ መሥራት እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በአጽኖት ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውር እያስከተለ የሚገኘው ከፍተኝ የሆነ ስቆቃና መከራ በብዙኃኑ ዘንድ ከእቁብ ሳይቆጠር በቸልተኝነት ስሜት እየታየ እንደ ሚገኝ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን የቸልተኝነት ስሜት ለማስወገድ ይቻል ዘንድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ምድረኮች ሊከፈቱ እንደ ሚገባውም ቅዱስነታቸው አስምረውበታል።

ይህንን ሕገ-ወጥ የሰው ልጆች ዝውውርን በተመለከተ በተለያየ ደረጃ እና ዓይነት ከፍተኛ ጥናቶች መደረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን  የፊታችን እሁድ እለት የሰው ልጆች ሕገ-ወጥ ዝውውርን በዓለማቀፍ ደረጃ በማውገዝ የሚከበረውን እለት አስምልክቶ Save The Children የተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት “የ2017 ታናንሽ የማይታዩ ባሪያዎች” በሚል አርእስት ባወጣው ሪፖኦርት ላይ የወንጀሉ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ስም ዝርዝር፣ በዚህ ወንጀል ድርጊት ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ ሀገራት፣ የዚህ ወንጀል ፈጻሚ ሰዎች ሚና እና ኃላፊነት የሚመለከት ስፊ ዘግባ ይዞ መውጣቱ ታውቁዋል።

ይህ Save the Children የተባለው የብጎ አድርጎት ድርጅት በተለይም ደግሞ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በ106 ሀገራት ላይ ትኩረቱን ባደረገው ሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው በዓለም ዙሪያ ከ 21 እስከ 35 ሚልዮን የሚገመቱ ሰዎች በዚሁ የሰው ልጆች የሕገ-ወጥ ዝውውር መረብ ሰለባ መሆናቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን በተለይም ደግሞ የዚህ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ከሆኑት ከ4 ሰዎች አንዱ ለአቅመ አዳም ያልደረሰ/ች ታዳጊ ወጣት መሆኑን/መሆኑዋን ሪፖርቱ የገለጸ ሲሆን ይህም ም የጉዳዩን አሳሳቢነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ እንደ ሆነም ተገልጹዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.