2017-07-20 15:31:00

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አዲስ ሊቀ መንበር መረጠ


የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ 115 ኛው ምሉእ ዓመታዊ ዓውደ ጉባኤውን እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 8 ቀን እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የጉባኤው አዲስ ሊቀ መንበር በመምረጥ ማጠቃለሉ አሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ጠቅሶ አያይዞም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጉባኤው መልእክት አስተላልፈው እንደነበርና ዓመታዊው ስብሰባው ፍርያማ እንዲሆን እያንዳንዱ የምክር ቤቱ አባል በተስፋ በፍቅርና በእምነት እያደገ በቃልና በሕይወት መስካሪያንና የመላ ፊሊፒንስ ወጣቶች ተንከባካቢያን የዚያ ታማኝ የሆነውን በቃልና በሕይወት ብፁዓን ጳጳሳቱ የሚመሰክሩት እምነትም ርህራሄ ውበትና ውህበትን የሚያጎላ ሆኖ፡ ወጣቱ ትውልድ ደስተኛ ወንጌላዊ ልኡክ እንዲሆን አበረታቱት ብለው እንደነበርም ገልጦ ይኽ ማኒላ በሚገኘው በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ የጉባኤ ኣዳራሽ የተካሄደው ጉባኤ ብፁዕ ኣቡነ ራሙሎ ቫለስ የጳጳሳቱን ጉባኤ በሊቀ መንበርነት የመሩት ያገልግሎት ዘመናቸውን ላጠናቀቁት የሊንጋየን ደጉፓን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ሶክራተስ ቪለጋስን እንዲተኩ መርጠዋል ሲል ይጠቁማል።

66 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እ.ኤ.አ. በ 1976 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት ከዛም በ1997 ዓ.ም. የኪዳፓዋን ጳጳስ እንዲሆኑ የተሰየሙና በመቀጠልም በ 2006 ዓ.ም. ለዛምቦአንጋ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከዛም በ 2012 ዓ.ም ወደ ዳቫኦ ሰበካ በተዛወሩት የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት 20ኛው ሊቀ መንበር እንዲሆኑ የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ቫለስ በአገሪቱ የሚገኙት 86 የቤተ ክርስቲያን ሕጋውያን ተቋማት ጭምር የሚመሩ ሲሆን፡ እ.ኤ.አ. በ 1983 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት የተቀበሉት ከ 2016 ዓ.ም. ጀምረው በሰበካ ካሉአን በማገልገል ላይ የነበሩት የስነ መጽሓፍ ቅዱስ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ፓብሎ ቪርጂሊዮ ዳቪድ ምክትል ሊቀ መንበር እንዲሆኑ ተመርጠዋል ሲል የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ ብፁዕ አቡነ ቪርጂሊዮ ዳቪድ እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም.  ለቅዱስ ፈርናንዶ በፓምፓንጋ ሰበካ ረዳት ጳጳስ በመሆን ለአስር አመት እንዳገለገሉም ይጠቁማል።

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ለሚያቅፈው ቋሚ ድርገቶችን በሊቀ መንበርነት የሚመሩትን ከመረጠ በኋላ ኣባ ማርቪን መጂያ የምክር ቤቱ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ሆነው እንዲቀጥሉ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ እንደመረጣቸውና የቋሚ ድረገቶች ሊቀ መናብርት ሆነው የተመረጡትም ኃላፊነታቸው እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በኋላ በይፋ እንደሚጀምሩም ኤሺያን ኔውስ የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ዋቢ በማድረግ ያመለክታል።    
All the contents on this site are copyrighted ©.