2017-07-24 15:26:00

ስፐይን፡ ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሠራተኞች ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ፥ የሥራ ዓለም በወንጌል መስበክ


በስፐይን አቪላ ከተማ ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሠራተኞ ማኅበር ቅዱስ  አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት ወንጌል በሥራ ዓለም ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን የሥራውን ዓለም በወንጌል መስበክ የሥራውን ዓለም ሰብአዊነት ያማከለ እንዲሆን ያደርገዋል። ስለዚህ የሥራው ዓለም በወንጌል መስበክ የሥራውን ዓለም ሰብአዊነት ለበስ ማድርግ ይሆናል የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ በማተኮር ባስተላለፉት መልእክት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም.  ከ 79 አህጉራት የተወጣጡ ተጋባእያን በማሳተፍ ለአንድ ሳምንት የተካሄደው 50ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይኽ መሬት ቤትና ሥራ ለሕይወት ክብር በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሠራተኞች ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ የባወጣው የጋራ የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ፥

“የዚህ ዓለም አቀፍ የሠተኞ ማኅበር ተግዳሮት የሥራውን ዓለም በወንጌል የመስበክ ተልእኮ ነው፡ ስለዚህ ስብከተ ወንጌል በሥራው ዓለም ቀጣይነት ባለው አግባብ ቃልና ሕይወትን ያስተሳሰረ ምስክርነት በማቅረብ መከወን አስፈላጊ ነው። መልካም ዜና እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር ያለው የሰብአዊነት እቅድ በእርሱ አምሳያና አርአያ የፈጠረውን ሰብ ሁሉ በግልም በማኅበም ማእከል ማድረግ”

የሚል ሃሳብ ያሰመረ መሆኑ ፊደስ የዜና አገልግሎ አመለከተ።

ይኽ 42 ተጋባኣያን በማሳተፍ የተካሄደው ጠቅላይ ዓውደ ጉባኤ የሥራ ዓለም ጠበብት የተለያዩ የብሔራዊ የክርስቲያን ማኅበር ተወካዮች ያሳተፈ፥

የሠራተኛው ድምጽ በቤተ ክርስቲያን ሁሌ ይስተጋባል

ዓለም አቀፍ የክርስቲያኖች ማኅበር 50ኛው ጠቅላይ ጉባኤው ማኅበሩ የተመሰረተበት ዝክረ 50ኛው ዓመት ጋር በማጣመር ያካሄደው መሆኑ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አያይዞ፥ ማኅበሩ የመላ ዓለም ሠራተኞች ዕለታዊ ተመክሮ በመካፈል ስለ የሥራው ዓለም ጉዳይ በተመለከተም ከቤተ ክርስቲያንና ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚሰጠውን ሥልጣናዊ ትምህርት በመከተል በዚሁ 50ኛው ጠቅላይ ጉባኤው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይድረስ ለአቪላ ሰበካ ጳጳስ በኩል ባስተላለፉት መልእክት የሠራተኛው ድምጽ በቤተ ክርስቲያን ሁሌ የሚያስተጋባ መሆኑና ቤተ ክርስቲያን ለሠራተኛው ዓለም የሥራና ሠራተኞች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ቅርብ በመሆን ሁሉም ሰብአዊ ክብሩ ተከብሮለት በሥራው ዓለም የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ማንም በማይነጥል ሁኔታ እንዲከበርለት ማሳሰባቸው ጉባኤው ባወጣው የፍጻሜ ሰነድ ላይ በማካተት፥ ቤተ ክርስቲያን ለሠራተኛውና ለሥራው ዓለም ምንኛ ቅርብ መሆኗ ያረጋግጣል።

የሥራው ዓለም በወንጌል የመስበክ ተልእኮ

ይኽ ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ማኅበር በዓለም ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የተለያዩ የሠራተኛ ማኅበራት ወቅታዊው ሁኔታ አቢይ ግምት በመስጠት የራሱን ኃላፊነትና ያለው ውስንነትንም ግንዛቤ በመስጠት፥ ሰላም የተሞላው ቅንና ፍትሐዊ ትብብር የሰፈነበት ተቀባይነት ያለው ዓለም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የራሱን ኃላፊነት በመወጣት መላ የዓለም ሠራተኛው ኅብረተሰብ በብሔራዊ በአውራጃ በወረዳ በመደራጀት የዚህ ኃላፊነት ተካፋይ እንዲሆን ይኽ የክርስቲያን ሠራተኞች ማኅበር የሥራውን ዓለም በወንጌል በመስበክ ኃላፊነት ተጠምዶ ሰብአዊነት የሚያስፋፋ መሆኑ ጉባኤው ባወጣው የፍጻሜ ሰነድ በማብራራት እንዳሰመረበት ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በሠራተኛው ማኅበራትና በሐዋርያዊ ግብረ ኖልው መካከል ግኑኝነት እንዲኖር ማነቃቃት

ጉባኤው ባወጣው የፍጻሜ ሰነድ፥ ዓለም አቀፉ የክርስቲያን ሠራተኞች ማኅበር የሥራ እቀዶቹን ጠቁሞ፥ ያለበት ኃላፊነት አጠናክሮ መኖር የሚከተለውን የሕይወት እርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለው እምነት ጠንክሮ እምነቱን በሕይወት መኖር እንዳለበና የቤተ ክርስቲያን የሥነ ማሕበራዊ ዓቀጸ እምነታዊ ትምህርትን በጥልቀት አውቆ ይኸንን ሁሉ በግልና በማኅበር ከሕይወቱ ጋር አሳክቶ በዓለም ያለው የሠራተኛና የሥራው ዓለም ወቅታዊው ሁኔት በማጤን ያንን የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥሰት የሚታይበትን ሁኔታ በማውገዝ መቃወም የሰዎች እኩልነት ማነቃቃት ለሥራ አጥ የኅበረተሰብ ክፍል ማኅበራዊ ድጎማ ያለው አስፈላጊነት በመሳሰብ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የተከበረ ሥራ ቀን እንደሚሳተፍም ባወጣው ሰነድ እንዳመለከተ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.