2017-07-24 15:32:00

ዛምቢያ፥ ዝክረ 125 ኛ ዓመት ህልወት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዛምቢያ


በዛምቢያ ዝክረ 125ኛው ዓመት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ህላዌ ምክንያት የሉሳካ ሊቀ ጳጳስና የአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ተለስፎረ ጆርጅ ምፑንዱ ባስተላለፉት መልእክት “በዛምቢያ የክርስትና ችቦ ቦግ ለማድረግና የክርስትናውን ብርኃን ለማስተላለፍ በስብከተ ወንጌል ተልእኮ ካለ ምንም ማቅማማትና ማመንታት መላ ሕይወታቸውን የሰው የተለያዩ የልኡካነ ወንጌል ማኅበር ካህናትና ደናግል ጥልቅ ምስጋና ማቅርረብ ይገባናል” እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

“በእነዚያ ልኡካነ ወንጌል የተላለፈው ክርስቲያናዊ ባህል ወራሾች የሆንን ያንን እነርሱ በእምነት በፍቅርና በተስፋ ያወረሱንን እምነት ምክንያት ላለብን ውሉዳዊ ዕዳ ለእግዚአብሔር በሀሴት በማመስገንና በአንድ ማእድ ዙሪያ ሆነን በመጸለይ እንካፈላለን” ያሉት ብፁዕ አቡነ ምፑንዱ አያይዘው፥ እነዚያ ቀደምት ልኡካነ ወንጌል በዛምቢያ እንደደረሱ በአስፍሆተ ወንጌል በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎታቸው መሳካት የተባበሩዋቸው በፍቅር ላስተናገዱዋቸው የአገሪቱ ዜጎች እናመሰግናለን። ባስተርጓሚነት በትምህርተክ ክርስቶስ አስተማሪነት እምነት በማስፋፋት ረገድ ቀደምት ልኡካንን የተባበሩት የአገሪቱ ዜጎችን ምክንያትም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን”

 እንዳሉ አስታወቀ።

በዚህ ዝክረ 125ኛው ህላዌ ክርስትና በዛምቢያ ምክንያት በተደረገው በዓል የዛምቢያው መንግሥት በአገሪቱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ ጠሊቅ እወቅና በመስጠት በማኅበራዊ ያገልግሎት ለምሉእ የሰብአዊ እድገት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን የድኾች አገሮች የብድር ጫና ቅነሳ ከዚህ በዘለለም ስረዛ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማነቃቃት ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሰጠው አቢይ ድጋፍ አስተዋጽኦ የተሟላ እድገት በማረጋገጥ ጎዳና የሰጠው አቢይ አስተዋጽኦ የጠቀሱት የዛምቢያ ርእሰ ብሔር ኢኖንገ ዊና ምስጋና ማቅረባቸው የጠቀሰው ፊደሰ የዜና አገልግሎት አያይዞ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር በትምህርትና በሕንጸት በጤና ጥበቃ ዘርፍ በግብረ ሰናይ ማንም የማይነጥል ሰውን ማእከል በማድረግ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዛምቢያ ለምትሰጠው አገልግሎት ማመስገናቸውን ገልጠው ይኽ ዝክረ 125ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ኅልውና በዛምቢያ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም  በተለያየ መንፈሳዊ ባህላዊ መርሃ ግብሮች የተከፈተ ሆኖ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁ ያመለክታል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ደምረው ሱራፍኤል  ሊቃነ ጳጳሳት ዘካቶሊክውያን የኢትዮጵያ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር  የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ሊቀ መንበር በዛምቢያ ዝክረ 125ኛው ዓመት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ህላዌ ክብረ በዓል ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት በቅድሚያ ምስጋና ለእግዚአብሔር በማቅረብ ያለፈውን ታሪክ የወቅቱን ሁኔታ ለማንበብና ከዚህ በመደርደርም መጻኢ ላይ ለማነጣጠር የሚያግዝ እንዲሆን በማሳሰብ በምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብርት ዛምቢያ በተለያየ መስክ የሰጠቸውን አስተዋጽኦ ጠቅሰው በዚህ ክብረ በዓል ምክንያት የሁሉም የአገሪቱ ምእመናን ሕዝግበ እግዚአብሔር በተለይ ደግሞ የድኾች ሁነተ ሕይወት በመጋራት በዛምቢያ ለምትገኘው ካቶሊክዊት ቤተ ክርስቲያን መልካም ዝክረ 125ኛው በዓል ተመኝተው አገልግሎትዋንና መላ አገረ ዛምቢያያንም እግዚአብሔር ይባርክ ብለው ያስተላለፉት መልእክት ማጠቃለላቸው የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ይፋዊ ድረገጽ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችሏል።   
All the contents on this site are copyrighted ©.