2017-07-22 08:35:00

ብፁዕ አቡነ ሳይትዝ፥ በወንጌል መሠረት ሌላውን ማስተናገድ


በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በተክሳስ ግዛት ለሚገኘው ለኤል ፓሶ ሰበካ ጳጳስ ብፅዕ አቡነ ማርክ ሳይትዝ፥ “ሐዘንና ስቃይ ይወገዳል” በሚል ርእስ ሥር ለሰበካቸው ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት፥ የአንድ አገር ደህንነትና ጸጥታ ለያይ የግንብ አጥር በማቆም በሮችን ለስደተኛውና ለተፈናቃዩ በመዝጋት የሚረጋገጥ እንዳልሆነ በጥልቀት በማሳሰብ እግዚአብሔር በፈጠረው ዓለም ውስጥ ለሁሉ በእርሱ ይሁን ለተባለው ፍጡር ሁሉ ቦታ አለው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ሳይትዝ ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት፥ “እንደ መጋቤ የእኔ ኃላፊነት” ይላሉ “የኢየሱስ ወንጌል ነው” ስለዚህ “በመካከላችሁ መጻእተኛ ልክ እንደ እናንተ በመካከላችሁ እንደ ተወለደ አስቡት ተቀበሉት” ብለው ክዚህ ጋር አያይዘውም የአገራቸው መንግሥት የሚከተለው የስደተኛውና የተፈናቃዮች-የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ የመቆጣጠሪያ ሕግ በትክክል በማጤና በስፋት የብዙ ስደተኞችና የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ቀጥተኛ ገጠመኝ ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት ለሁሉም እንደ ያስተንትኖ ሃሳብ አካተው በማቅረብ ስለ ስደተኛውና ስለ ፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂው ወንድም ወይንም እህት በተባለና በይሆናል እንዲሁም በፍርሃት ከመግለጹ ይልቅ ከእራሱ እንደበት ስለ ሁኔታው ግንዛቤ እንዲኖርና የሰው ልጅ በተስፋ የሚኖር ነው፡ ስለዚህ ወደ ተስፋ እንዳይጓዝ ለማድረግ አይቻልም። በቅዱስ መጽሓፍም ይሁን በዓለም ታሪክ ውስጥ በስፋት የሚረጋገጥ እውነት መሆኑ በማብራራት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት ወር 2016 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግስታት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ኣካሂደው በዚያ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና መክሲኮን በሚያዋስነው በሲዩዳድ ኹዋረዝ ክልል መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፥ በስደተኛው ላይ የሚፍፈጸመው ቅትለትና ብዝበዛና አልድልዎ ፈጽሞ እንዲወገድ በኃይለ ቃል ያስተላለፉት ጥሪ ጠቅሰው፥ በሥልጣን ላይ ያለው የተመረጠው መንግሥት አሁንም የስደተኛውና የፖለቲካ ጥገኝነት ስለ ሚጠይቀው የመቆጣጠሪያ ሕግ  መንግሥት በተለወጠ ቁጥር የውድቅ ሆኖ በሌላ የሚተካ እንደ የመንግሥት መቀያየር የሚቀያየር ሳይሆን ምሉእና ቋሚ ሰውን ማእከል ያደረገ የሕይወት ባህል የሚያንጸባርቅ ሊሆን ይገባዋል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፥ በማንኛውም አገሮም ይሁን የስደተኛው የመቆጣጠሪያው ሕግ የስደተኛው ሕይወት እንደ ዋጋ የሚያስከፍል ስደተኛው ለሌላ ችግር የሚያጋልጥ  መሆን የለበትም ብለው በወንዝ በተራራ  በመሳሰሉት መልክኣ ምድራዊ አቀማመጥ አማካኝነት የተለያየን ሆነን ይባስ ሌላውን የሚያገል የሚነጥል አግላይና ነጣይ ኤኮኖሚ ፖሊቲካ በማስፋፋት እንዲባባስ በማድረግ ከዚህ በመንደርደርም የሚፈጠረው ኢፍትሐዊ የሆነ የስደተኛ የመቆጣጠሪያ ደንብ ወደ ጎን በማድረግ የሚለያየን መልክኣ ምድራዊ አቀማመጥ ለመገናኘት ለመተዋወቅ የሚገፋፋ ይሁን የተለያየን ብንሆንም ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችንን ወደ አዲሱቷ እየሩሳሌም በመምራት አዲስ ሰብአዊነትን አጽንተዋል በማለት ያስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት እንዳጠቃለሉ የሐዋርያዊ መልእክት ጽማሬውን ያጠናቀረው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።   








All the contents on this site are copyrighted ©.